በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ውይይት መጀመር

ምዕራፍ 2

ተፈጥሯዊ አነጋገር

ተፈጥሯዊ አነጋገር

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “በትክክለኛው ጊዜ የተነገረ ቃል . . . ምንኛ መልካም ነው!”—ምሳሌ 15:23

ፊልጶስ ምን አድርጓል?

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም የሐዋርያት ሥራ 8:30, 31ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1.   ሀ. ፊልጶስ ውይይቱን የጀመረው እንዴት ነው?

  2.  ለ. ውይይቱን የጀመረበትና እውነትን ለዚህ ሰው ያስተዋወቀበት መንገድ የጭውውት ለዛውን የጠበቀ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

ከፊልጶስ ምን እንማራለን?

2. ውይይቱን ለመምራት ከመሞከር ይልቅ ጭውውቱ ራሱ እንዲመራን ከፈቀድን የምናነጋግረው ሰው ዘና ይላል፤ መልእክቱን ለመስማትም ፈቃደኛ ሊሆን ይችላል።

ፊልጶስን ምሰል

3. ጥሩ አድርገህ ታዘብ። በሰውየው የፊት ገጽታ ላይ የሚነበበው ነገርና አኳኋኑ ስለ እሱ ብዙ የሚነግረን ነገር አለ። ግለሰቡ ሊያነጋግርህ የሚፈልግ ይመስላል? ከሆነ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለማስተዋወቅ በቀላሉ ጥያቄ ልታነሳለት ትችላለህ፤ ለምሳሌ “አምላክ፣ ስም እንዳለው ሰምተህ ታውቃለህ?” ልትለው ትችላለህ። ግለሰቡ ሊያዋራህ የማይፈልግ ከሆነ አታስገድደው።

4. ትዕግሥተኛ ሁን። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ለማንሳት አትቸኩል። በውይይቱ ላይ ይህን ማንሳት ተስማሚ የሚሆንበትን ጊዜ ጠብቅ። አንዳንድ ጊዜ ይህን ለማድረግ የሚያስችል አመቺ አጋጣሚ የምታገኘው ግለሰቡን በሌላ ጊዜ ስታገኘው ሊሆን ይችላል።

5. እንደአስፈላጊነቱ ለውጥ አድርግ። ውይይታችሁ ወዳላሰብከው አቅጣጫ ሊያመራ ይችላል። ስለዚህ ለግለሰቡ ሁኔታ የሚስማማ ሐሳብ ለማንሳት ፈቃደኛ ሁን፤ ከተዘጋጀኸው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ የተለየ ቢሆንም እንኳ እንደአስፈላጊነቱ ለውጥ ማድረግህ ጠቃሚ ነው።