በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 19ለ

ቀስ እያለ የሚፈሰው ውኃ ትልቅ ወንዝ ሆነ!

ቀስ እያለ የሚፈሰው ውኃ ትልቅ ወንዝ ሆነ!

ሕዝቅኤል ከይሖዋ ቤተ መቅደስ ወጥቶ ቀስ እያለ የሚፈስ ውኃ በአስደናቂ ሁኔታ እየጨመረ ሄዶ ሁለት ኪሎ ሜትር በማይሞላ ርቀት ውስጥ ትልቅ ወንዝ ሲሆን ተመለከተ። በወንዙ ዳርና ዳር ለመብልና ለመድኃኒት የሚሆኑ ዛፎች አሉ። የዚህ ሁሉ ትርጉም ምንድን ነው?

በረከት የሚያስገኝ ወንዝ

በጥንት ዘመን፦ ግዞተኞቹ ወደ ትውልድ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ በቤተ መቅደሱ የሚከናወነውን ንጹሕ አምልኮ መልሶ በማቋቋሙ ሥራ ሲካፈሉ የይሖዋ በረከት ይፈስላቸው ነበር

በዘመናችን፦ በ1919 ንጹሕ አምልኮ መልሶ ሲቋቋም ከዚያ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መጠን ለአምላክ ታማኝ አገልጋዮች መንፈሳዊ በረከት የሚፈስበት መንገድ ተከፈተ

ወደፊት፦ ከአርማጌዶን በኋላ የይሖዋ በረከት መንፈሳዊም ሆነ አካላዊ ጥቅም ያስገኛል

ሕይወት ሰጪ ውኃ

በጥንት ዘመን፦ ይሖዋ ታዛዥ የሆኑ ሕዝቦቹን በመንፈሳዊ ሕያው እንዲሆኑና ጥሩ ሕይወት እንዲመሩ በማድረግ አብዝቶ ባርኳቸዋል

በዘመናችን፦ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሰዎች፣ በመንፈሳዊው ገነት ውስጥ በብዛት እየፈሰሰ ያለውን የይሖዋን በረከት ማግኘትና በመንፈሳዊ ሕያው መሆን ችለዋል

ወደፊት፦ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞት ተነስተው አርማጌዶንን በሕይወት ካለፉ ሰዎች ጋር በገነት ይኖራሉ፤ የይሖዋ በረከት ለሁሉም ተትረፍርፎ ይፈስላቸዋል

ለመብልና ለመድኃኒት የሚሆኑ ዛፎች

በጥንት ዘመን፦ ይሖዋ ከግዞት የተመለሱ ታማኝ ሕዝቦቹን በመንፈሳዊ መግቧቸዋል፤ እንዲሁም ለረጅም ዘመናት ሲያሠቃያቸው ከቆየው መንፈሳዊ ሕመም ፈውሷቸዋል

በዘመናችን፦ በተትረፈረፈ ሁኔታ የሚቀርበው መንፈሳዊ ምግብ ብዙ ሰዎች በዛሬው ጊዜ ያለውን ዓለም ቀስፎ የያዘውን መንፈሳዊ ሕመምና ረሃብ እንዲቋቋሙ አስችሏቸዋል

ወደፊት፦ ክርስቶስና አብረውት የሚገዙት 144,000 ቅቡዓን፣ ታዛዥ የሰው ልጆች ወደ ፍጽምና እንዲደርሱ እንዲሁም ለዘላለም ጤናማና ጠንካራ ሆነው እንዲኖሩ ይረዷቸዋል!