በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 18

ግንዛቤ የሚያሰፋ

ግንዛቤ የሚያሰፋ

1 ቆሮንቶስ 9:19-23

ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ ርዕሰ ጉዳዩን እንዲያስቡበት ብሎም ጠቃሚ ትምህርት እንዳገኙ እንዲሰማቸው በሚያደርግ መንገድ ትምህርቱን ለማቅረብ ጥረት አድርግ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • አድማጮችህ ስለ ጉዳዩ ያላቸውን እውቀት ግምት ውስጥ አስገባ። ከዚህ በፊት የሚያውቋቸውን ነገሮች እንዲሁ ከመድገም ይልቅ ርዕሰ ጉዳዩን ከሌላ አቅጣጫ እንዲመለከቱት እርዳቸው።

  • ምርምር አድርግ እንዲሁም አሰላስል። ቁልፍ የሆኑ ነጥቦችን ለማስረዳት፣ አድማጮች ብዙም የማያውቋቸውን መረጃዎች ወይም ወቅታዊ ሁኔታዎች ጥቀስ። ስለምታቀርበው ትምህርት እንዲሁም በርዕሰ ጉዳዩና በምትጠቅሳቸው መረጃዎች መካከል ስላለው ዝምድና በጥሞና አስብ።

  • የትምህርቱን ጠቀሜታ አጉላ። ከመጽሐፍ ቅዱስ የምትጠቅሳቸው ሐሳቦች አድማጮችን በዕለታዊ ሕይወታቸው እንዴት ሊጠቅሟቸው እንደሚችሉ ግለጽ። ከአድማጮችህ ሕይወት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሁኔታዎች፣ አመለካከቶችና ድርጊቶች እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ትምህርቱን አብራራ።