በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 2

‘ማስተማርና ምሥራቹን መስበክ’

‘ማስተማርና ምሥራቹን መስበክ’

አናጺነት፣ ተአምር መሥራት፣ መፈወስ። ኢየሱስ እነዚህንና ሌሎች ብዙ ነገሮችን አከናውኗል። ይሁን እንጂ ሰዎች ሲጠሩት በእነዚህ መግለጫዎች አልተጠቀሙም። ከዚህ ይልቅ መምህር እያሉ ይጠሩት ነበር። ደግሞም በሕይወቱ ውስጥ ያከናወነው ዋና ሥራ ‘ማስተማርና ምሥራቹን መስበክ’ ነበር። (ማቴዎስ 4:​23) እኛም የኢየሱስ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን ተመሳሳይ ሥራ አለን። በዚህ ክፍል ውስጥ ኢየሱስ የተወውን ምሳሌ እንመረምራለን፤ ይህም ሥራችንን በምን መንገድ ማከናወን እንዳለብን ትምህርት ይሰጠናል።