ጥናት 9
በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ማስተማር
ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
-
ትምህርቱን ይበልጥ ግልጽ የሚያደርጉ ነገሮችን ተጠቀም። ዋና ዋና ነጥቦችን ለማጉላት ሥዕሎችን፣ ካርታዎችን፣ የጊዜ ሰሌዳዎችን ወይም ሌሎች የሚታዩ ነገሮችን ተጠቀም። እርግጥ በጣም አስፈላጊ ላልሆኑ ነጥቦች ይህን ማድረግ አያስፈልግም። አድማጮችህ፣ ለማስተማሪያነት የተጠቀምክበትን ነገር ብቻ ሳይሆን ማጉላት የፈለግከውን ነጥብም እንዲያስታውሱ እርዳቸው።
-
ለማስተማር የምትጠቀምበት ነገር ለአድማጮችህ በደንብ የሚታይ ሊሆን ይገባል።