“ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም”
ምዕራፍ 10
“ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም”
1. በምግብ ረገድ በዓለም ላይ የወደቀው ስጋት ምን ያህል ከባድ ነው?
ዛሬ ዓለምን ካጋጠሟት ዐበይት ችግሮች አንዱ ምግብን የሚመለከት ነው። የዋጋ መናር ለብዙዎች ችግር ፈጥሮባቸዋል። ሌሎች ደግሞ ብዙ ሕዝብ የሚረፈርፍ ችጋር ተጋርጦባቸዋል። በየዓመቱ 40 ሚልዮን ሰዎች፣ በአንዳንድ ዓመታትም እስከ 50 ሚልዮን የሚደርሱ ሰዎች፣ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ባለማግኘት እየሞቱ መሆናቸው በቅርቡ ተዘግቧል። ይህን ቁጥር አሥር ጊዜ የሚያጥፉ ሌሎች ደግሞ በተመጣጠነ ምግብ እጦት በጽኑ ይሠቃያሉ። አንዳንድ አገሮች ሊመገቡት ከሚችሉት በላይ እህል ቢያመርቱም የፖለቲካ ተቀናቃኝነትና የንግድ ስግብግብነት ተራፊው ምርት በጣም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንዳይደርስ ጋሬጣ ሆነዋል። — ከራእይ 6:5, 6 ጋር አወዳድር።
2. የተትረፈረፈ እህል በሚመረትባቸው አገሮችም ውስጥ ሁኔታው አሳሳቢ የሆነው ለምንድን ነው?
2 የተትረፈረፈ ምርት አላቸው የሚባሉት አገሮችም እንኳን ስለ ወደፊቱ ጊዜ ይሰጋሉ። ለምን? የዘመኑ የእርሻ ዘዴ በነዳጅ ዘይት ላይ የተመካ ነው። በዓለም ያለው ነዳጅም ሊሟጠጥ የማይችል አይደለም። በፋብሪካ የተመረቱ ማዳበሪያዎችን ከመጠን በላይ መጠቀሙም በመሬት ውስጥ ያለውን ውኃ በክሎታል። አዝርዕቶችን ለማዳን ተብሎ በገፍ የተረጨው የተባይ ማጥፊያም አፈሩን ለም ለማድረግ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ትላትሎችን እያጠፋቸው ነው። ሰው በሚደክምበት በየትኛውም መስክ ከባድ ችግሮች ያለማቋረጥ እየጨመሩ ሄደዋል። የኢንተርናሽናል ምሁራን መድረክ ፕሬዘዳንት የሆኑት ኦሬሊዮ ፔቺ ዓለም “በየቦታው እየተፈናጠረ ከሚያወድም ጥይት” ጋር ይመሳሰላል ብለዋል። የወደፊት ተስፋችንን እንደዚህ ዓይነት ታሪክ ባስመዘገበ ዓለም ላይ መጣሉ ትክክል ይሆናልን? — ኤርምያስ 10:23፤ ምሳሌ 14:12
3. ለሁሉም የሰው ልጆች የሚበቃ ምግብ እንደሚያቀርብ ዋስትና ለመስጠት የሚችለው ማን ነው? በዚህስ እንድትተማመን የሚያደርግህ ምንድን ነው?
መዝሙር 2:7, 8) ክርስቶስ ሁሉም የሰው ዘሮች ምድር ከምታፈራው ምርት እንደልብ እንዲያገኙ ለማድርግ ጥበቡም ችሎታውም ይኖረዋል። (መዝሙር 72:7, 8, 16፤ ቆላስይስ 1:15–17) አሁን ያለው ስግብግብ ሥርዓት ከተወገደ በኋላ ምድር ፍሬያማ ገነት እንድትሆን የሰውን ልጆች ጥረት እየተቆጣጠረ ፈር ያስይዘዋል።
3 በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከአምላክ ብቻ የሚገኘው እርዳታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን በአስተዋይነት አምነው ተቀብለዋል። የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢቶች መርምረው ይሖዋ አምላክ ሰማያዊ ልጁን፣ ክርስቶስን፣ በዙፋን ላይ እንዳስቀመጠውና ጠቅላላዋን ምድር ግዛቱ አድርጎ እንደሰጠው ተገንዝበዋል። (4. የዚህ ሥጋዊ አቅርቦት ተጠቃሚ ለመሆን አሁን ምን ማድረግ ይኖርብናል?
4 ይሁን እንጂ ከእርሱ አገዛዝ ዘላቂ ጥቅም ሊያገኙ የሚችሉት ሰው በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር የገባቸው፣ የመንፈሳዊ ነገሮችን ዋጋማነት የተገነዘቡና የአምላክን ፈቃድ በመማርና በማድረግ የመጠናከርን አስፈላጊነት ያስተዋሉ ብቻ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የዚህን አስፈላጊነት ደጋግሞ በመጥቀስ ያጎላዋል። (ዮሐንስ 4:34፤ 6:27፤ ኤርምያስ 15:16) ኢየሱስ “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል” ብሎ በተናገረ ጊዜ ይህን ጉዳይ አጠንክሮ ገልጾታል። (ማቴዎስ 4:4) ከአሁኑ ዓለም ፍጻሜ በሕይወት ለመትረፍ ዛሬ እንደዚህ ያለው መንፈሳዊ ምግብ ያስፈልገናል። እንዴት ልናገኘው እንደምንችልም ስለ ዮሴፍና ስለ ወንድሞቹ የሚተርከው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ በምሳሌ ያስረዳናል።
“ወደ ዮሴፍ ሂዱ”
5. ዮሴፍ ባሪያ ሆኖ ወደ ግብፅ ሊሄድ የቻለው እንዴት ነው?
5 የአብርሃም የልጅ ልጅ ተወላጅ የሆነው ዮሴፍ በሕይወት ውስጥ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አምላክ በሕልም አመልክቶት ነበር። በዚህ ምክንያትና አባቱ ለእርሱ ልዩ ፍቅር ስለነበረው የዮሴፍ ዘፍጥረት 37:3–11, 28
ግማሽ ወንድሞች ጠሉት። እርሱን ለመግደልም አሴሩ። በኋላ ግን ለባርነት ሸጡትና ወደ ግብፅ ተወሰደ። ታዲያ አምላክ ለዮሴፍ የነበረው ዓላማ እንዴት ይፈጸም ይሆን? —6. (ሀ) የፈርዖን ትኩረት እንዴት ወደ ዮሴፍ ሊዞር ቻለ? (ለ) ፈርዖንን ያስጨነቁት ሕልሞች ምን ነበሩ?
6 ዮሴፍ 30 ዓመት በሆነው ጊዜ ይሖዋ ለግብፁ ገዥ ለፈርዖን ሁለት አስጨናቂ ሕልሞችን አሳየው። በመጀመሪያው ሕልም ላይ “መልካቸው ያማረ ሥጋቸውም የወፈረ” ሰባት ላሞችን፤ እንዲሁም “መልካቸው የከፋ ሥጋቸውም የከሳ” ሌሎች ሰባት ላሞችን አየ። ከሲታሞቹ ላሞች ወፍራሞቹን ዋጧቸው። በሌላም ሕልም ላይ ፈርዖን በአንድ አገዳ ላይ የነበሩ “ያማሩና መልካም የሆኑ” ሰባት እሸቶችን፤ እንዲሁም “የሰለቱና በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ” ሌሎች ሰባት እሸቶችን አየ። የሰለቱት እሸቶች መልካሞቹን ዋጧቸው። የዚህ ሁሉ ፍቺ ምንድን ነው? ከግብፅ ጠቢባን እነዚህን ሕልሞች ሊፈታ የቻለ አንድም አልነበረም። ነገር ግን የፈርዖን ጠጅ አሳላፊ እስር ቤት ሳለ አብሮት እስረኛ የነበረው ዮሴፍ ሕልም በትክክል ተርጉሞ እንደነበረ ትዝ አለው። ፈርዖንም ዮሴፍን ወዲያው አስመጣው። — ዘፍጥረት 41:1–15
7. (ሀ) ዮሴፍ በግብፅ የእህል ጉዳይ አስተዳዳሪ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? (ለ) ረሃቡ እየጸና ሲሄድ ግብፃውያን ሕይወታቸውን ለማትረፍ ምን አደረጉ?
7 ዮሴፍ ለራሱ ምንም ክብር ባለመፈለግ “የፈርዖን ሕልም አንድ ነው፤ እውነተኛው አምላክ ሊያደርገው ያሰበውን ለፈርዖን ነግሮታል” በማለት ለፈርዖን አስታወቀ። (ዘፍጥረት 41:16, 25 አዓት) ዮሴፍ የሁለተኛው ሕልም ፍቺ ከመጀመሪያው ሕልም ጋር አንድ እንደሆነና የነገሩን እውነተኝነት ለማስረገጥ ሕልሙ የተደገመ መሆኑን ተናገረ። በግብፅ ሰባት የጥጋብ ዓመታት ካለፉ በኋላ ሰባት የረሃብ ዓመታት ሊመጡ ነው። ረሃብ የሚጠናባቸው ዓመታት ከመምጣታቸው በፊት የጥጋብ ዓመታት እያሉ እህል ለማከማቸት ጥሩ ችሎታ ያለውን ሰው እንዲሾም ዮሴፍ ፈርዖንን መከረው። አምላክ ራሱ ይህንን ለዮሴፍ እንደገለጸለት በመገንዘብ ፈርዖን ዮሴፍን የእህል ጉዳይ አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመው። ይህም ከፈርዖን ቀጥሎ ያለው ከፍተኛ ሥልጣን ነው። በቅድሚያ እንደተነገረው ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ እህል በገፍ የተመረተባቸው ሰባት ዓመታት መጡ። ዮሴፍም እጅግ ብዙ እህል አከማቸ። ከዚያ በኋላ የተተነበየለት ረሃብ አገሪቱን ማስጨነቅ ጀመረ። ሕዝቡ ፈርዖንን እህል እንዲሰጣቸው በለመኑት ጊዜ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፣ እርሱ ያላችሁንም ሁሉ አድርጉ” ይላቸው ነበር። ስለዚህ ዮሴፍ በመጀመሪያ በገንዘብ፣ ቀጥሎም በከብቶቻቸው ልዋጭ በመጨረሻም ራሳቸውንና መሬታቸውን እንዲሸጡ በማድረግ እህል ሰጣቸው። ሕይወታቸውን ለማትረፍ ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለፈርዖን አገልግሎት ለመስጠት ተገደዱ። — ዘፍጥረት 41:26–49, 53–56፤ 47:13–26
8. (ሀ) የሚበላ ነገር ለማግኘት የዮሴፍ ግማሽ ወንድሞች ምን ለማድረግ ተገደዱ? (ለ) ይህ ታሪክ ተመዝግቦ የቆየልን ለምንድን ነው?
8 ረሃቡ በግብፅ ዙሪያ የነበሩትንም አገሮች ነካ። ከጊዜ በኋላም የራሱ የዮሴፍ ግማሽ ወንድሞች ከከነዓን መጡ። ለባርነት ከሸጡት ከ20 ዓመት በላይ አልፎ ስለነበር አላወቁትም። በዮሴፍ ሕልሞች ላይ አስቀድሞ እንደተገለጸው በፊቱ ወድቀው ሰገዱለትና እህል እንዲሰጣቸው ለመኑት። (ዘፍጥረት 37:6, 7፤ 42:5–7) ዮሴፍ በብልሃት ሲፈትናቸው ለእርሱና ለአባታቸው የነበራቸውን አመለካከት እንደለወጡ አሳማኝ ማስረጃ ተመለከተ። በመጨረሻም ማንነቱን ገለጸላቸውና አምላክ እርሱን ከእነርሱ በፊት ወደ ግብፅ የላከው ‘ሕይወት ለማትረፍ’ እንደሆነ አስረዳቸው። በእርሱም ትእዛዝ አባታቸውንና ቤተሰባቸውን ወደ ግብፅ አመጡ። (ዘፍጥረት 45:1–11) ይህ ሁሉ የተመዘገበው ለጥቅማችን ነው፤ ትንቢታዊ ትርጉሙ በጊዜያችን የተፈጸሙ ሁኔታዎችን ይመለከታል። — ሮሜ 15:4
በአሁኑ ጊዜ ረሃባችንንና ጥማታችንን ማስታገሥ
9. (ሀ) ዛሬ በዓለም ላለው መንፈሳዊ ረሃብ ምክንያቱ ምንድን ነው? (ለ) ይህስ የሰውን ልጅ ችግሮች ካመጡት መሠረታዊ ነገሮች አንዱ የሆነው ለምንድን ነው?
9 ለሰው ዘር ችግሮች መንስዔ ከሆኑት መሠረታዊ ነገሮች አሞጽ 8:11) በመንፈሳዊ የተራቡ ሰዎች የሕይወት ትርጉም ምንድን ነው? ሰዎች ለምን ይሞታሉ? ስለ ወደፊቱ ጊዜ እርግጠኛ የሆነ ተስፋ ይኖራልን? ለሚሉት ትልልቅ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት በከንቱ ይዳክራሉ። እንደነዚህ ያሉት ሰዎች መንፈሳዊ ረሃብ ስላሳበዳቸው ምኞታቸውን ለማርካት በብልግናና በወንጀል ተግባሮች በመሳተፍ ብዙውን ጊዜ ራሳቸውንና ሌሎችን ጉዳት ላይ ይጥላሉ።
አንዱ መንፈሳዊ ረሃብ ነው። ይሖዋን ትተውታል፤ ስለዚህ እርሱም ቃሉን ማስተዋልን ነፈጋቸው። በዚህ ምክንያት “የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት” ያልሆነ ረሃብና ጥማት ደርሶባቸዋል። (10. (ሀ) የኢሳይያስ 65:13, 14 ትንቢት በሚፈጸምበት በአሁኑ ጊዜ በይሖዋ አገልጋዮች ላይ ምን ሁኔታዎች ይታያሉ? (ለ) የመንፈሳዊ ረሃብና የመንፈሳዊ ጥጋብ ዘመን መቼ ነው?
10 ከዚህ ተቃራኒ ግን ይሖዋ ከጐኑ ለቆሙት ታማኝ አገልጋዮቹ የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ ሰጥቷቸዋል። በመካከላቸውም እውነተኛ ፍቅር ይገኛል። በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው ቃሉ ውስጥ የሚገኙት አርኪ መንፈሳዊ እውነቶች እንዲገቧቸው ልቦናቸውን ከፍቶላቸዋል፤ ምሥክሮቹ ሆነው የሚያከናውኑት ሥራም ሰጥቷቸዋል። እነርሱም በመንፈሳዊ ለተራቡና ከአምላክ ጋር ለመዛመድ ለሚፈልጉ ሌሎች ሰዎች እነዚህን እውነቶች በደስታ ያካፍላሉ። (ኢሳይያስ 65:13, 14፤ ሉቃስ 6:21) በጥንቷ ግብፅ ሰባቱን የጥጋብ ዓመታት ሰባት የረሃብ ዓመታት ተከትለዋቸው ነበር። በዘመናችን ግን የመንፈሳዊ ረሃብና የመንፈሳዊ ጥጋብ ጊዜያት ጐን ለጐን ይጓዛሉ።
11. (ሀ) የፈርዖንና የዮሴፍ አምሳያዎች እነማን ናቸው? ለምንስ? (ለ) “እጅግ ብዙ ሰዎች” የወሰዱት እርምጃ በረሃብ የተጠቁት ግብፃውያን ከወሰዱት እርምጃ ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው?
11 በዛሬው ጊዜ ያለው ገዥ ፈርዖን አይደለም። በፈርዖን የተመሰለው የጽንፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዥ ይሖዋ አምላክ ነው። ይሖዋም ለኢየሱስ ክርስቶስ ከራሱ ቀጥሎ ያለውን ሥልጣን ሰጥቶታል። ኢየሱስ ታላቁ ዮሴፍ እንደመሆኑ መጠን ሕይወት አድን የሆነ መንፈሳዊ ምግብ የማከፋፈሉን ኃላፊነት ይሖዋ በእምነት አስረክቦታል። የዚህ ዓለም ሃይማኖታዊና ዓለማዊ ፍልስፍናዎች የሰውን ዘር ለሚሞረሙር መንፈሳዊ ረሃብ ዳርገውታል።
በሕይወት ቆመው ለመሄድ የሚችሉት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በመምጣትና እርሱ በሚሰጠው አመራር መንፈሳዊ ምግብ በማግኘት ብቻ ነው። በረሃብ በተጠቁት ግብፃውያን የተመሰሉ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንደዚያ እያደረጉ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለይሖዋ ለዘላለም ወስነዋል። በዚህ ምክንያት ከሚመጣው የመለኮታዊ ቁጣ ቀን በሕይወት ለመትረፍ ከታጩት እጅግ ብዙ ሰዎች መካከል ሆነዋል።12. (ሀ) በሰማይ የሚገኘው ኢየሱስ እዚህ ምድር ላይ ያለነው ሰዎች መንፈሳዊ ምግብ እንድናገኝ የሚያደርገው እንዴት ነው? (ለ) “ታማኝና ልባም ባሪያ” ማን ስለመሆኑ የሚያሳምንህ ነገር ምንድን ነው?
12 ታዲያ ኢየሱስ ያለው በሰማይ ነው። እዚህ ምድር ላይ የምንገኘውን ለመጥቀም መንፈሳዊ ምግብ የሚያድለን እንዴት ነው? ይህን ምግብ “በታማኝና ልባም ባሪያ” በኩል እንደሚያቀርብልን አስቀድሞ ገልጾ ነበር። (ማቴዎስ 24:45–47) ይህ “ባሪያ” የብዙ አባላት ጥምር ሲሆን ገና በምድር ላይ ያሉ በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖችን ጉባኤ ያመለክታል። (ከኢሳይያስ 43:10 ጋር አወዳድር።) የእነርሱ ቀሪዎች አሁንም በምድር ላይ ይገኛሉ። ይህ እውነተኛ የክርስቲያን ጉባኤ የትኛው እንደሆነ የሚያስተምራቸውንና የሚያደርጋቸውን ነገሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማስተያየት በቀላሉ ለይቶ ማወቅ ይቻላል። ኢየሱስ ያዘዘውን በሐቅ ያስተምራል። ስለዚህ አባላቱ በሙሉ የአምላክን መንግሥት ለሕዝብ ያውጃሉ እንጂ በዓለም ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ገብተው አይፈተፍቱም። በሕዝበ ክርስትና ልዩ ልዩ ኑፋቄዎች መካከል ተሰባጥረው የሚገኙ አይደሉም። ኢየሱስ እንዳለው አንድነት አላቸው። ጌታቸውን በመምሰል ሁሉም የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው። (ዮሐንስ 17:16, 20, 21ን፣ ማቴዎስ 24:14ን፣ 28:19, 20ንና ራእይ 1:5ን ተመልከት።) በመንፈሳዊ ምግብ የተትረፈረፉ ሲሆኑ ይህንን በረከት ለሌሎች ለማካፈል በጣም ፈቃደኞች ናቸው።
13. (ሀ) ብዙ ሰዎች እንደ አሥሩ የዮሴፍ ግማሽ ወንድሞች መሆናቸውን ያሳዩት በምን መንገዶች ነው? (ለ) ሁላችንም ክርስቶስ “በባሪያው” ክፍል ከሚያድለው መንፈሳዊ ምግብ እንዴት ልንጠቀም እንችላለን?
13 ብዙ ሰዎች እነዚህን ቅቡዓን ክርስቲያኖች ‘ከእኛ የምትበልጡ ይመስላችኋል? ትክክል የሆናችሁት እናንተ ብቻ ናችሁ ኤፌሶን 4:5፤ ሮሜ 12:5) በቅንነትና በትሕትና ያደረጉት ምርምር ወደዚህ ድርጅት መርቷቸዋል። በፊት የኢየሱስን ቅቡዓን ተከታዮች ያሳደዱት ወይም ለእነዚህ አሳዳጆች የሞራል ድጋፍ የሰጡት አሁን ግን እውነተኛ የልብ ለውጥ ያሳዩት እንደነዚህ ያሉት ሰዎች በአሥሩ የዮሴፍ ግማሽ ወንድሞች ተመስለዋል። (ዮሐንስ 13:20) ኢየሱስ ክርስቶስ ‘በታማኝ ባሪያው’ ክፍል የሚሰጠውን መንፈሳዊ ምግብ በአመስጋኝነት ይቀበላሉ። በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ላይ የሚብራሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ሲመገቡ፣ በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎች አዘውትረው ሲገኙና የአምላክን ፈቃድ ለመፈጸም በትጋት ሲሠሩ መንፈሳዊ ጥንካሬ ያገኛሉ። አንተስ ከእነዚህ ትሑታን አንዱ ነህን? — ዕብራውያን 10:23–25፤ ከዮሐንስ 4:34 ጋር አወዳድር።
እንዴ?’ እያሉ አፊዘውባቸዋል። ውሎ አድሮ ግን አንዳንዶቹ ይሖዋ በእርግጥ በምድር ላይ ምሥክሮች እንዳሉትና እነርሱም በእርግጥ ቃሉን እንደሚያውጁ በትሕትና ተቀብለዋል። የእውነተኛ ክርስቲያኖች ጉባኤ አንድ ብቻ እንደሆነና አባሎቹም የተባበሩ መሆን እንዳለባቸው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሳይ መሆኑን ተገንዘበዋል። (14. ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ድራማ በስተጀርባ ካሉት መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር በሚስማማ መንገድ የሚኖሩ ሁሉ ምን ዓይነት መንፈሳዊ ሁኔታዎችን አግኝተዋል?
14 በዚህ መንገድ ሕይወታቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለፈጣሪያቸው በፍቅር የሚያስረክቡ ሁሉ አስደሳች እርካታ ያገኛሉ። በመንፈሳዊ “ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፣ ከእንግዲህም ወዲህ አይጠሙም፣ . . . በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ [ኢየሱስ ክርስቶስ] እረኛቸው ይሆናልና፣ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋል።” — ራእይ 7:16, 17፤ ኢሳይያስ 25:6–9
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]