ሣጥን 9ሠ
“ነገሮች ሁሉ የሚታደሱበት ዘመን”
የሐዋርያት ሥራ 3:21
ሐዋርያው ጴጥሮስ “ነገሮች ሁሉ የሚታደሱበት ዘመን” ሲል ክርስቶስ ከነገሠበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሺው ዓመት ማብቂያ ድረስ ስለሚዘልቅ አስደናቂ ዘመን በትንቢት መናገሩ ነበር።
-
1914—ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ። የአምላክን ሕዝቦች በመንፈሳዊ ሁኔታ መልሶ የማቋቋሙ ሥራ በ1919 ጀመረ
የመጨረሻዎቹ ቀናት
-
አርማጌዶን—የክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ይጀምራል፤ ‘ነገሮች ሁሉ በሚታደሱበት ዘመን’ ውስጥ በሚካተተው በዚህ ወቅት ምድር ቃል በቃል ትታደሳለች፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ታማኝ የሰው ልጆችም ሥጋዊ በረከቶችን ያገኛሉ
የሺህ ዓመት ግዛት
-
የሺው ዓመት ግዛት ፍጻሜ—ኢየሱስ የማደሱን ወይም መልሶ የማቋቋሙን ሥራ አጠናቅቆ መንግሥቱን ለአባቱ ያስረክባል
ዘላለማዊ ገነት
በኢየሱስ አገዛዝ ሥር . . .
-
የአምላክ ስም ክብር ይጎናጸፋል
-
የታመሙ ጤንነታቸው ይመለሳል
-
አረጋውያን ወደ ወጣትነት ይመለሳሉ
-
ሙታን ዳግመኛ ሕያው ይሆናሉ
-
ታማኝ የሰው ልጆች ፍጹም ይሆናሉ
-
ምድር ገነት ትሆናለች