በአያያዝ ዘዴኛ ግን ጥብቅ መሆን
ጥናት 14
በአያያዝ ዘዴኛ ግን ጥብቅ መሆን
1. የዘዴኛነትን አያያዝ መኮትኮት የሚገባን ለምንድን ነው?
1 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲሰብኩ በላካቸው ጊዜ በሚናገሩትና በሚያደርጉት ሁሉ ልባሞች መሆን እንደሚያስፈልጋቸው ገልጾላቸው ነበር። ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ቃል ቢገባላቸውም አስፈላጊ ያልሆነ ችግር ሊያመጣባቸው የሚችል ነገር ማድረግ አልነበረባቸውም። (ማቴ. 10:16) ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው እንኳን አንዳቸው ሌላውን በግድየለሽነት እንዳይጎዱ ስለሚናገሯቸውና ስለሚያደርጓቸው ነገሮች መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል። (ምሳሌ 12:8, 18) ስለዚህ ዘዴኛነትን መኮትኮት ያስፈልጋል።
2. ዘዴ ማለት ምን ማለት ነው?
ሮሜ 9:33፤ 2 ቆሮ. 2:15, 16) ስለዚህ በአነጋገራችንና በአሠራራችን ዘዴኞች ብንሆንም ለአምላክ እውነት ግን ጥብቅ ነን።
2 ሰውን በዘዴ መያዝ ተብሎ የተተረጎመው “ታክት” የተባለው የእንግሊዝኛ ቃል “ከሌሎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት መደረግና መነገር ስለሚገባው ትክክለኛ ነገር ማስተዋል፣ ሌሎችን ያለማስከፋት ችሎታ” ተብሎ ተተርጉሟል። ዘዴኛ መሆን ማለት የሌሎች ስሜት በማይጎዳበት መንገድ መናገር ወይም ማድረግ ማለት ነው። በአነጋገራችንና በአሠራራችን ሌሎችን ለማስከፋት አንፈልግም። ይሁን እንጂ እንዲህ ሲባል በምንናገረው ወይም በምናደርገው ነገር ፈጽሞ ሌሎችን አናስከፋም ማለት አይደለም። የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ራሱ አንዳንዶችን ያስከፋቸዋል። (3. ለዘዴኛ አያያዝ መሠረቱ የአምላክ መንፈስ ፍሬ የሆነበትን መንገድ አብራራ።
3 የአምላክን የመንፈስ ፍሬዎች የምናሳይ ከሆንን በዕለታዊ ኑሮአችን ዘዴኛ ለመሆን አንቸገርም። (ገላ. 5:22, 23) ለምሳሌ ያህል ፍቅር ያለው ሰው ሌሎችን ለመርዳት ልባዊ የሆነ ፍላጎት ይኖረዋል እንጂ ሊያበሳጫቸው አይፈልግም። ደግ የሆነ ሰው በሚያደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ረጋ ያለና ጨዋ ይሆናል። ራስን የመግዛት ባሕርይ የኮተኮተና ፈታኝ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ እንኳ የማይቆጣ ሰው ሌላውን ሰው ወደራሱ አመለካከት መመለስ ይችላል። ቁጡና ግልፍተኛ የሆነ ሰው ግን የማይገባ ነገር ስለሚናገር የሚናገራቸው ሰዎች እንዲጠሉት ያደርጋል። (ምሳሌ 15:18) አነጋገራችንና ድርጊታችን ምክንያታዊ አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች የሚስብ እንጂ የሚያርቅ መሆን የለበትም።
4–8. (ሀ) ከቤት ወደ ቤት በምናደርገው አገልግሎት ዘዴኞች የምንሆነው እንዴት ነው? (ለ) ዘዴኛ ለመሆን ለትክክለኛ ነገር ያለንን የጸና አቋም ማላላት ይኖርብናልን? ዘዴኛ አያያዝ የሚጠይቀው ምን ማድረግን ነው?
4 በመስክ አገልግሎት ዘዴኛ መሆን። ከቤት ወደ ቤት በምታደርገው አገልግሎት የቤቱን ባለቤት በሚያሳስበው ጉዳይ ላይ ውይይት በመጀመርና የአምላክ መንግሥት እንዴት መፍትሔ እንደምታመጣ በመግለጽ ዘዴኛ መሆን ይቻላል። ሰውዬው ለጽድቅ ያለውን ፍቅር፣ ምክንያታዊ አስተሳሰብና የተሻለ ዘመን ለማየት ያለውን ፍላጎት ለማነሳሳት ሞክር። በሰውዬው ላይ ማሾፍ ወይም ሃይማኖታዊ አመለካከቱን ማውገዝ አእምሮውን ከመዝጋት በስተቀር የሚፈይደው ነገር አይኖርም። ስለዚህ ክርክር በሚያስነሱ ጉዳዮች ላይ ከመነጋገር ይልቅ ሰዎች በአጠቃላይ ትክክል ናቸው ብለው ስለሚያምኑባቸው ነገሮች ተናገር። አከራካሪ ወደሆነ ርዕሰ ጉዳይ ማለፍ አስፈላጊ ከሆነ በመጀመሪያ ከቤቱ ባለቤት ጋር የምትስማማበትን ነጥብ አግኝና ይህን ነጥብ ጠበቅና ጎላ አድርግ። የመንግሥቱን ተስፋ ሰጪ እውነቶችና በረከቶች በሰውዬው አእምሮ ውስጥ ለማስረጽ ከቻልክ ሌሎቹ ጉዳዮች ይገባናል የማንለውን የአምላክን ደግነት እየተገነዘበ ሲሄድ ይስተካከላሉ።
5 ዘዴኛ የሆነ ሰው የሚያናግረው ሰው በውይይቱ እንዲካፈልና አስተያየቱን በነፃነት እንዲገልጽ ለማበረታታት የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ጳውሎስ ከሚመሰክርላቸው ሰዎች አንጻር ነገሮችን ለመመልከት ጥረት ያደርግ ነበር። ይህን በማድረጉም ምሥራቹን አሳማኝ የሚያደርጉ ጠንካራ 1 ቆሮ. 9:20–22) እኛም እንዲሁ ማድረግ ይኖርብናል። ራሳችንን በሌሎች ቦታ አድርገን ለምን እንደዚህ ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ፣ ለምን እንደዚያ ብለው እንደሚያምኑና እንደሚናገሩ ለመረዳት መሞከር በዘዴ እንድንይዛቸው ያስችለናል። አስተሳሰባቸው የተለወጠው በሕይወታቸው ውስጥ ለየት ያለ ሁኔታ ስላጋጠማቸው ወይም እንደ ባለ ሥልጣን አድርገው በሚመለከቱት ነገር ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለሌላው ሰው አመለካከት ፍንጭ ካገኘህ አስተሳሰቡንና ለዚህ አስተሳሰቡ ምክንያት የሆነውን ነገር አላስፈላጊ ቅሬታ በመፍጠር ሳታስቀይመው ወደ መልእክትህ ወይም ወደ መንግሥቱ ምሥራች ልታስገባው ትችላለህ።
ምክንያቶችን ለማቅረብ ችሏል። (6 የሌላውን ሰው አመለካከት ግምት ውስጥ ማስገባት ለትክክለኛው ነገር ያለንን አቋም እንዳላላን ተደርጎ ሊቆጠር አይችልም። ዘዴኛነት ሐቁን ማጣመም ማለት አይደለም። በማንኛውም ጊዜ ትክክል ለሆነው ነገር የጸና አቋም መያዝ አስፈላጊ ነው። ይህ ካልሆነ ግን ዘዴኛ ከመሆን ይልቅ ለእውነት ያለንን አቋም ማላላት ይሆንብናል። እንዲህ የምናደርገው ለጽድቅ ባለን ፍቅር ሳይሆን ለሰዎች ባለን ፍርሃት ተገፋፍተን ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ዘዴኛ መሆን ለትክክለኛው ነገር ያለንን አቋም ማላላት ሳይሆን አንዳንድ እውቀቶች የሚሰጡበትን ትክክለኛ ጊዜ መወሰን ነው። ሰውዬው የተናገራቸውን አንዳንድ ነገሮች እንዳልሰሙ ሆኖ ማለፍ ዘዴ የሚሆንበት ጊዜ አለ። አንዳንድ ነገሮችን ደግሞ ሰውዬው እስኪበስል ድረስ ሳይናገሩ ማቆየት ጥሩ ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ “የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፣ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም” ብሎ ነበር። (ዮሐ. 16:12) ስለዚህ ከምናነጋግረው ሰው ጋር የማንስማማበት ነጥብ ቢኖርም ወዲያው እያንዳንዱን ስህተት መናገር አይኖርብንም። ብንናገር አእምሮውን ከመዝጋትና ተጨማሪ ውይይት እንዳያደርግ ከመከልከል በቀር ሌላ ጥቅም አይኖረውም።
7 ከአንድ ሰው ጋር በምናደርገው ውይይት ወቅት ሰውዬው ስህተት ናቸው ብሎ የሚያስባቸውን በርካታ ነጥቦች ከመጽሐፍ ቅዱስ ቢጠቅስ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ለእያንዳንዱ የተቃውሞ ሐሳብ መልስ ለመስጠት አስቸጋሪ ይሆናል። አብዛኛውን ጊዜ ከእነዚህ የተቃውሞ ሐሳቦች ውስጥ አብዛኞቹን ችላ ብሎ በጊዜው ውይይት ከሚደረግበት ርዕሰ ጉዳይ ላይ አግባብነት ባላቸው ነጥቦች ላይ ብቻ ማተኮሩ የተሻለ ይሆናል። ወይም ሰውዬው ዓለማዊ ክርክር ውስጥ ሊያስገባህ ይሞክር ይሆናል። እንደነዚህ ስላሉት ዓለማዊ ችግሮች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ብቻ በመናገር በዘዴ ከክርክሩ ራቅ። ይህንንም በማድረግህ የኢየሱስን አርዓያ ትከተላለህ። — ማቴ. 22:15–22
8 የተቆጣ የቤት ባለቤት ሲያጋጥምህ ዘዴኛ ግን ጥብቅ ሁን። በምሳሌ 15:1 ላይ የሚገኘውን ምክር አስታውስ። “የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች፤ ሸካራ ቃል ግን ቁጣን ታስነሳለች።” ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች ፈጽሞ ምክንያተ ቢስ ሲሆኑ ትቶ መሄድ የተሻለ ይሆናል። — ማቴ. 7:6
ሰውዬውን ረጋ ለማድረግ ስትል ብቻ ለእውነት ያለህን አቋም አታላላ። ከዚህ ይልቅ ሰውዬው ለምን እንደዚያ እንደተሰማው ለመረዳት ሞክር። ይህን የመሰለ አመለካከት ለምን እንደኖረው ልትጠይቀው ትችል ይሆናል። ለጥያቄህ መልስ ከሰጠህ አንተም በተራህ እንደዚያ ያለ አመለካከት የኖረህ ለምን እንደሆነ ልትነግረው ትችላለህ። ውይይቱን ለማቆየት የቻልከው ለምንም ያህል ጊዜ ቢሆን የተሻለ ውጤት የሚያስገኝልህ ዘዴኛ መሆን ነው።9, 10. ከወንድሞቻችን ጋር ባለን ግንኙነት ዘዴኛ አያያዝ ይፈለግብናልን?
9 ክርስቲያን ወንድሞችን በዘዴ መያዝ። ዘዴኛ መሆን የሚገባን ይሖዋን ለማያውቁ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ከመንፈሳዊ ወንድሞቻችን ጋር ባለን ግንኙነትም ሁሉ ነው። በመስክ አገልግሎት በጣም ዘዴኛ የሆኑ ወንድሞችና እህቶች በወንድማማችነት ዝምድናቸው ረገድ ዘዴኛ መሆን የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የሚዘነጉበት ጊዜ አለ። በይሖዋ ድርጅት ውስጥ የፍቅርና የአንድነት መንፈስ ለመገንባትና ጥሩ የሆነ የዕለት ተዕለት ግንኙነት እንዲኖር ጨዋነትና እርጋታ የተሞላበት አነጋገርና ድርጊት ያስፈልጋል። ጳውሎስ “ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ” ብሏል። — ገላ. 6:10
10 ስለ ወንድሞቻችን በተለይም ስለ መንፈሳዊነታቸው አጥብቀን እናስባለን። ምክንያቱም ሁላችንም የይሖዋ ድርጅት አባሎች ነን። (ፊልጵ. 2:2, 4) ይሁን እንጂ ዘዴኛ የሆነ ሰው ስለ ወንድሞቹ ሁኔታ ለማወቅ ቢፈልግም በግል ጉዳያቸው ውስጥ እየገባ ስለማይመለከተው ጉዳዮች መጠየቅ እንደማይገባው ይገነዘባል። ዘዴኛ መሆን “በሌሎች ጉዳይ” ከመግባት ይጠብቀናል። — 1 ጴጥ. 4:15
11. በጉባኤ ውስጥ ያሉ አገልጋዮች ዘዴኛ መሆን እንደሚያስፈልጋቸው ቅዱሳን ጽሑፎች የሚያሳዩት እንዴት ነው?
11 በተለይ የጉባኤ ኃላፊነት ያላቸው ወንድሞች ዘዴኛ መሆን ያስፈልጋቸዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስ በተሳሳተ አካሄድ ላይ ለሚገኙ የጉባኤ አባሎች ሊያደርግ ስለሚገባው አያያዝ መምሪያ ሲሰጠው ረጋ ማለትና ደግ መሆን እንደሚያስፈልገው አጠንክሮ ጽፎለታል። “የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር ለማስተማርም የሚበቃ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም። . . . ወደ አእምሮ ይመለሳሉ ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ።” (2 ጢሞ. 2:24–26) ሐዋርያው በተመሳሳይ ሳያውቀው በተሳሳተ መንገድ ውስጥ የወደቀን ሰው በሚያነጋግርበት ጊዜ ‘የየዋህነት መንፈስ’ ማሳየት ይገባል የሚል ምክር ሰጥቷል። (ገላ. 6:1) አገልጋዮች እንዲህ ያለውን ሰው በሚመክሩበት ጊዜ ዘዴኞችና ለጽድቅ ሥርዓቶች ጥብቅ መሆን ይገባቸዋል።
12, 13. በቤታችን ውስጥም ዘዴኛ አያያዝ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው?
12 ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ረገድ ሊኖረን የሚገባው የዘዴኛነት አያያዝ በቤተሰብ ክልል ውስጥ ያሉትንም የሚጨምር መሆን አለበት። በቤተሰባችን ውስጥ ያሉትን በደንብ ስለምናውቃቸው ብቻ መዳፈር 1 ጴጥ. 3:1, 2
ወይም ደግነት በጎደለው መንገድ መናገር አይገባንም። እነርሱም ቢሆኑ በዘዴ መያዝ ይኖርባቸዋል። የመዳፈር ወይም የሽሙጥ ወይም ሸካራ ንግግር ቢነገራቸው ይከፋሉ። የቤተሰብ አባሎች የይሖዋ አገልጋዮች ባይሆኑ ዘዴኛነት በጎደለው መንገድ ማነጋገር እንችላለን ማለት ነውን? በፍጹም አይደለም፤ ምክንያቱም የማያምኑትን ሰዎች በዘዴ መያዝ አንድ ቀን እውነተኛ አምልኮን እንዲቀበሉ ሊያደርጋቸው ይችላል። —13 ቲኦክራሲያዊ ዘዴ መጠቀማችን ከሕዝብ ጋር፣ ከመንፈሳዊ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንም ጋር ይሁን ከቤተሰባችን ጋር ባለን ግንኙነት ሁሉ ብዙ ጥሩ ፍሬ ያስገኝልናል። ምሳሌ 16:24 ላይ እንደተገለጸውም ሰሚዎችን ያስደስታል። “ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፣ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።” እንግዲያው የምታገኘውን ሁሉ ለመጥቀም ባለህ ጠንካራ ፍላጎት ተነሳስተህ የዘዴኛነትን አያያዝ አዳብር።
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]