በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 16ለ

ማዘንና መቃተት፣ ምልክት ማድረግ፣ ማጥፋት—መቼና እንዴት?

ማዘንና መቃተት፣ ምልክት ማድረግ፣ ማጥፋት—መቼና እንዴት?

በሕዝቅኤል ምዕራፍ 9 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ራእይ በዘመናችንም ፍጻሜውን ያገኛል። በትንቢቱ ላይ የተገለጹት ነገሮች እንዴት እንደሚፈጸሙ መረዳታችን የዚህን ሥርዓት ፍጻሜ በልበ ሙሉነት እንድንጠባበቅ ይረዳናል

“ማዘንና መቃተት”

መቼ፦ በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ፣ ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት

እንዴት፦ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች በዓለም ላይ ለሚፈጸመው ክፋት ያላቸውን ጥላቻ በቃልም ሆነ በድርጊት ያሳያሉ። እነዚህ ሰዎች ለስብከቱ ሥራ አዎንታዊ ምላሽ ይሰጣሉ፤ ክርስቶስን ለመምሰል ጥረት ያደርጋሉ፤ ራሳቸውን ለይሖዋ ወስነው ይጠመቃሉ እንዲሁም የክርስቶስን ወንድሞች በታማኝነት ይደግፋሉ

“ምልክት ማድረግ”

መቼ፦ በታላቁ መከራ ወቅት

እንዴት፦ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው በሕዝቦች ሁሉ ላይ ለመፍረድ የሚመጣውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይወክላል። የእጅግ ብዙ ሕዝብ አባላት ‘በጎች ናችሁ’ ተብለው ይፈረድላቸዋል ወይም ምልክት ይደረግባቸዋል፤ ይህም ከአርማጌዶን እንደሚተርፉ ያመለክታል

“ማጥፋት”

መቼ፦ በአርማጌዶን ጦርነት ወቅት

እንዴት፦ ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክትንና አብረውት የሚገዙትን 144,000 ቅቡዓን ያቀፈውን ሰማያዊ ሠራዊቱን በማሰለፍ ይህን ክፉ ዓለም ሙሉ በሙሉ ካጠፋ በኋላ ከንጹሕ አምልኮ ጎን የቆሙትን ሰዎች ጽድቅ ወደሚሰፍንበት አዲስ ዓለም ያስገባቸዋል