በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 11

በጋለ ስሜት መናገር

በጋለ ስሜት መናገር

ሮም 12:11

ፍሬ ሐሳብ፦ ግለት በሚንጸባረቅበት መንገድ በመናገር የአድማጮችህን ስሜት ለመቀስቀስና ለተግባር ለማነሳሳት ጥረት አድርግ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ትምህርቱ ልብህን ሊነካው ይገባል። ንግግርህን በምትዘጋጅበት ጊዜ፣ ትምህርቱ ስላለው ጥቅም ቆም ብለህ አስብ። ከልብ በመነጨ ስሜት መናገር እንድትችል ትምህርቱን በደንብ እስኪዋሃድህ ድረስ አጥናው።

  • ስለ አድማጮችህ አስብ። የምታነበው ወይም የምትናገረው ነገር አድማጮችህን እንዴት እንደሚጠቅማቸው ለማሰብ ሞክር። አድማጮችህ ከትምህርቱ የሚያገኙት ጥቅም ቁልጭ ብሎ እንዲታያቸው በሚያደርግ መንገድ ንግግርህን ተዘጋጅ።

  • ንግግርህን ሕያው በሆነ መንገድ አቅርብ። ሞቅ ባለ ስሜት ተናገር። ተስማሚ የሆኑ አካላዊ መግለጫዎችን ተጠቀም፤ ፊትህ ላይ የሚነበበው ነገርም የልብህን ስሜት የሚገልጽ ሊሆን ይገባል።