በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 14

ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ

ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ

ዕብራውያን 8:1

ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ ንግግርህን በትኩረት እንዲከታተሉ እርዳቸው፤ በተጨማሪም እያንዳንዱ ዋና ነጥብ ከንግግርህ ዓላማና ጭብጥ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ግልጽ አድርግላቸው።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • የንግግርህን ዓላማ ለይተህ እወቅ። የንግግሩ ዓላማ መረጃ መስጠት ነው? አንድ ነገር ትክክል መሆን አለመሆኑን ማሳመን ነው? ወይስ አድማጮችህን ለተግባር ማነሳሳት? ይህን ከግምት በማስገባት ንግግርህን አዋቅር። ዋና ዋና ነጥቦቹን የምታብራራበት መንገድ የንግግርህን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችል መሆን አለበት።

  • የንግግርህን ጭብጥ ጎላ አድርገህ ግለጽ። ንግግርህን ስታቀርብ ከጭብጡ ጋር የተያያዙ ቁልፍ ቃላትን ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ቃላትን በተደጋጋሚ ጥቀስ።

  • ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች ግልጽና ያልተወሳሰቡ እንዲሆኑ አድርግ። ከጭብጡ ጋር የሚዛመዱትንና በተመደበልህ ጊዜ ውስጥ በደንብ ማብራራት የምትችላቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ብቻ ምረጥ። ዋና ዋና ነጥቦችን አታብዛ፤ እያንዳንዱን ዋና ነጥብ በግልጽ ተናገር፤ አንዱን ዋና ነጥብ አብራርተህ ወደ ሌላው ከመሸጋገርህ በፊት ትንሽ ቆም በል፤ የንግግርህ ፍሰት ሳይስተጓጎል ከአንዱ ወደ ሌላው ነጥብ ለመሸጋገር ጥረት አድርግ።