በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 17

በቀላሉ የሚገባ

በቀላሉ የሚገባ

1 ቆሮንቶስ 14:9

ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮች መልእክቱን በቀላሉ መረዳት በሚችሉበት መንገድ ትምህርቱን አቅርብ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ጥሩ ዝግጅት አድርግ። ትምህርቱን ቀላል በሆነ መንገድ እንዲሁም በራስህ አባባል ማቅረብ እንድትችል ርዕሰ ጉዳዩን በደንብ መረዳት ይኖርብሃል።

  • አጫጭር ዓረፍተ ነገሮችንና ያልተወሳሰቡ ሐረጎችን ተጠቀም። ረዘም ያሉ ዓረፍተ ነገሮችን መጠቀም የምትችል ቢሆንም ዋና ዋና ነጥቦችን ለማስተላለፍ እጥር ምጥን ያሉ ዓረፍተ ነገሮችንና ሐረጎችን መጠቀሙ የተሻለ ነው።

  • ያልተለመዱ ቃላትን ትርጉም አብራራ። በተቻለ መጠን፣ ያልተለመዱ ቃላትን ላለመጠቀም ጥረት አድርግ። አድማጮችህ የማያውቋቸውን ቃላት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሰዎችን ወይም ጥንታዊ መለኪያዎችንና ልማዶችን የግድ መጥቀስ ካለብህ ተጨማሪ ማብራሪያ ስጥ።