በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 5

ታላቁ የጥፋት ውኃ—አምላክን የሰሙት እነማን ነበሩ? ያልሰሙትስ?

ታላቁ የጥፋት ውኃ—አምላክን የሰሙት እነማን ነበሩ? ያልሰሙትስ?

በኖኅ ዘመን ይኖሩ የነበሩት አብዛኞቹ ሰዎች ክፉ ድርጊት ይፈጽሙ ነበር። ዘፍጥረት 6:5

አዳምና ሔዋን ልጆች ወለዱ፣ ሰዎችም በምድር ላይ እየበዙ ሄዱ። ከጊዜ በኋላ የተወሰኑ መላእክት ዓምፀው ከሰይጣን ጎን ተሰለፉ።

እነዚህ መላእክት የሰው አካል ለብሰው ወደ ምድር በመምጣት የሰውን ሴቶች ልጆች አገቡ። ሴቶቹም ከሰው የላቀ ኃይል ያላቸውን ጨካኝና ብርቱ የሆኑ ልጆች ወለዱ።

ዓለም ክፉ ድርጊት በሚፈጽሙ ሰዎች ተሞላች። መጽሐፍ ቅዱስ “የሰው ልጅ ክፋት በምድር ላይ እንደበዛና የልቡም ሐሳብ ሁሉ ምንጊዜም ወደ መጥፎ ብቻ ያዘነበለ” እንደነበር ይገልጻል።

ኖኅ አምላክ ያዘዘውን በመስማት መርከብ ሠርቷል። ዘፍጥረት 6:13, 14, 18, 19, 22

ኖኅ ጥሩ ሰው ነበር። ይሖዋ ታላቅ የጥፋት ውኃ በማምጣት ክፉ ሰዎችን ሊያጠፋ እንደሆነ ለኖኅ ነገረው።

በተጨማሪም አምላክ ትልቅ መርከብ እንዲሠራ እንዲሁም ቤተሰቡንና ሁሉንም ዓይነት እንስሳት ወደ መርከቡ እንዲያስገባ ነገረው።

ኖኅ የጥፋት ውኃ ሊመጣ እንደሆነ በመናገር ሰዎችን ቢያስጠነቅቅም እነሱ ግን አልሰሙትም። እንዲያውም አንዳንዶቹ ሳቁበት፤ ሌሎቹ ደግሞ ጠሉት።

ኖኅ መርከቡን ሠርቶ ሲያጠናቅቅ እንስሳቱን ወደ ውስጥ አስገባቸው።