በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ለምን አስፈለገ?

መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች መጻሕፍት ልዩ የሚያደርገው የአምላክን ፍቅራዊ መመሪያ የያዘ መሆኑ ነው። (1 ተሰሎንቄ 2:13) ከመጽሐፍ ቅዱስ የምታገኘውን ትምህርት በሥራ ካዋልከው በእጅጉ ትጠቀማለህ። ‘የበጎ ስጦታ ሁሉ የፍጹምም በረከት ሁሉ’ ምንጭ ለሆነው አምላክ ያለህ ፍቅር ከማደጉም በላይ ይበልጥ ወደ እርሱ ትቀርባለህ። (ያዕቆብ 1:17) እንዴት በጸሎት ወደ እርሱ እንደምትቀርብ ትማራለህ። ችግር በሚያጋጥምህ ጊዜ የአምላክን እርዳታ ማግኘት ትችላለህ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሰፈሩት የአቋም ደረጃዎች ጋር ተስማምተህ የምትኖር ከሆነ አምላክ የዘላለም ሕይወት ይሰጥሃል።—ሮሜ 6:23

መጽሐፍ ቅዱስ የእውቀት ብርሃን የሚፈነጥቅ እውነት ይዟል። የመጽሐፍ ቅዱስን እውቀት የሚቀስሙ ሰዎች በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አንቆ ከያዘው የተሳሳተ አመለካከት ነፃ ይወጣሉ። ለምሳሌ ያህል ስንሞት ምን እንደምንሆን እውነቱን ማወቃችን ሙታን ጉዳት ሊያደርሱብን ይችላሉ ከሚል ፍርሃት ወይም በሞት የተለዩን ዘመዶቻችንና ወዳጆቻችን እየተሠቃዩ ነው ከሚለው ፍርሃት ነፃ ያወጣናል። (ሕዝቅኤል 18:4) መጽሐፍ ቅዱስ ትንሣኤን አስመልክቶ የሚሰጠው ትምህርት የሚወዷቸውን በሞት ያጡ ሰዎችን ሁሉ ያጽናናል። (ዮሐንስ 11:25) ስለ ክፉ መላእክት እውነቱን ማወቃችን በመናፍስታዊ ድርጊቶች መካፈል አደገኛ መሆኑን የሚያስጠነቅቀን ሲሆን በምድር ላይ መከራ የበዛው ለምን እንደሆነ እንድንገነዘብ ይረዳናል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት አምላካዊ የሆኑ መሠረታዊ ሥርዓቶች አካላዊ ጥቅም በሚያስገኝ መንገድ እንድንመላለስ ያስተምሩናል። ለምሳሌ ያህል በልማዶቻችን “ልከኛ” መሆን ለጥሩ ጤንነት አስተዋጽኦ ያበረክታል። (1 ጢሞቴዎስ 3:2) ‘ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን በማንጻት’ ጤንነታችንን ከሚጎዱ ነገሮች እንቆጠባለን። (2 ቆሮንቶስ 7:1) በተጨማሪም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን የአምላክ ምክር ተግባራዊ ማድረጉ ትዳራችን ደስታ የሰፈነበት እንዲሆንና ለራሳችን ያለን አክብሮት ከፍ እንዲል ያደርጋል።—1 ቆሮንቶስ 6:18

የአምላክን ቃል ተግባራዊ የምታደርግ ከሆነ ደስተኛ ትሆናለህ። የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ውስጣዊ ሰላምና እርካታ እንድናገኝ ከመርዳቱም በላይ ተስፋችንን ያለመልምልናል። እንደ ርኅራኄ፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ደግነትና እምነት ያሉ ግሩም ባሕርያትን እንድናዳብር ይረዳናል። (ገላትያ 5:22, 23፤ ኤፌሶን 4:24, 32) እንደነዚህ ያሉ ባሕርያት የተሻልን ባል ወይም ሚስት የተሻልን አባት ወይም እናት እንዲሁም የተሻልን ልጅ እንድንሆን ይረዱናል።

የወደፊቱ ጊዜ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ብለህ አስበህ ታውቃለህ? የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በጊዜ ሂደት የት ላይ እንደምንገኝ ይጠቁሙናል። እነዚህ ትንቢቶች አሁን ዓለም በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መግለጽ ብቻ ሳይሆን አምላክ በቅርቡ ምድርን ወደ ገነትነት እንደሚለውጣት ያስረዳሉ።—ራእይ 21:3, 4

መጽሐፍ ቅዱስን ለማወቅ የሚያስችል እርዳታ

መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ሞክረህ ምናልባት ለመረዳት አስቸጋሪ ሆኖብህ ይሆናል። በአእምሮህ ውስጥ ለሚመላለሱ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዴት መልስ ማግኘት እንደምትችል ለማወቅ ተቸግረህ ይሆናል። ከሆነ እንደዚህ ያለ ችግር ያጋጠመህ አንተ ብቻ አይደለህም። ሁላችንም ብንሆን የአምላክን ቃል ለመረዳት እርዳታ ማግኘት ያስፈልገናል። ወደ 235 በሚያክሉ አገሮች ውስጥ የሚገኙት የይሖዋ ምሥክሮች በሚልዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች በነፃ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይሰጣሉ። አንተንም ለመርዳት ፈቃደኞች ናቸው።

ብዙውን ጊዜ መሠረታዊ ከሆኑ ትምህርቶች በመነሳት መጽሐፍ ቅዱስን ደረጃ በደረጃ ማጥናቱ የተሻለ ነው። (ዕብራውያን 6:1) በጥናቱ በገፋህ መጠን “ጠንካራ ምግብ” ይኸውም ጥልቅ እውነቶችን የመረዳት ችሎታ ይኖርሃል። (ዕብራውያን 5:14) የመጨረሻ ባለ ሥልጣን ተደርጎ የሚጠቀሰው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? እንደተባለው ብሮሹር ያሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎች የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ጥቅሶች ለማስተዋል እንድትችል ይረዱሃል።

መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት በየሳምንቱ የተወሰነ ጊዜ ለመመደብ ፈቃደኛ ነህ?

በአብዛኛው አንተን በሚያመችህ ጊዜና ቦታ መጽሐፍ ቅዱስን እንድታጠና ዝግጅት ሊደረግ ይችላል። ብዙ ሰዎች በራሳቸው ቤት ሌላ ሰው በግል መጽሐፍ ቅዱስን ያስጠናቸዋል። በስልክ የሚያጠኑ አንዳንድ ሰዎችም አሉ። የጥናቱ ፕሮግራም ብዙ ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ሆነው እንደሚማሩት ያለ ሳይሆን ትምህርት የመቅሰም አቅምህንና የትምህርት ደረጃህን ጨምሮ የግል ሁኔታዎችህን ግምት ውስጥ በማስገባት በግለሰብ ደረጃ የሚዘጋጅ ነው። ፈተና ስለሌለው የሚያስፈራህ ሁኔታ አይኖርም። ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችህ መልስ የምታገኝ ከመሆኑም በላይ ወደ አምላክ እንዴት መቅረብ እንደምትችል ትማራለህ።

እንደዚህ ላለው ጥናት ክፍያ አትጠየቅም። (ማቴዎስ 10:8) ለየትኛውም ሃይማኖት አባላት እንዲሁም የራሳቸው ሃይማኖት ባይኖራቸውም ስለ አምላክ ቃል ያላቸውን እውቀት የማሳደግ ልባዊ ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ያለ ክፍያ የሚሰጥ ትምህርት ነው።

በውይይቱ ላይ ማን መገኘት ይችላል? መላው ቤተሰብህ መገኘት ይችላል። ልትጋብዛቸው የምትፈልጋቸው ጓደኞች ካሉህ መገኘት ይችላሉ። ካልፈለግህ ደግሞ ውይይቱን ከአንተ ጋር ብቻ ማድረግ ይቻላል።

ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት በየሳምንቱ አንድ ሰዓት መድበዋል። መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት በየሳምንቱ ከዚህ የበለጠ ወይም ያነሰ ሰዓት መመደብ የምትችል ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች አንተን ለመርዳት ፕሮግራማቸውን ያስተካክላሉ።

መጽሐፍ ቅዱስን እንድትማር የቀረበ ግብዣ

ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር እንድትገናኝ እንጋብዝሃለን። ይህን ማድረግ የምትችልበት አንደኛው መንገድ ቀጥሎ ወዳለው አድራሻ በመጻፍ ነው። ከዚያም አንድ ሰው ያለ ክፍያ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያስጠናህ ዝግጅት ይደረጋል።

አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።

በየትኛው ቋንቋ እንደምትፈልግ ጥቀስ

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

ሌላ መግለጫ ካልተሰጠ በስተቀር የተጠቀሱት ጥቅሶች የተወሰዱት በ1954 ከተተረጐመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።