በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 20

ግቡን የሚመታ መደምደሚያ

ግቡን የሚመታ መደምደሚያ

መክብብ 12:13, 14

ፍሬ ሐሳብ፦ መደምደሚያህ፣ አድማጮችህ ትምህርቱን አምነው እንዲቀበሉና እርምጃ እንዲወስዱ የሚያነሳሳ መሆን ይኖርበታል።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • መደምደሚያህ ካነሳኸው ርዕሰ ጉዳይ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ መሆን ይኖርበታል። ስታብራራቸው የነበሩትን ዋና ዋና ነጥቦችና ጭብጡን ደግመህ መናገር አሊያም በሌላ አባባል መጥቀስ ትችላለህ።

  • አድማጮችህን ለተግባር አነሳሳቸው። አድማጮችህ ሊወስዱት የሚገባው እርምጃ ምን እንደሆነ እንዲሁም ይህን ማድረግ ያለባቸው ለምን እንደሆነ ግለጽ። ትምህርቱ አስፈላጊ እንደሆነ እንዲሁም የምትናገረውን ነገር ከልብህ እንደምታምንበት በሚያሳይ መንገድ ተናገር።

  • መደምደሚያህ አጭርና ያልተወሳሰበ ይሁን። አዳዲስ ዋና ዋና ነጥቦችን አታንሳ። በተቻለህ መጠን ጥቂት ቃላት ተጠቅመህ አድማጮችህን ለተግባር አነሳሳቸው።