ተመላልሶ መጠየቅ
ምዕራፍ 9
ስሜትን መረዳት
መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።”—ሮም 12:15
ኢየሱስ ምን አድርጓል?
1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ማርቆስ 6:30-34ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦
ከኢየሱስ ምን እንማራለን?
2. የሰዎችን ስሜት ለመረዳት ጥረት ማድረጋችን መልእክታችንን ስለማድረስ ብቻ ሳይሆን ስለ ሰዎቹም እንድናስብ ያነሳሳናል።
ኢየሱስን ምሰል
3. በጥሞና አዳምጥ። ግለሰቡ ሐሳቡን እንዲገልጽ ፍቀድለት። አታቋርጠው፤ ስሜቱን፣ የሚያሳስበውን ነገር ወይም ተቃውሞውን ሲገልጽ ወዲያውኑ ውድቅ ለማድረግ አትቸኩል። ትኩረት ሰጥተህ የምታዳምጠው ከሆነ ለአመለካከቱ አክብሮት እንዳለህ መረዳት ይችላል።
4. ስለ ግለሰቡ አስብ። ካደረጋችሁት ውይይት ተነስተህ ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦
5. ስለሚያስፈልገው ነገር አወያየው። መጽሐፍ ቅዱስን ቢያጠና ለጥያቄዎቹ መልስ የሚያገኘው እንዴት እንደሆነ እንዲሁም ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ምን ምክሮች እንደሚያገኝ ሳትዘገይ አንሳለት።