“ተከታዬ ሁን”
የዚህ መጽሐፍ ዓላማ የኢየሱስን ሕይወትና አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መከለስ ሳይሆን እሱን መከተል የሚቻልበትን መንገድ በግልጽ ማስተዋል እንድንችል መርዳት ነው።
መቅድም
ለኢየሱስ ያለህ ፍቅር እንዲያድግ እንዲሁም የእሱን ፈለግ በጥብቅ በመከተል አሁንም ሆነ ለዘላለም የይሖዋን ልብ ደስ ማሰኘት እንድትችል ልባዊ ምኞታችን ነው።
ምዕራፍ 1
“ተከታዬ ሁን”—ኢየሱስ ምን ማለቱ ነበር?
እውነተኛ የኢየሱስ ተከታይ መሆን ከምንናገረው ነገር አሊያም ለእሱ ካለን ስሜት የበለጠ ነገርን ያካትታል።
ምዕራፍ 2
“መንገድ፣ እውነትና ሕይወት”
ወደ አብ መቅረብ የሚቻለው በልጁ በኩል ብቻ ነው። ኢየሱስ፣ አምላክ ለአጽናፈ ዓለሙ ያለውን ዓላማ በማስፈጸም ረገድ ወሳኝ የሆነ ቦታ ተሰጥቶታል።
ክፍል 1
ክርስቶስን “መጥተህ እይ”
ምዕራፍ 4
“እነሆ፣ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ”
ኢየሱስ በሦስት መንገዶች እንደ አንበሳ ዓይነት ድፍረት አሳይቷል፦ ለእውነት ጥብቅና በመቆም፣ ለፍትሕ በመቆርቆርና ተቃውሞን በመጋፈጥ።
ምዕራፍ 7
“በጽናት የተቋቋመውን እሱን በጥሞና አስቡ”
ኢየሱስ በጽናት ረገድ እንከን የለሽ ታሪክ አስመዝግቧል። ለመጽናት የረዳው ምንድን ነው? የእሱን የጽናት ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?
ክፍል 2
‘ማስተማርና ምሥራቹን መስበክ’
ምዕራፍ 8
“የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው”
ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት የሰበከው ለምን እንደሆነ፣ ስለ ምን እንደሰበከና ስለተሰጠው ሥራ ምን አመለካከት እንደነበረው እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
ምዕራፍ 10
“ተብሎ ተጽፏል”
ከአምላክ ቃል መጥቀስ፣ ለቃሉ ጥብቅና መቆምና ቃሉን ማብራራት እውነትን ለሌሎች በማካፈል ረገድ የኢየሱስን ምሳሌ የምንከተልባቸው ቁልፍ መንገዶች ናቸው።
ምዕራፍ 11
“ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም”
ኢየሱስ ከተጠቀመባቸው የማስተማሪያ ዘዴዎች መካከል ሦስቱን እንዲሁም እነዚህን ዘዴዎች እንዴት መኮረጅ እንደምንችል እንድትመረምር እንጋብዝሃለን።
ክፍል 3
“ክርስቶስ ያለው ፍቅር ግድ ይለናል”
ምዕራፍ 14
‘እጅግ ብዙ ሰዎች ወደ እሱ መጡ’
ልጆችን ጨምሮ በጣም ብዙ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መቅረብ አልከበዳቸውም። ኢየሱስ ይህን ያህል የሚቀረብ ሰው እንዲሆን ያስቻለው ምንድን ነው?
ምዕራፍ 16
“ኢየሱስ . . . እስከ መጨረሻው ወደዳቸው”
ኢየሱስ አገልግሎቱን ባከናወነባቸው ጊዜያት ሁሉ ለደቀ መዛሙርቱ ያለውን ፍቅር በተለያዩ መንገዶች አሳይቷል። እኛስ ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት እንደ ኢየሱስ ዓይነት ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?