በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 8

ትምህርት አዘል ምሳሌዎች

ትምህርት አዘል ምሳሌዎች

ማቴዎስ 13:34, 35

ፍሬ ሐሳብ፦ የአድማጮችህን ትኩረት የሚስቡና ዋናውን ነጥብ ለማጉላት የሚረዱ ቀለል ያሉ ምሳሌዎችን በመጠቀም ንግግርህ ማራኪ እንዲሆን ማድረግ ትችላለህ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ቀላል የሆኑ ምሳሌዎችን ተጠቀም። ኢየሱስ እንዳደረገው ቀላል ምሳሌዎችን በመጠቀም ከባድ ወይም ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን ማስረዳት ትችላለህ። ምሳሌውን የሚያወሳስቡ አላስፈላጊ ዝርዝር ነጥቦችን አትጥቀስ። የምትጠቀምበት ምሳሌ ከትምህርቱ ጋር የሚጣጣም ሊሆን ይገባል፤ ምሳሌው ከነጥቡ ጋር እንዴት እንደሚያያዝ ግልጽ ካልሆነ አድማጮችህ ግራ ሊጋቡ ይችላሉ።

  • ስለ አድማጮችህ አስብ። ከአድማጮችህ ሕይወት ጋር የተያያዙና ትኩረታቸውን ሊስቡ የሚችሉ ምሳሌዎች ተጠቀም። አድማጮችህን የሚያሸማቅቁ ወይም ቅር የሚያሰኙ ምሳሌዎች አትጠቀም።

  • ዋናው ነጥብ ላይ ትኩረት አድርግ። ምሳሌህ ዝርዝር ሐሳቦችን ሳይሆን ዋናውን ነጥብ የሚያጎላ ሊሆን ይገባል። አድማጮችህ ምሳሌውን ብቻ ሳይሆን ከምሳሌው የሚገኘውን ትምህርትም እንዲያስታውሱ እርዳቸው።