በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሥዕል ማውጫ

የሥዕል ማውጫ

በገጽ ቁጥር የተቀመጠ

  • የፊትና የኋላ ሽፋን ጳውሎስ፣ ጣቢታ፣ ጋልዮስ፣ ሉቃስ፣ የቤተ መቅደስ ጠባቂ ከሐዋርያት ጋር፣ ሰዱቃዊ፣ ጳውሎስ ታጅቦ ወደ ቂሳርያ ሲወሰድ፣ በዘመናችን የድምፅ ማጉያ በተገጠመለት መኪናና በሸክላ ማጫወቻ የስብከቱ ሥራ ሲከናወን።

  • ገጽ 1 ጳውሎስና ሉቃስ ወደ ሮም በምትሄድ ዕቃ ጫኝ መርከብ ላይ ተሳፍረው፤ ጳውሎስ በሰንሰለት ታስሯል።

  • ገጽ 2, 3 የበላይ አካል አባላት የሆኑት ወንድም ጆን ባርና ወንድም ቴዎዶር ጃራዝ የዓለም ካርታ እየተመለከቱ።

  • ገጽ 11 በገሊላ በሚገኝ አንድ ተራራ ላይ ኢየሱስ ለ11 ታማኝ ሐዋርያቱና ለሌሎች ተከታዮቹ ተልእኮ ሲሰጣቸው።

  • ገጽ 14 ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲያርግ። ሐዋርያቱ ቀና ብለው እየተመለከቱት።

  • ገጽ 20 በጴንጤቆስጤ ዕለት ደቀ መዛሙርቱ እንግዶችን በገዛ ቋንቋቸው ሲያናግሯቸው።

  • ገጽ 36 ሐዋርያቱ በንዴት በጦፈው በቀያፋ ፊት ቆመው። የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች ሐዋርያቱን ለማሰር የሳንሄድሪንን ትእዛዝ በተጠንቀቅ እየተጠባበቁ ነው።

  • ገጽ 44 ከታች፦ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አንድ የምሥራቅ ጀርመን ፍርድ ቤት የይሖዋ ምሥክሮችን የአሜሪካ ሰላዮች ናቸው ብሎ በሐሰት ሲፈርድባቸው።—ኖየ በርሊነር ኢሉስትኽየተ የተባለው መጽሔት የጥቅምት 3, 1950 እትም

  • ገጽ 46 እስጢፋኖስ ተከስሶ ሳንሄድሪን ፊት ቆሟል። ከእስጢፋኖስ ማዶ፣ ሀብታም የሆኑት ሰዱቃውያን፣ ከወዲህ በኩል ደግሞ አክራሪ የሆኑት ፈሪሳውያን አሉ።

  • ገጽ 54 ጴጥሮስ በአንድ አዲስ ደቀ መዝሙር ላይ እጁን ጭኖ፤ ስምዖን ደግሞ የሳንቲም ከረጢት ይዞ ቆሟል።

  • ገጽ 75 ጴጥሮስና የጉዞ ጓደኞቹ ወደ ቆርኔሌዎስ ቤት ሲገቡ። ቆርኔሌዎስ የመቶ አለቃ መሆኑን የሚያሳይ ልዩ ካባ በግራ ትከሻው ላይ ጣል አድርጓል።

  • ገጽ 83 ጴጥሮስ አንድ መልአክ እየመራው ከእስር ቤት ሲወጣ፤ ጴጥሮስ ታስሮ የነበረው በአንቶኒያ ግንብ ሳይሆን አይቀርም።

  • ገጽ 84 ከታች፦ በ1945 በሞንትሪያል፣ ኩዊቤክ አቅራቢያ የተነሳው የሕዝብ ዓመፅ።—ዊኬንድ ማጋዚን የተባለው መጽሔት የሐምሌ 1956 እትም

  • ገጽ 91 ጳውሎስንና በርናባስን ከጵስድያዋ አንጾኪያ ሲያስወጧቸው። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. መባቻ ላይ እንደተገነባ የሚገመተው የከተማዋ አዲሱ የውኃ ማስተላለፊያ ግንብ ከበስተጀርባ ይታያል።

  • ገጽ 94 ጳውሎስና በርናባስ በልስጥራ ለየት ያለ ክብር እንዳይሰጣቸው ሲከላከሉ። በአደባባይ መሥዋዕት በሚቀርብባቸው ወቅቶች በአብዛኛው አካባቢው እንዲያሸበርቅ ይደረጋል፤ ሙዚቃው ስለሚደምቅ ጫጫታም ይበዛል።

  • ገጽ 100 ከላይ፦ ሲላስና ይሁዳ በሶርያዋ አንጾኪያ የሚገኘውን ጉባኤ ሲያበረታቱ። (ሥራ 15:30-32) ከታች፦ አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካች በኡጋንዳ ለሚገኝ አንድ ጉባኤ ንግግር ሲሰጥ።

  • ገጽ 107 በኢየሩሳሌም ያለው ጉባኤ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተሰብስቦ።

  • ገጽ 124 ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በሮማውያን የንግድ መርከብ ተሳፍረው ሲጓዙ። የወደብ መብራት ከርቀት ይታያል።

  • ገጽ 139 ጳውሎስና ሲላስ በቁጣ ገንፍሎ ከወጣ ሕዝብ ለማምለጥ አንድ ግቢ ውስጥ ሲገቡ።

  • ገጽ 155 ጋልዮስ የጳውሎስን ከሳሾች ሲያባርራቸው። ለሥልጣኑ የሚመጥን ልብስ ለብሷል፤ ወይን ጠጅ ጥለት ያለው ነጭ የንጉሣውያን ልብስ እንዲሁም ካልኬ የሚባለውን ጫማ አድርጓል።

  • ገጽ 158 ድሜጥሮስ በኤፌሶን በሚገኝ የብር አንጥረኛ ሱቅ ውስጥ ሠራተኞቹን ሲያናግር። ከብር የተሠሩ የአርጤምስ ቤተ መቅደስ ቅርጾች እንደ ስጦታ ዕቃ ይሸጡ ነበር።

  • ገጽ 171 ጳውሎስና የጉዞ ጓደኞቹ መርከብ ሲሳፈሩ። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. የተገነባው የታላቁ ወደብ ሐውልት ከበስተጀርባ ይታያል።

  • ገጽ 180 ከታች፦ በ1940ዎቹ በካናዳ ጽሑፎቻችን በታገዱበት ወቅት አንድ ወጣት የይሖዋ ምሥክር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን በድብቅ ሲያመጣ። (አስመስሎ የተነሳ ፎቶግራፍ።)

  • ገጽ 182 ጳውሎስ ሽማግሌዎቹ ያቀረቡለትን ጥያቄ ሲቀበል። መዋጮውን ለማድረስ አብረውት የመጡት ሉቃስና ጢሞቴዎስ ከበስተኋላ ተቀምጠዋል።

  • ገጽ 190 የጳውሎስ እህት ልጅ ቀላውዴዎስ ሉስዮስን ሲያነጋግረው፤ ቦታው ጳውሎስ እንደታሰረበት የሚገመተው የአንቶኒያ ግንብ ነው። ከበስተጀርባ የሄሮድስ ቤተ መቅደስ ይታያል።

  • ገጽ 206 ጳውሎስ በአንድ የጭነት መርከብ ውስጠኛ ክፍል ሆኖ በጉዞ ለዛሉት መንገደኞች ሲጸልይ።

  • ገጽ 222 እስረኛው ጳውሎስ ከአንድ የሮም ወታደር ጋር በሰንሰለት ተቆራኝቶ የሮምን ከተማ በከፊል እየተመለከተ።