የአምላክን መንግሥት ምድራዊ ግዛት የሚወርሱትን አሁን በሕይወት የሚገኙ ሰዎች የሚያመለክቱ ትንቢታዊ አምሳያዎችና መግለጫዎች
የአምላክን መንግሥት ምድራዊ ግዛት የሚወርሱትን አሁን በሕይወት የሚገኙ ሰዎች የሚያመለክቱ ትንቢታዊ አምሳያዎችና መግለጫዎች
የሚከተሉት ቡድኖች ወይም ግለሰቦች ለእነርሱ ጥላ ነበሩ:-
(1) የኖኅ ወንዶች ልጆችና ሚስቶቻቸው (ዘፍጥረት 6–9)
(2) ሎጥና ሴቶች ልጆቹ (ዘፍጥረት 19)
(3) ስለ አድራጎታቸው የተጸጸቱት የዮሴፍ አሥር ወንድሞች (ዘፍጥረት 37, 42– 45)
(4) ራሳቸውን ለዮሴፍ የሸጡት በረሃብ የተጠቁ ግብፃውያን (ዘፍጥረት 41፤ 47:13–26)
(5) ከእስራኤል ጋር ግብፅን ለቆ የወጣው ድብልቅ ሕዝብ (ዘጸአት 12:38)
(6) ከሌዊ ነገድ ውጭ የነበሩት አሥራ ሁለት የእስራኤል ነገዶች በስርየት ቀን (ዘሌዋውያን 16፤ ማቴዎስ 19:28)
(7) በእስራኤል ውስጥ የሚቀመጡ መጻተኞች (ዘሌዋውያን 19:34)
(8) የሙሴ አማች፣ ኦባብ (ዘኁልቁ 10:29–32)
(10) ከእስራኤል ጋር ሰላም የፈጠሩት ገባዖናውያን (ኢያሱ 9, 10)
(11) የቄኔያዊው በሔቤር ሚስት ኢያዔል (መሳፍንት 4, 5)
(12) የንጉሥ ሳኦል ልጅ ዮናታን (1 ሳሙኤል 18፤ 23:16, 17)
(13) ከዳዊት ጎን ተሰልፈው የተዋጉት የባዕድ አገር ዜጎች (2 ሳሙኤል 15:18–22)
(14) የሳባ ንግሥት (1 ነገሥት 10)
(15) ንዕማን ከለምጽ ሲነፃ (2 ነገሥት 5)
(16) የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ (2 ነገሥት 10:15–28)
(17) ፊታቸውን ወደ ይሖዋ ቤተ መቅደስ አድርገው የጸለዩ ባዕዳን (2 ዜና መዋዕል 6:32, 33)
(18) ናታኒምና እስራኤላውያን ያልሆኑ የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች (ዕዝራ 2, 8)
(19) ሬካባውያን (ኤርምያስ 35)
(20) ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ (ኤርምያስ 38፤ 39:16–18)
(21) ንስሐ የገቡት የነነዌ ሰዎች (ዮናስ 3)
በተጨማሪም በትንቢታዊ ሁኔታ እንደሚከተለው ተገልጸዋል:-
(1) በአብርሃም ዘር በኩል ራሳቸውን የሚባርኩት የምድር ወገኖች (ዘፍጥረት 12:3፤ 22:18 አዓት )
(2) ከይሖዋ ሕዝብ ጋር ደስ የሚላቸው ብሔራት (ዘዳግም 32:43)
(3) ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉ ጻድቃን (መዝሙር 37:9, 29)
(4) የሙሽራይቱ ደናግል ባልንጀሮች (መዝሙር 45:14)
(5) ቅኖችና ነቀፋ የሌላቸው (ምሳሌ 2:21)
(6) በይሖዋ ቤት ትምህርት የሚሰጣቸውና በመንገዶቹ የሚሄዱት ብሔራት (ኢሳይያስ 2:2–4)
(7) ምልክቱን ለማግኘት ፍለጋ የሚያደርጉ ብሔራት (ኢሳይያስ 11:10)
(8) ከጨለማ የሚወጡ ብሔራት (ኢሳይያስ 49:6, 9, 10)
(9) በፊት የማይታወቅ የነበረ ብሔር (ኢሳይያስ 55:5)
(10) ይሖዋን የሚያገለግሉትና ስሙን የሚወዱ መጻተኞች (ኢሳይያስ 56:6)
(11) እንደ ደመና እየተመሙ፣ እንደ ርግቦች እየበረሩ የመጡት፣ ‘የባሕሩ በረከት’ “የአሕዛብ ብልጥግና” (ኢሳይያስ 60:5, 6, 8)
(12) የእስራኤልን በጎች የሚያሰማሩ መጻተኞች፣ አራሾችና ወይን ጠባቂዎች (ኢሳይያስ 61:5)
(13) የጸሐፊ ቀለም ቀንድ በያዘው ሰው ግምባራቸው ላይ ምልክት የተደረገባቸው (ሕዝቅኤል 9)
(14) የይሖዋን ስም የሚጠሩትና በአስፈሪው የይሖዋ ቀን ሕይወታቸው የሚጠበቅላቸው ሰዎች (ኢዩኤል 2:32)
(15) ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጡት ዕቃዎች (ሐጌ 2:7)
(16) ‘ወደ ይሖዋ የሚጠጉት’ ብሔራት (ዘካርያስ 2:11)
(17) የአንዱን አይሁዳዊ የልብስ ዘርፍ የሚይዙት አሥር ሰዎች (ዘካርያስ 8:23)
(18) ንጉሡ ሰላምን የሚናገራቸው ብሔራት (ዘካርያስ 9:10)
(19) ለንጉሡ ወንድሞች መልካም የሚያደርጉ “በጎች” (ማቴዎስ 25:31– 46)
(20) የተጸጸተው አባካኝ ልጅ (ሉቃስ 15:11–32)
(21) የመልካሙን እረኛ ድምፅ የሚሰሙት “ሌሎች በጎች” (ዮሐንስ 10:16)
(22) በኢየሱስ የሚያምኑትና ‘ፈጽሞ የማይሞቱት’ ሰዎች (ዮሐንስ 11:26)
(23) ለከንቱነት ባርያ ከመሆን ነፃ ወጥቶ የአምላክ ልጆች ወደሚያገኙት ክብራማ ነፃነት የሚደርሰው ፍጥረት (ሮሜ 8:20, 21)
(24) በአምላክ ልጅ በማመናቸው ምክንያት የዘላለም ሕይወት የሚያገኙት የዓለም ሰዎች (1 ዮሐንስ 2:2፤ ዮሐንስ 3:16, 36)
(25) በይሖዋ መቅደስ ቀንና ሌሊት የሚያገለግሉ “እጅግ ብዙ ሰዎች” (ራእይ 7:9–17)
(26) የሕይወትን ውኃ ለራሱ የሚጠጣና ሌሎችን “ና” የሚል (ራእይ 22:17)
ከዚህ በላይ የተገለጹት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ማብራሪያ የተሰጠባቸው ወይም የተጠቀሱት ብቻ ናቸው።