ትክክል የሆነውን ለማድረግ ያለብን ትግል
ምዕራፍ 26
ትክክል የሆነውን ለማድረግ ያለብን ትግል
1. ክርስቲያኖች ምን ሁለት ነገሮችን መታገል አለባቸው?
የሰይጣን ዓለም እስካለ ድረስ ክርስቲያኖች ክፉ የሆነው ግፊቱ እንዳይለውጣቸው መታገል ይኖርባቸዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ “የዲያብሎስን ሽንገላ [ወይም ተንኰል] ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ” ሲል ጽፏል። (ኤፌሶን 6:11-18) ይሁን እንጂ የምንታገለው ሰይጣንንና የሰይጣንን ዓለም ብቻ አይደለም። መጥፎ የሆነውን እንድንፈጽም የሚቀሰቀሱብንን የራሳችን ምኞቶች ጭምር መታገል ያስፈልገናል። መጽሐፍ ቅዱስ “የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነው” ይላል። — ዘፍጥረት 8:21፤ ሮሜ 5:12
2. (ሀ) ብዙ ጊዜ መጥፎ ለማድረግ ኃይለኛ ምኞት የሚያድርብን ለምንድን ነው? (ለ) መጥፎ ምኞቶችን መታገል ያለብን ለምንድን ነው?
2 ከመጀመሪያው ሰው ከአዳም በተወረሰው ኃጢአት ምክንያት ልባችን ክፉ የሆነውን ለማድረግ ይመኝ ይሆናል። በዚህ ምኞት ከተሸነፍን በአዲሱ የአምላክ ሥርዓት ውስጥ የዘላለም ሕይወት አናገኝም። ስለዚህ ትክክል የሆነውን ለማድረግ መታገል ያስፈልገናል። ሌላው ቀርቶ ሐዋርያው ጳውሎስም እንኳን እንዲህ ዓይነቱ ትግል ነበረበት። እርሱም “መልካሙን አደርግ ዘንድ ስወድ በእኔ ክፉ እንዲያድርብኝ ሕግን አገኛለሁ” በማለት ሁኔታውን ገልጾታል። (ሮሜ 7:21-23) አንተም ይህ ውጊያ ወይም ትግል ከባድ ሆኖ ታገኘው ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ በውስጥህ ከባድ የሃሳብ ግጭት ይፈጠር ይሆናል። በዚህ ጊዜ ምን ለማድረግ ትወስናለህ?
3. (ሀ) ብዙ ሰዎች በውስጣቸው ምን ግጭት አለባቸው? (ለ) ብዙ ሰዎች ትክክል የሆነውን ለማድረግ ፈልገው ሳለ መጥፎ በማድረጋቸው የትኛው ሐቅ ጎልቶ ይታያል?
3 በምድር ላይ ፍጹም ሁኔታዎች ተፈጥረው ለዘላለም እንድንኖር አምላክ የሰጠንን አስደናቂ ተስፋ ታውቃለህ። እነዚህን ተስፋዎች ታምንባቸዋለህ፤ እነዚህንም መልካም ነገሮች ለማግኘት ትፈልጋለህ። ስለዚህ አምላክን ማገልገሉ ለዘለቄታው እንደሚጠቅምህ ታውቃለህ። ይሁን እንጂ በልብህ ውስጥ መጥፎ መሆናቸውን የምታውቃቸውን ነገሮች ትመኝ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ዝሙት ለመፈጸም፣ ለመስረቅ ወይም በሌላ ዓይነት መጥፎ አድራጎት ለመሳተፍ ኃይለኛ ምኞት ያድርብህ ይሆናል። ኤርምያስ 17:9
ይህንን መጽሐፍ እያጠኑ ያሉ አንዳንድ ሰዎች አምላክ እነዚህን ነገሮች እንደሚያወግዛቸው ቢያውቁም እንደነዚህ ያሉ መጥፎ ድርጊቶችን እየፈጸሙ ሊሆን ይችላል። ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ እየፈለጉ መጥፎውን መሥራታቸው “የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው” የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። —በትግሉ ማሸነፍ ይቻላል
4. (ሀ) በትግሉ ማሸነፋችን ወይም መሸነፋችን በማን ላይ የተመካ ነው? (ለ) ትክክል የሆነውን ለመሥራት በሚደረገው ትግል ለማሸነፍ ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
4 እንዲህም ሲባል አንድ ሰው መጥፎ ለማድረግ ያደረበትን ኃይለኛ ምኞት ሊቆጣጠረው አይችልም ማለት አይደለም። ፍላጎቱ ካለህ ልብህ በትክክለኛው መንገድ እንዲመራህ ልታጠነክረው ትችላለህ። ይህን ማድረጉ ግን ያንተው ፋንታ ነው። (መዝሙር 26:1, 11) ማንም ሌላ ሰው ውጊያውን ሊያሸንፍልህ አይችልም። ስለዚህ ከሁሉ በፊት ሕይወት ሰጪ የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት መውሰድህን ቀጥል። (ዮሐንስ 17:3) ይሁን እንጂ ይህንን እውቀት ወደ ጭንቅላትህ መክተቱ አይበቃም። ወደ ልብህ ጠልቆ መግባት ይኖርበታል። የምትማረውን ነገር በሥራ ላይ ለማዋል ፍላጎት እስኪቀሰቀስብህ ድረስ በጥልቅ እንዲነካህ ያስፈልጋል።
5. ለአምላክ ሕጎች የልብ አድናቆት ሊያድርብህ የሚችለው እንዴት ነው?
5 ይሁን እንጂ ለአምላክ ሕጎች ልባዊ አድናቆት ሊያድርብህ የሚችለው እንዴት ነው? ስለ እነርሱ ማሰላሰል ወይም ጠለቅ ብለህ ማሰብ ያስፈልግሃል። ለምሳሌ እንዲህ እያልክ ራስህን ጠይቅ:- አምላክን መታዘዙ የሚያመጣው ልዩነት ምንድን ነው? ከዚያም የሚቀጥለውን እንደጻፈችው የ19 ዓመት ልጅ ያሉ የአምላክን ሕግ የሚጥሱ ሰዎች ምን ዓይነት ኑሮ እንዳላቸው ተመልከት “ሦስት ጊዜ የአባለዘር በሽታ ያዘኝ፤ ለሦስተኛ ጊዜ ሲይዘኝ ልጅ ለመውለድ የነበረኝን ችሎታ አጣሁ፤ ምክንያቱም ማሕፀኔን አስወጥቻለሁ።” ሰዎች የአምላክን ሕጎች ሳይታዘዙ ሲቀሩ የሚፈጠሩትን ችግሮች ሁሉ ማሰቡ በእውነትም የሚያሳዝን ነው። (2 ሳሙኤል 13:1-19) ዝሙት የፈጸመች አንዲት ሴት “ካለመታዘዝ ጋር የሚመጣው ስቃይና የስሜት መቃወስ ሲታሰብ ነገሩ ፈጽሞ ሊደረግ የማይገባው ነው። በአሁኑ ጊዜ ያን በመፈጸሜ ስቃዬን እያየሁ ነው” በማለት በሐዘን ተናግራለች።
6. (ሀ) መጥፎ የሆነውን በማድረግ የሚገኝ ደስታ ምንም ጥቅም የሌለው ለምንድን ነው? (ለ) ሙሴ በግብጽ ውስጥ ምን ዓይነት ኑሮ አግኝቶ ሊደሰት ይችል ነበር?
6 ሆኖም ሰዎች ዝሙት መፈጸምና መስከር እንዲሁም ዕፅ መውሰድ ደስ ይላል ብለው ሲናገሩ ትሰማለህ። ይሁን እንጂ ደስታ የሚሉት ነገር ጊዜያዊ ብቻ ነው። እውነተኛና ዘላቂ ደስታ የሚያሳጣህን ድርጊት ለመፈጸም ፈጽሞ አትታለል። ዕብራውያን 11:24, 25) እንግዲያው ከዚህ ለማየት እንደምንችለው በግብጹ የንጉሣዊ ቤተሰብ ኑሮ ውሰጥ ብልሹ በሆነ ምግባርና በልክስክስነት ደስታ ይገኝ ነበር። ታዲያ ሙሴ ከዚህ ሁሉ ለምን ሸሸ?
የፈርዖን ሴት ልጅ እንደ ልጅዋ አድርጋ ያሳደገችውን ሙሴን አስታውስ። እርሱ በጥንቷ ግብጽ ውስጥ በንጉሣዊ ቤተሰብ መሐል በሀብት ተንደላቅቆ አደገ። ይሁን እንጂ ካደገ በኋላ “ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ” ሲል መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። (7. ሙሴ በግብጹ የንጉሣዊ ቤተሰብ ውስጥ ከሚገኘው “ጊዜያዊ የኃጢአት ደስታ” ለምን ሸሸ?
7 ሙሴ በይሖዋ አምላክ ስላመነ ነው። በተጨማሪም በግብጹ የንጉሣዊ ቤተሰብ ውስጥ በኃጢአት ማግኘት ከሚችለው ጊዜያዊ ደስታ በጣም የላቀ ሌላ ነገር እንዳለ ያውቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ “ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቷልና ” ሲል ይነግረናል። ሙሴ አምላክ ስለሰጣቸው ተስፋዎች ያሰላስል ወይም በጥልቅ ያስብ ነበር። አምላክ ጻድቅ የሆነ አዲስ ሥርዓት ለመፍጠር የተናገረውን ዓላማ ያምንበት ነበር። ልቡ ይሖዋ ለሰው ዘር በሚያሳየው ታላቅ ፍቅርና እንክብካቤ ተነክቶ ነበር። ሙሴ ይሖዋን ያወቀው ስለ እርሱ በመስማት ወይም በማንበብ ብቻ አልነበረም። ዕብራውያን 11:26, 27) ይሖዋ ለሙሴ እውን ሆኖለት ነበር። ይሖዋ ስለ ዘላለም ሕይወት የሰጣቸው ተስፋዎችም እንደዚሁ እውን ሆነው ይታዩት ነበር።
“የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶአል” በማለት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (8. (ሀ) ትክክል የሆነውን ለመሥራት በሚደረገው ትግል ለማሸነፍ ምን ያስፈልገናል? (ለ) አንድ ወጣት የገለጸው ምን ዓይነት አስተሳሰብ ቢኖረን ጥበብ ነው?
8 ያንተስ ሁኔታ ልክ እንደዚሁ ነውን? ይሖዋን እውን እንደሆነ አካል፤ አንተን እንደሚያፈቅር አባት አድርገህ ትመለከተዋለህን? አምላክ ገነት በምትሆነዋ ምድር ላይ ስለሚሰጠን የዘላለም ሕይወት ተስፋ በምታነብበት ጊዜ አንተም በዚያ ገብተህ እነዚህን በረከቶች አግኝተህ ስትደሰት ይታይሃልን? (ገጽ 156-162 ተመልከት) እኛን ወደ ስህተት ለማስገባት ከሚመጡብን ብዙ ተጽእኖዎች ጋር በምናደርገው ትግል አሸናፊ ለመሆን ከይሖዋ ጋር ቅርብ ዝምድና እንዲኖረን ያስፈልጋል። በተጨማሪም ልክ ሙሴ እንዳደረገው ‘ብድራታችንን ትኩር ብለን መመልከት’ ያስፈልገናል። ዝሙት ለመፈጸም ፈተና የደረሰበት አንድ የ20 ዓመት ወጣት የሙሴ ዓይነት አስተሳሰብ ነበረው። እርሱም:- “የዘላለም ሕይወት ተስፋዬን ከፍ አድርጌ ይዤው ስለነበረ ለጥቂት ደቂቃዎች ብልግና ልለውጠው አልቻልኩም” ብሏል። ይህ ሊኖረን የሚገባ ትክክለኛ አቋም አይደለምን?
ሌሎች ከሠሯቸው ስሕተቶች መማር
9. ትክክል የሆነውን ለመሥራት በሚደረገው ትግል ንጉሥ ዳዊት የወደቀው በምን መንገድ ነው?
9 በዚህ ውጊያ ውስጥ ጥበቃህን ለአንድ አፍታም ቢሆን ላላ ማድረግ አትችልም። ንጉሥ ዳዊት አንድ ጊዜ እንደዚያ አድርጎ ነበር። አንድ ቀን በቤቱ ጣሪያ ላይ ቆሞ ሲመለከት ውብ የነበረችው ቤርሳቤህ ገላዋን ስትታጠብ አየ። ተገቢ ያልሆኑ ሃሳቦች በልቡ ውስጥ ከማደጋቸው በፊት ወዲያው ዘወር በማለት ፋንታ ትኩር ብሎ መመልከቱን ቀጠለበት። 2 ሳሙኤል 11:1-17
ከቤርሳቤህ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ያደረበት ምኞት በጣም ስላየለበት ከእርሷ ጋር ለመተኛት ሲል ወደ ቤተ መንግሥቱ አስመጣት። በኋላም ስላረገዘችበትና የፈጸመውን ምንዝር ለመሸፋፈን ባለመቻሉ ባሏ በጦር ሜዳ ላይ እንዲገደል አደረገ። —10. (ሀ) ዳዊት ለኃጢአቱ የተቀጣው እንዴት ነው? (ለ) ዳዊት ወደ ምንዝር እንዳይወድቅ ምን ሊከለክለው ይችል ነበር?
10 ይህ የከፋ ኃጢአት ነበር። ዳዊትም በዚህ ምክንያት ፍዳውን አይቷል። በፈጸመው ድርጊት ምክንያት በጭንቀት ከመሰቃየቱም በላይ ይሖዋ በቀረው የሕይወቱ ዘመን ከቤተሰቡ ሁከት እንዳይጠፋ በማድረግ ቀጣው። (መዝሙር 51:3, 4፤ 2 ሳሙኤል 12:10-12) የዳዊት ልብ እርሱ ከሚገምተው በላይ ተንኰለኛ ነበረች። የተሳሳቱ ምኞቶቹ አሸነፉት። ከዚያም በኋላ “እነሆ በአመጻ ተጸነስሁ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ” ብሎ ተናገረ። (መዝሙር 51:5) ይሁን እንጂ ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር የፈጸመው መጥፎ ድርጊት የግድ መሆን ያለበት ነገር አይደለም። የዳዊት ችግር እርሷን ማየቱን አለማቆሙ ነበር። የሌላ ወንድ ሚስት ለሆነችው ሴት የተሰማው የጾታ ፍላጎት እንዲያድግ ከሚገፋፋው ሁኔታ አልሸሸም።
11. (ሀ) በዳዊት ላይ ከደረሰው ነገር ምን መማር አለብን? (ለ) ምን ድርጊቶች ፍትወተ ሥጋን ሊቀሰቅሱ ይችላሉ ብለህ ታስባለህ? (ሐ) አንድ ወጣት እንደተናገረው ጥበበኛ የሆነ ሰው ከምን ይርቃል?
11 በዳዊት ላይ ከደረሰው ሁኔታ ተገቢ ያልሆኑ የጾታ ስሜቶችን ከሚቀሰቅሱ ሁኔታዎች ራሳችንን መጠበቅ እንደሚገባን እንማራለን። ለምሳሌ ያህል ለጾታ ትኩረት የሚሰጡ መጻሕፍት ብታነብ፣ ወይም እንደዚህ ያሉ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችና ፊልሞች ብትመለከት ምን ይሆናል? የጾታ ፍላጎትህ መቀስቀሱ አይቀርም። እንግዲያው የጾታ ፍላጎት ከሚቀሰቅሱ ተግባሮች ወይም መዝናኛዎች ራቅ። (ቆላስይስ 3:5፤ 1 ተሰሎንቄ 4:3-5፤ ኤፌሶን 5:3-5) ከሌላ ሰው ጋር ወደ ዝሙት በሚመራ ሁኔታ ላይ አትገኝ። አንድ የ17 ዓመት ልጅ የሚከተለውን ጥበብ ያለበት ሃሳብ ሰጥቷል:- “ማንም ሰው የት ላይ ስደርስ ማቆም እንዳለብኝ አውቃለሁ ብሎ ሊናገር ይችላል። እውነት ነው አንድ ሰው መቼ ማቆም እንዳለበት ሊያውቅ ይችላል፤ ሆኖም ስንቶቹ እንደዚያ አድርገዋል? ከዚያ ሁኔታ ዘወር ማለቱ የተሻለ ነው።”
12. የትኛውን የዮሴፍ ምሳሌ ማስታወስ አለብን?
12 ዳዊት የዮሴፍን ምሳሌ ቢያስታውስ ኖሮ በአምላክ ላይ ያንን ታላቅ ኃጢአት ባልፈጸመም ነበር። ዮሴፍ በግብጽ ውስጥ የጶጢፋርን ቤተሰብ እንዲያስተዳድር ሃላፊነት ተሰጠው። ጶጢፋር ወደ ሌላ ቦታ ሲሄድ በጾታ ፍላጎት ያበደችው ሚስቱ ውብ የነበረውን ዮሴፍን “ከእኔ ጋር ተኛ እያለች” ለማሳት ትሞክር ነበር። ዮሴፍ ግን እምቢ አለ። ከዚያም አንድ ቀን ያዘችውና ከእርሷ ጋር እንዲተኛ ለማድረግ ሞከረች። ዮሴፍ ግን እጅዋን አስለቀቀና ጥሏት ሸሸ። የጾታ ምኞትን ስለ ማርካት በማሰብ ፋንታ በአምላክ ፊት ትክክል የሆነውን ስለማድረግ በማሰቡ የልቡን ጥንካሬ ጠበቀ። “እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?” ብሎ ጠየቀ። —እንድታሸንፍ የተዘጋጀልህ እርዳታ
13, 14. (ሀ) በዚህ ትግል ለማሸነፍ ምን ያስፈልጋል? (ለ) በቆሮንቶስ የነበሩት ሰዎች ምን ዓይነት ለውጦችን አደረጉ? ከየት ባገኙት እርዳታስ? (ሐ) ጳውሎስና ቲቶ በፊት ምን ዓይነት ሰዎች ነበሩ?
13 በዚህ ትግል ለማሸነፍ ከፈለግህ የምታውቀውን እንድትሠራበት ግፊት እስኪያድርብህ ድረስ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ወደ ልብህ ጠልቆ እንዲገባ መፍቀድ ይኖርብሃል። ይሁን እንጂ ከአምላክ ሕዝብም ጋር 1 ቆሮንቶስ 6:9-11
መተባበር፣ የሚታየው የይሖዋ ድርጅት ክፍል መሆን ያስፈልግሃል። በመጥፎ ድርጊት የቱንም ያህል ጠልቀህ ብትገባም ይህ ድርጅት በሚሰጥህ እርዳታ አኗኗርህን ለመለወጥ ትችላለህ። አኗኗራቸውን ስለለወጡ በጥንቷ የቆሮንቶስ ከተማ ስለነበሩ ሰዎች ሲጽፍ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሏል:- “ወይስ አመጸኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ፣ ወይም ስግብግቦች ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፣ ተቀድሳችኋል፣ ጸድቃችኋል።” —14 እስቲ አስበው! ከእነዚያ የቀድሞ ክርስቲያኖች መካከል አንዳንዶቹ በፊተኛው ሕይወታቸው ዝሙት የሚፈጽሙ፣ የሚያመነዝሩ፣ ወንድ ከወንድ የጾታ ግንኙነት የሚያደርጉ፣ ሌቦችና ሰካራሞች ነበሩ። ይሁን እንጂ ከክርስቲያኑ ድርጅት እርዳታ አገኙና ተለወጡ። ሐዋርያው ጳውሎስ ራሱ በፊት መጥፎ ነገሮችን ሠርቶ ነበር። (1 ጢሞቴዎስ 1:15) ለክርስቲያን ወንድሙ ለቲቶ:- “እኛ ደግሞ አስቀድሞ የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፣ የምንስት፣ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ ” ነበርን ሲል ጽፎለታል — ቲቶ 3:3
15. (ሀ) ጳውሎስ ትክክል የሆነውን ለማድረግ ቀላል ሆኖ እንዳላገኘው የሚያሳየው ምንድን ነው? (ለ) ከጳውሎስ ምሳሌ እንዴት ለመጠቀም እንችላለን?
15 ጳውሎስ ክርስቲያን ከሆነ በኋላ ትክክል የሆነውን ለማድረግ ሁኔታው ቀላል ሆኖለታልን? አልሆነለትም። ጳውሎስ በፊት ባሪያ ሆኖላቸው ከነበሩት የተሳሳቱ ምኞቶችና ተድላዎች ጋር በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ውጊያ አካሂዷል። እንዲህ ብሎ ጻፈ:- “ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልኩ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምኩ አስገዛዋለሁ።” (1 ቆሮንቶስ 9:27) ጳውሎስ ሥጋውን ኃይለኛ ቁጥጥር አድርጎበታል። ሥጋው መጥፎ ለማድረግ በሚመኝበት ጊዜ ትክክል የሆነውን ለማድረግ ራሱን አስገድዷል። አንተም እርሱ ያደረገውን ብታደርግ በውጊያው ታሸንፋለህ።
16. ትክክል የሆነውን ለመሥራት በሚደረገው ትግል ለማሸነፍ የትኞቹ ዘመናዊ ምሳሌዎች ሊረዱን ይችላሉ?
16 አንድን ዓይነት መጥፎ ልማድ ማሸነፉ ከብዶህ ከሆነ የይሖዋ ምስክሮች በሚቀጥለው ጊዜ በሚያደርጉት ትልቅ ስብሰባ ተገኝ። በዚያ የሚገኙት ሰዎች በሚያሳዩት ንጹሕ ጠባይና ደስታ በጣም እንደምትነካ አያጠራጥርም። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሰዎች መካከል ብዙዎቹ ዝሙት፣ ምንዝር፣ ስካር፣ ግብረ ሰዶም፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የዕፅ ሱሰኝነት፣ ስርቆት፣ ማጭበርበር፣ ውሸትና ቁማር በጣም የተስፋፋበት ዓለም ክፍል ነበሩ። ብዙዎቹ አንድ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ይፈጽሙ ነበር። 1 ጴጥሮስ 4:3, 4) በተጨማሪም ከዚያ አነስ በሚሉት የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጓቸው የጉባኤ ስብሰባዎች ስትገኝ [ይህን ሳትዘገይ ማድረግ ይኖርብሃል] አንተ አሁን እየታገልካቸው ያሉትን መጥፎ ልማዶችና ምኞቶች ባሸነፉ ሰዎች መሃል ትቀመጣለህ። ስለዚህ አይዞህ! እነርሱ ትክክል የሆነውን ለመሥራት በሚደረገው ትግል እያሸነፉ ናቸው። አንተም በአምላክ እርዳታ ለማሸነፍ ትችላለህ።
(17. (ሀ) በትግሉ ለማሸነፍ ከፈለግን ከእነማን ጋር መሰብሰብና መገናኘት ያስፈልገናል? (ለ) ችግሮችህን ለማስወገድ ከእነማን እርዳታ ማግኘት ትችላለህ?
17 ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ለተወሰነ ጊዜ ስታጠና ቆይተህ ከሆነ በመንግሥት አዳራሻቸው በሚደረጉት ስብሰባዎች እንደተገኘህ አያጠራጥርም። በዚህ ዓይነቱ ስብሰባ መገኘቱን የዘወትር ልማድህ አድርገው። ሁላችንም ከእንዲህ ዓይነቱ ክርስቲያናዊ ስብሰባ የሚገኘው ማጽናኛ ያስፈልገናል። (ዕብራውያን 10:24, 25) የጉባኤውን “ሽማግሌዎች” እወቃቸው። ኃላፊነታቸው ‘የአምላክን መንጋ እንደ እረኛ ሆነው መጠበቅ’ ነው። (1 ጴጥሮስ 5:1-3፤ ሥራ 20:28) እንግዲያውስ ከአምላክ ሕጎች ጋር የሚጋጭ አንድ ዓይነት ልማድ ለማሸነፍ እርዳታ የሚያስፈልግህ ከሆነ ወደ እነርሱ ለመሄድ አታመንታ። አፍቃሪ፣ ደግና አሳቢ ሆነው ታገኛቸዋለህ። — 1 ተሰሎንቄ 2:7, 8
18. ወደፊት የሚሆን ምን ነገር ውጊያውን እንድትገፋበት ኃይል ይሰጥሃል?
18 የሰይጣን ዓለም ብቻ ሳይሆን በውስጣችን ያለው ኃጢአተኛ ሁኔታችን መጥፎ እንድንሠራ ይገፋፋናል። ስለዚህ ለአምላክ ታማኝ ሆኖ መገኘቱ በየዕለቱ ትግል ማድረግ የሚያስፈልገው ነው። ይሁን እንጂ ትግሉ ለዘላለም የማይቀጥል መሆኑ እንዴት ጥሩ ነው! በቅርቡ ሰይጣን ይወገዳል። ጠቅላላው ክፉ ዓለሙም ይደመሰሳል። ከዚያም በጣም ቀርቦ ባለው በአዲሱ የአምላክ ሥርዓት ውስጥ አካሄዳችንን በጣም ቀላል የሚያደርጉልን የጽድቅ ሁኔታዎች ይሰፍናሉ። በመጨረሻው የኃጢአት ርዝራዥ በሙሉ ይጠፋል። ትክክል የሆነውን ለመሥራት የምናደርገው ይህ ከባድ ውጊያ ከዚያ በኋላ ይቀርልናል።
19. ይሖዋን ለማስደሰት ማንኛውንም ጥረት ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን ያለብህ ለምንድን ነው?
19 ይህ አዲስ ሥርዓት ስለሚያመጣቸው በረከቶች ዘወትር አስብ። አዎን፣ “የመዳንን ተስፋ ራስ ቁር” በራስህ ላይ ድፋ። (1 ተሰሎንቄ 5:8) አቋምህ እንደሚከተለው ብላ እንደተናገረችው ሴት አቋም እንዲሆን እንመኛለን:- “ይሖዋ ስላደረገልኝና ወደፊት ሊያደርግልኝ ተስፋ ስለሰጠኝ ነገር ሁሉ አስባለሁ። ይሖዋ በእኔ ላይ ትዕግሥቱ አላለቀም። በብዙ መንገዶች ባርኮኛል። ከሁሉ የተሻለውን ነገር ብቻ እንደሚመኝልኝ አውቃለሁ። እኔም እርሱን ለማስደሰት እፈልጋለሁ። የዘላለም ሕይወት ማንኛውም ጥረት ሊደረግለት የሚገባው ነው።” ጽድቅን በታማኝነት ከተከተልን ይሖዋ ለሚያፈቅሩት አመጣላችኋለሁ ብሎ ተስፋ የሰጣቸው ነገሮች በሙሉ እውን ሲሆኑ እናያለን። — ኢያሱ 21:45
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 219 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
በጥንቷ ግብጽ አንድ ሰው በደስታ መኖር የሚችልበት ሁኔታ ከነበረ ሙሴ ያንን ለምን አልፈለገውም?
[በገጽ 220, 221 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]
ዳዊት ትኩር ብሎ መመልከቱን ቀጠለ፤ ወደ ብልግና ከመራው ሁኔታ ዘወር አላለም
[በገጽ 222 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ዮሴፍ የጶጢፋር ሚስት በኃይል አስገድዳ አብሯት እንዲተኛ ለማድረግ ስትሞክር ጥሏት ሸሸ