“እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናል”
ምዕራፍ 19
“እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናል”
1, 2. (ሀ) ዘካርያስ 8:23 በጊዜያችን ምን ይሆናል ብሎ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር? (ለ) እዚህ ላይ የተጠቀሰው አምላክ ማን ነው? ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የግል ስሙን የሚያጎላው እንዴት ነው?
“እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ።” ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ ሰዎች በጊዜያችን እንደዚህ ብለው እንደሚናገሩ መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ ገልጿል። (ዘካርያስ 8:23) የዘካርያስ ትንቢት እዚህ ላይ የጠቀሰው አምላክ ማን ነው? መልሱ ምንም አያጠራጥርም። ከሌሎች መጻሕፍት ጋር ሲወዳደር አነስተኛ በሆነው በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ብቻ የግል ስሙ 135 ጊዜ ይገኛል። እርሱም ይሖዋ ነው!
2 ይሖዋ ስለሚለው የግል ስሙ እርሱ ራሱ እንዲህ ብሏል:- “ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፣ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።” (ዘጸአት 3:15) ይህ ስም በተሟላው የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 7,000 ጊዜ ያህል መገኘቱ ስሙ ምን ያህል ትልቅ ቦታ እንዳለው ያረጋግጣል። ጌታ እና አምላክ የሚሉትና የመሳሰሉት የማዕረግ ስሞች አንድ ላይ ተዳምረው ይህን ያህል ጊዜ አልተጠቀሱም። በትንቢቱ ላይ እንደተገለጸው በእነዚህ ‘የመጨረሻ ቀኖች’ ይህ ስም ከአንድ ቡድን ጋር በጐላ ሁኔታ ተያይዞ ይታያል።
“ከእናንተ ጋር እንሂድ”
3. በዘካርያስ 8:20–23 ላይ አስቀድሞ እንደተገለጸው (ሀ) ይሖዋን የሚፈልጉት እነማን ናቸው? (ለ) ከእነማንስ ጋር ይቀላቀላሉ?
3 ይህን በሚመለከት ነቢዩ ዘካርያስ በጥንቷ ኢየሩሳሌም የይሖዋ ቤተ መቅደስ እንደገና በሚሠራበት ጊዜ በመንፈስ አነሳሽነት የሚከተለውን ጽፎአል:- “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:- በብዙ ከተሞች የሚቀመጡ አሕዛብ ገና ዘካርያስ 8:20–23
ይመጣሉ፤ በአንዲት ከተማ የሚኖሩ ሰዎች:- እግዚአብሔርን እንለምን ዘንድ፣ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን እንፈልግ ዘንድ ኑ እንሂድ፤ እኔም እሄዳለሁ እያሉ ወደ ሌላ ከተማ ይሄዳሉ። ብዙ ወገኖችና ኃይለኞች አሕዛብ በኢየሩሳሌም የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ፣ እግዚአብሔርንም ይለምኑ ዘንድ ይመጣሉ የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:- በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው:- እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።” —4. ይህ ትንቢት ለአይሁድ ሃይማኖትም ሆነ ለሕዝበ ክርስትና የማይሠራው ለምንድን ነው?
4 ይህ ትንቢት ከዘሩባቤል ጊዜ ጀምሮ፣ እንደገና ከተሠራው የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ያገኘው ውስን ፍጻሜ በዘመናችን በላቀ መንገድ የሚፈጸመውን የሚያመለክት ነበር። ግን ከየትኛው ሕዝብ ጋር በተያያዘ መንገድ መፈጸም ይኖርበታል? ‘ይሖዋን ፈልገው ለማግኘት’ የሚጥሩ ሰዎች ባሕላዊ አምልኮታቸውን ሙጥኝ ብለው እንደያዙት ሥጋዊ አይሁዶች ወዳሉ፣ በአጉል አስተሳሰብ የተነሳ የአምላክን ስም ለመጥራትም እንኳ እምቢ ወዳሉ ሰዎች ቢሄዱ ምክንያታዊ አይሆንም። የአይሁዶችን በመለኮታዊ ስም ያለመጠቀም ልማድ ወደተከተለችው ሕዝበ ክርስትናም ቢሄዱ ምክንያታዊ አይሆንም። በጊዜያችን ሰዎች ይሖዋን ለማምለክ የሚሄዱት ወደ ምድራዊቷ ኢየሩሳሌም አይደለም። ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረው አምላክ በዚያች ኢየሩሳሌም ውስጥ ይገኝ የነበረውን ቤተ መቅደስ ትቶታል፤ ቤተ መቅደሱም እስከ ጊዜያችን ድረስ ዳግም እንዳይሠራ ሆኖ በ70 እዘአ ተደምስሷል። ምክንያታዊ የሆነ ማንኛውም ሰው አምላክ ክርስትናን ካልተቀበሉት እስራኤላውያን ጋር እንዳልሆነ ይህ ሁኔታ ይጠቁምለታል። — ማቴዎስ 23:37, 38፤ ከ1 ነገሥት 9:8, 9 ጋር አወዳድር።
5. ቅዱሳን ጽሑፎች (ሀ) በዛሬው ጊዜ ይሖዋን የምትወክለዋን “ኢየሩሳሌም” (ለ) በዘካርያስ ትንቢት የተጠቀሰውን “አይሁዳዊ ሰው” ማንነት ለይተን እንድናውቅ የሚረዱን እንዴት ነው?
5 ዛሬ ይሖዋን የምትወክለው “ኢየሩሳሌም” በዕብራውያን ላይ ‘የሕያው እግዚአብሔር ከተማ . . . ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም’ ተብላ ተገልጻለች። የጥንቷ ኢየሩሳሌም ለይሖዋ አገዛዝ በዓይን የምትታይ ዓርማ እንደነበረች ሁሉ፣ “ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም”ም ኢየሱስ ክርስቶስ በአሕዛብ ዘመናት መጨረሻ ማለትም በ1914 ንጉሥ ሆኖ ዙፋን ላይ የተቀመጠባት የአምላክ መሲሐዊት መንግሥት ናት። ( 12:221 ዜና መዋዕል 29:23፤ ሉቃስ 21:24) ይህች መንግሥት የሰው ልጆች ብቸኛና እውነተኛ ተስፋ መሆኗን በታማኝነት የሚያውጁላት ተወካዮች በዚህ ምድር ላይ አሏት። መንግሥቲቱ በ1914 መቋቋሟን በመጀመሪያ ያወጁት የ“ታናሹ መንጋ” ቀሪዎች ነበሩ። በመንፈሳዊ አነጋገር ‘የአምላክ እስራኤል’ እነርሱ ናቸው። ዘካርያስ ትንቢት የተናገረላቸው አይሁድ እነርሱ ናቸው። (ሉቃስ 12:32፤ ገላትያ 6:16፤ ሮሜ 2:28, 29) ለአምላክ ባላቸው ፍቅር ተገፋፍተውና ይሖዋ እውነተኛና ሁሉን የሚችል አምላክ መሆኑን ለማሳወቅ ያለባቸውን ኃላፊነት በአድናቆት በመቀበል ከ1931 ጀምሮ የይሖዋ ምሥክሮች በሚል ስም ይጠራሉ። — ኢሳይያስ 43:10–12
ተለይተው የሚታወቁት እንዴት ነው?
6. (ሀ) ዛሬ አምላክ በመካከላቸው አለ ሊባልላቸው የሚችሉት ሰዎች እነማን ስለመሆናቸው በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩትን ሰዎች ያሳመናቸው ምንድን ነው? (ነጥቦቹን አንድ በአንድ ተናገር፤ ጥቅሶቹን አንብብ።) (ለ) አንተን ከሁሉ በላይ የነኩህ የትኞቹ ነጥቦች ናቸው?
6 እነዚህ መንፈሳዊ አይሁዳውያን የይሖዋ ምሥክርነት ግዴታቸውን ሳያጓድሉ በመፈጸማቸው በምድር ዙሪያ በሚልዮን የሚቆጠሩ ቅን ሰዎች ‘ይሖዋን ፈልገው ሊያገኙ’ ችለዋል። እነዚህ ቅን ሰዎች ይሖዋ በእርግጥ ስሙን ከተሸከመው ከዚህ ሕዝብ ጋር እንዳለ ለማወቅ ችለዋል። ለዚህ ምን የሚያሳምናቸው ነገር አግኝተዋል? ብዙ ነገሮች አሉ፤ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው:-
(1) የይሖዋ ምሥክሮች የሚያምኑባቸው ነገሮች ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ናቸው። የተመሠረቱትም በተነጣጠሉ ጥቅሶች ላይ ሳይሆን በጠቅላላው የአምላክ ቃል ላይ ነው። የይሖዋ ምሥክሮች ከራሳቸው አመንጭተው ከማስተማር ከዮሐንስ 7:16–18 ጋር አወዳድር።)
ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን በመጥቀስ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ። ይሖዋ እንዲናገር በመፍቀድ ከፍ ያለ ክብር ይሰጡታል። ((2) አምላክ ራሱ ከአሕዛብ “ለስሙ የሚሆንን ወገን” የሚወስድበት ጊዜ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ተናግሮ ነበር። (ሥራ 15:14) እነርሱ ራሳቸው ስሙን እየጠሩ ይጠቀሙበታል፤ በመላው ምድርም ስሙን ለማሳወቅ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። (ኢሳይያስ 12:4, 5) በዓለም ዙሪያ ይሖዋ ከሚለው የአምላክ የግል ስም ጋር የጎላ ትስስር ያላቸው የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው።
(3) የይሖዋ ምሥክሮች የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ አላቸው። ከቅዱሳን ጽሑፎች የሚቀስሙት ትምህርትና ይህ ትምህርት ለሕይወት ባላቸው አመለካከት ላይ በሚያስከትለው ውጤት ምክንያት ከአጠቃላይ ዓለም ጋር ሲነፃፀሩ ደስተኛ ሕዝብ ሆነዋል። የአገልጋዮቹ ሁኔታ እንደዚህ እንደሚሆን ይሖዋ ተናግሮ ነበር። (ኢሳይያስ 65:13, 14፤ ከማቴዎስ 4:4 ጋር አወዳድር።)
(4) የይሖዋ ምሥክሮች የሥነ ምግባር ደረጃቸውን ለመደንገግና በዕለታዊ የኑሮ ጉዳዮች፣ ይኸውም በቤተሰብ፣ በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ቤት፣ በመዝናኛ ምርጫ፣ ሊርቋቸው የሚገቡ ድርጊቶችን ለመለየት፣ እንዲሁም ጊዜና ጉልበት ሊያጠፉላቸው የሚገቡትን ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ለመወሰን የአምላክን ቃል መመዘኛ አድርገው ይጠቀሙበታል። እንደዚህ ለሚያደርጉ ሁሉ ‘መንገዳቸውን የተቃና እንደሚያደርግላቸው’ ይሖዋ ቃል ገብቷል። (ምሳሌ 3:5, 6)
(5) የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች አመራር በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረውን የአምላክ ጉባኤ አሠራር የተከተለ ነው። በዚያን ጊዜ ሽማግሌዎቹ ከሌላው ልቀው የሚታዩ የቀሳውስት ክፍል በመሆን ፋንታ ለመንጋው ምሳሌ የሚሆኑና ለአምላክ መንግሥት በጋራ የሚደክሙ የሥራ ባልደረቦች ነበሩ። (1 ጴጥሮስ 5:2, 3፤ 2 ቆሮንቶስ 1:24)
(6) የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ አይገቡም። ከዚህ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ ለእውነተኛ ክርስቲያኖች የመደበላቸውን ሥራ፣ ይኸውም መጨረሻው ከመምጣቱ በፊት የአምላክን መንግሥት ምሥራች በዓለም ሁሉ የማወጁን ሥራ ማቴዎስ 24:14፤ ከዮሐንስ 17:16ና ከ18:36 ጋር አወዳድር።)
ያከናውናሉ። ((7) የይሖዋ ምሥክሮች እርስ በርሳቸው በእውነት ይዋደዳሉ። ኢየሱስም እውነተኛ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደሚያደርጉ ተናግሮ ነበር። የቆዳ ቀለም፣ የጎሣ ልዩነት፣ የኢኮኖሚ ሁኔታዎች፣ ብሔር፣ ቋንቋና የመሳሰሉት ነገሮች እንዲናናቁ አያደርጓቸውም። ሰብዓዊ አለፍጽምና ቢኖርም ዓለም አቀፍ ወንድማማች በመሆን እርስ በርስ በእውነት ተሳስረዋል። ለዚህ ሁሉ መመስገን የሚገባው አምላክ ነው። (ዮሐንስ 13:35፤ ከሥራ 10:34, 35 ጋር አወዳድር።)
(8) እንደ መጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ሁሉ በዚህ ዘመን ያሉ የይሖዋ ምሥክሮችም ስደት ቢደርስባቸውም አምላክን ማገልገላቸውን ቀጥለዋል። እምነታቸውን በአምላክ ላይ በመጣል በተቃዋሚዎች ላይ የበቀል እርምጃ ከመውሰድ ታቅበዋል። እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ ዛሬም አምላክ ከአገልጋዮቹ ጎን በመቆም ከአሳዳጆቹ እጅ አስጥሏቸዋል። (ኤርምያስ 1:8፤ ኢሳይያስ 54:17)
7. (ሀ) ‘አሥሩ ሰዎች’ እነማን ናቸው? (ለ) ይሖዋ በእርግጥ አምላካቸው እንደሆነ የሚያረጋግጡት እንዴት ነው?
7 አስቀድሞ እንደተነገረው፣ “ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች” የመንግሥቱ ወራሽ ለሆኑት ቀሪዎች “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከአናንተ ጋር እንሂድ” በማለት በሙሉ እምነት ለመናገር ከሚያበቋቸው ምክንያቶች ጥቂቶቹ እነዚህ ናቸው። (ዘካርያስ 8:23) ቅዱሳን ጽሑፎች “አሥር” ቁጥርን የምድራዊ ጉዳዮችን ሙላት ለማመልከት ይጠቀሙበታል። ስለዚህ “አሥር ሰዎች” ሲል በአሁኑ ጊዜ በመንፈስ ከተቀቡት የክርስቶስ “ወንድሞች” ጋር በንጹሕ አምልኮ የሚተባበሩትን ሁሉ ያመለክታል። ከቅቡዓኑ ጋር በስብሰባዎቻቸው ላይ መገኘት ብቻ ሳይሆን ከእውነተኛው አምላካቸው ከይሖዋ ጐን የቆሙ መሆናቸውን በግልጽ ያሳውቃሉ። በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሕይወታቸውን ለይሖዋ ይወስናሉ፤ ይህንንም በውኃ ጥምቀት ያሳያሉ። በዚህ መንገድ ‘ወደ ይሖዋ ለመጠጋት’ የሚፈልጉ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። ከዚያም ምሥክሮቹ በምድር ዙሪያ በሚያከናውኑት ሥራ በደስታ ይሳተፋሉ። — ዘካርያስ 2:11፤ ኢሳይያስ 61:5, 6
ጥሩ አብነት የሆኑ ሰዎች
8. (ሀ) የሳባ ንግሥት ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ያነሳሳት ምንድን ነው? (ለ) እዚያ በደረሰች ጊዜ ምን አደረገች? ከምንስ ውጤት ጋር? (ሐ) በዘመናችን እንደ እርሷ ያሉ ሰዎች የተገኙት እንዴት ነው? (መዝሙር 2:10–12 አዓት )
8 ይህን እርምጃ ከሚወስዱት መካከል አንዳንዶቹ በሰሎሞን ዘመን የነበረችውን የሳባን ንግሥት ይመስላሉ። ሩቅ አገር ሆና ‘ከይሖዋ ስም ጋር በማያያዝ የሰሎሞንን ዝና ትሰማ ነበር።’ ከሰሎሞን ጋር በግል ተነጋግራ አታውቅም፤ በኢየሩሳሌም ወደነበረው የይሖዋ ቤተ መቅደስም ከዚያ በፊት አልሄደችም። የምትሰማው ነገር ሁሉ ልክ እንደሚወራው ስለመሆኑ ጥርጣሬ ነበራት። ይሁን እንጂ 2,250 ኪሎ ሜትር የሚያህል ርቀት በግመል ተጉዛ እውነቱን ለማወቅ ጥረት አደረገች። ‘አስቸጋሪ ለሆኑት ጥያቄዎቿ’ ሁሉ መልስ አገኘች። እንዲያውም “እኩሌታውን አልነገሩኝም ነበር” ብላ በመደነቅ ተናግራለች። ይሖዋ የሚያመልኩትን ሰዎች ይወዳል ብላ ከመደምደም በስተቀር ሌላ ምንም ለማለት አልቻለችም። (1 ነገሥት 10:1–9) በዓለም ታዋቂ የነበሩ አንዳንድ ሰዎችም በዛሬው ጊዜ የእርሷን ምሳሌ ተከትለዋል። ዝቅተኛ ኑሮ ያላቸው ብዙ ሰዎችም እንደዚሁ አድርገዋል። እነዚህ ሁሉ የይሖዋ ምሥክሮች ከታላቁ ሰሎሞን ከኢየሱስ ክርስቶስ በስተቀር እንደ ንጉሣቸው አድርገው ማንንም ሰው እንደማይመለከቱ ተጨባጭ ማስረጃዎችን ተመለክተዋል። የአምላክን ቃል በመንተራስ የሚቀርቡላቸው መልሶች አእምሯቸውንና ልባቸውን ያረካሉ። ስለሆነም አብረዋቸው ይሖዋን ለመባረክ ይነሳሳሉ። — ከሉቃስ 11:31 ጋር አወዳድር።
9. (ሀ) የረዓብ አቋም ከሳባ ንግሥት አቋም የሚለየው በምን መንገድ ነው? (ለ) የረዓብንና የቤተሶቿን ሕይወት ወደማትረፍ ያደረሱትን ሁኔታዎች በሚመለከት ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ምንድን ነው? (ሐ) በዛሬው ጊዜ እንደ ረዓብ ያሉትን ሰዎች ለይቶ የሚያሳውቃቸው ምንድን ነው?
9 ሌሎች ሰዎችም አስቀድማ በሰማችው መሠረት የእስራኤል አምላክ “በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ” ነው ብላ እንዳመነችው እንደ ኢያሪኮዋ ረዓብ ናቸው። (ኢያሱ 2:11) የእስራኤል ሰላዮች ወደ ምድሪቱ በገቡ ጊዜ በደንብ ተቀብላ ደበቀቻቸው፤ በሕይወቷ ቆርጣም ከመገደል አዳነቻቸው። እምነት ነበራት፤ ይህንንም ከይሖዋ ሕዝብ ጎን በመቆም በሥራ አረጋግጣለች። (ዕብራውያን 11:31፤ ያዕቆብ 2:25) ሕይወቷን ለማትረፍ የተሰጣትን መመሪያ በጥንቃቄ ተከትላለች። ደግሞም ረዓብ ለአባቷና ለእናቷ እንዲሁም ለወንድሞቿና ለእህቶቿ ፍቅራዊ አሳቢነት አሳይታለች። ለመዳን የሚያስፈልጉትን ብቃቶች ለመከተል የሚፈቅዱ ከሆነ የሚድኑበትን መንገድ ከፈተችላቸው። (ኢያሱ 2:12, 13, 18, 19) ከዚህም የተነሳ ኢያሪኮና በኣልን አምላኪ የሆኑት ነዋሪዎቿ ሲደመሰሱ እርሷና ቤተሰቧ ተርፈዋል። (ኢያሱ 6:22, 23) ይህ ለዘመናችን ከፍተኛ ቁምነገር ይዟል። ይሖዋ እንደ ረዓብ ያሉ ሰዎችን ከጥፋት እንደሚያድን ያሳያል። ታዲያ እርሷን የሚመስሉ መሆናቸውን የሚያሳየው ምንድን ነው? በይሖዋ ያምናሉ፤ ከመንፈሳዊ እስራኤል አባሎች ጋር ይሰለፋሉ፤ በዚህ መገናኛ መሥመር በኩል የሚመጣላቸውን መመሪያ ይከተላሉ፤ የቅርብ ቤተሰቦቻቸውንና ሌሎች ዘመዶቻቸውንም የእነርሱን ምሳሌ መከተሉ ብልህነት እንደሆነ ለማሳመን ከልብ ይጥራሉ።
10. (ሀ) የዘካርያስ ትንቢት እንደገለጸው ሰዎች ወደ ይሖዋ ምሥክሮች እንዲመጡ የሚስባቸው ዋናው ነገር ምንድን ነው? (ለ) ልባችን ለይሖዋ ባለን ፍቅር የተሞላ መሆኑን በዝንባሌያችንና በድርጊታችን ልናሳይ የምንችለው እንዴት ነው?
10 እርግጥ፣ ከየብሔሩ ብዙ ሰዎች ወደ ይሖዋ ምሥክሮች እንዲመጡ የሚማርካቸው ዋናው መስሕብ ይሖዋ አምላክ ራሱ ነው። ቃሉ ይማርካቸዋል። አገልጋዮቹ በሕይወታቸው የሚያፈሯቸው የመንፈስ ፍሬዎችም የሚጋብዙ ናቸው። ባሕርያቱንና ከሰው ልጆች ጋር ባለው ግንኙነት ያደረጋቸውን ነገሮች ሲያውቁም ሰይጣንና እምነተቢስ የሆኑ የሰው ልጆች በአምላክ ስም ላይ የከመሩትን ስድብ አምላክ የሚያስወግድበትን ጊዜ በናፍቆት ይጠብቃሉ። እነርሱ ራሳቸው ጉዳዮቻቸውን አምላካቸውን በሚያስደስትና ሌሎችም እርሱን እንዲያከብሩ በሚያነሳሳ መንገድ ለማከናወን ይጥራሉ። (1 ጴጥሮስ 2:12) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ያስተማራቸውን በመከተል “በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን” ብለው በሙሉ ልባቸው ይጸልያሉ። (ማቴዎስ 6:9, 10) “ለስሙ [ለይሖዋ ስም] የሚሆን ወገን” ለመሆናቸው የማያሳስት ማስረጃ ከሚታይባቸው ሰዎች ጐን ተሰልፈው ለአምላክ ቅዱስ አገልግሎት በማቅረብ ከጸሎታቸው ጋር የሚስማማ ነገር ያደርጋሉ።
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]