በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 1

አምላክን መስማት የምንችለው እንዴት ነው?

አምላክን መስማት የምንችለው እንዴት ነው?

አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ያናግረናል። 2 ጢሞቴዎስ 3:16

እውነተኛው አምላክ ሰዎችን በመጠቀም ሐሳቡ በአንድ ቅዱስ መጽሐፍ ላይ እንዲጻፍ አድርጓል። ይህ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። መጽሐፉ በጣም አስፈላጊ የሆነ መረጃ የያዘ ነው፤ አምላክም ይህን መረጃ እንድታውቀው ይፈልጋል።

አምላክ ለእኛ ከሁሉ የተሻለው ነገር ምን እንደሆነ የሚያውቅ ከመሆኑም ሌላ የጥበብ ሁሉ ምንጭ ነው። አንተም እሱን በመስማት ጥበበኛ መሆን ትችላለህ።—ምሳሌ 1:5

አምላክ በምድር ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያነቡ ይፈልጋል። በአሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቋንቋዎች ይገኛል።

አምላክን መስማት የምትፈልግ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና በውስጡ ያለውን ሐሳብ መረዳት ይኖርብሃል።

በሁሉም ቦታ ያሉ ሰዎች እየሰሙ ነው። ማቴዎስ 28:19

የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን መማር እንድትችል ሊረዱህ ይችላሉ።

ስለ አምላክ የሚገልጸውን እውነት በምድር ዙሪያ ያስተምራሉ።

ይህን ትምህርት ያለምንም ክፍያ መማር ትችላለህ። በአካባቢህ ወደሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች የስብሰባ አዳራሽ በመሄድ ስለ አምላክ መማር ትችላለህ።