በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 2

በጭውውት መልክ መናገር

በጭውውት መልክ መናገር

2 ቆሮንቶስ 2:17

ፍሬ ሐሳብ፦ የራስህን ተፈጥሮአዊ አነጋገር ተጠቅመህ ከልብ በመነጨ ስሜት ተናገር፤ አነጋገርህ ስለ ርዕሰ ጉዳዩም ሆነ ስለ አድማጮችህ ምን እንደሚሰማህ የሚያሳይ ይሁን።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ወደ ይሖዋ ጸልይ እንዲሁም በሚገባ ተዘጋጅ። በራስህ ላይ ሳይሆን በመልእክቱ ላይ ለማተኮር እንዲረዳህ ወደ ይሖዋ ጸልይ። የምታስተላልፋቸው ዋና ዋና ነጥቦች ቁልጭ ብለው ይታዩህ። በጽሑፉ ላይ የሰፈሩትን ሐሳቦች ቃል በቃል ከመድገም ይልቅ ነጥቡን በራስህ አባባል ግለጸው።

  • ከልብ በመነጨ ስሜት ተናገር። መልእክቱ ለአድማጮችህ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ቆም ብለህ አስብ። በእነሱ ላይ ትኩረት አድርግ። እንዲህ ካደረግክ አቋቋምህ፣ አካላዊ መግለጫዎችህ እንዲሁም በፊትህ ላይ የሚነበበው ስሜት ከልብህ እንደምትናገር የሚያሳይና ወዳጃዊ መንፈስ የሚንጸባረቅበት ይሆናል።

  • አድማጮችህን እያየህ ተናገር። በአካባቢያችሁ እንደ ነውር የማይታይ ከሆነ አድማጮችህን ፊት ለፊት እያየህ ተናገር። ንግግር በምታቀርብበት ጊዜ አድማጮችህን በጥቅሉ ገረፍ አድርገህ ከማየት ይልቅ የተለያዩ ግለሰቦችን በየተራ እያየህ ለመናገር ጥረት አድርግ።