በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 1

ክርስቶስን “መጥተህ እይ”

ክርስቶስን “መጥተህ እይ”

ኢየሱስ ሰው ሆኖ በምድር ላይ የኖረው ከ2,000 ዓመታት ገደማ በፊት ቢሆንም ዛሬም የአምላክን ልጅ ‘መጥተን ማየት’ እንችላለን። (ዮሐንስ 1:​46) የወንጌል ዘገባዎች ስለ ኢየሱስ ማንነት፣ አስተሳሰብና ነገሮችን ስለሚያከናውንበት መንገድ ሕያው የሆነ ትረካ ይዘዋል። ይህ ክፍል የኢየሱስን ድንቅ ባሕርያት እንድንቃኝ ይረዳናል።