በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ደቀ መዛሙርት ማድረግ

ምዕራፍ 10

ቁርጠኝነት

ቁርጠኝነት

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “የአምላክን ምሥራች ለማካፈል ብቻ ሳይሆን ራሳችንን ጭምር ለእናንተ ለመስጠት ቆርጠን ነበር፤ ምክንያቱም እናንተ በእኛ ዘንድ እጅግ የተወደዳችሁ ነበራችሁ።”—1 ተሰ. 2:8

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ዮሐንስ 3:1, 2ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1.   ሀ. ኒቆዲሞስ ኢየሱስ ጋ በምሽት መሄድ የመረጠው ለምን ሊሆን ይችላል?—ዮሐንስ 12:42, 43ን ተመልከት።

  2.  ለ. ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. ለሰዎች ፍቅር ካለን ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ለመርዳት ቁርጠኛ እንሆናለን።

ኢየሱስን ምሰል

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪህ በሚመቸው ጊዜና ቦታ አጥኑ። የምታስጠናው ሰው የሚመርጠው ቀንና ሰዓት ይኖር ይሆን? የት ቢያጠናስ ይመቸዋል? በሥራ ቦታው፣ ቤቱ ወይስ ሌላ ቦታ? በተቻለህ አቅም ፕሮግራምህን ከእሱ ጋር ለማስማማት ጥረት አድርግ።

4. በቋሚነት አጥኑ። የማትኖርበት ሁኔታ ከተፈጠረ ጥናታችሁን አትሰርዝ። ከዚህ ይልቅ እንዲህ ማድረግ ትችል ይሆን?

  1.   ሀ. በዚያው ሳምንት በሌላ ቀን ማጥናት

  2.  ለ. በስልክ ወይም በቪዲዮ ኮንፈረንስ ማጥናት

  3.  ሐ. ሌላ አስፋፊ ጥናቱን እንዲመራ ማመቻቸት

5. ትክክለኛ አመለካከት እንዲኖርህ ጸልይ። ተማሪው በቋሚነት ለማጥናት ወይም የተማረውን ተግባራዊ ለማድረግ ቢቸገርም እንኳ ተስፋ እንዳትቆርጥበት ወደ ይሖዋ ጸልይ። (ፊልጵ. 2:13) መቼም ግለሰቡ ጥሩ ባሕርያት ይኖሩታል፤ እነዚያ ላይ ለማተኮር እንዲረዳህ ጸልይ።