በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 20ሀ

የምድሪቱ አከፋፈል

የምድሪቱ አከፋፈል

የምድሪቱ ወሰኖች ልኬት በዝርዝር መገለጹ ግዞተኞቹ የሚወዷት አገራቸው ተመልሳ እንደምትቋቋም እርግጠኛ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ዛሬስ ከዚህ ራእይ ምን ትምህርት እናገኛለን? የራእዩን ሁለት ገጽታዎች እስቲ እንመልከት፦

የተረጋገጠ ቦታና ትልቅ ግምት የሚሰጠው የሥራ ድርሻ

ራእዩ ከግዞት የሚመለሱት እስራኤላውያን በሙሉ ተመልሳ በምትቋቋመው ተስፋይቱ ምድር ውስጥ ርስት እንደሚያገኙ ያመለክት ነበር። ዛሬም በተመሳሳይ ሁሉም የይሖዋ አገልጋዮች በመንፈሳዊው ገነት ውስጥ ቦታ አላቸው። በድርጅቱ ውስጥ የምናበረክተው አስተዋጽኦ ምንም ያህል አነስተኛ ቢሆን፣ በመንፈሳዊው ገነት ውስጥ የተረጋገጠ ቦታና ከፍ ያለ ግምት የሚሰጠው የሥራ ድርሻ አለን። ሁሉም የይሖዋ አገልጋዮች በእሱ ፊት በእኩል ደረጃ ውድ ናቸው።

እኩል ድርሻ

በሕዝቅኤል ራእይ መሠረት፣ በሁሉም ነገዶች ርስት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ምድሪቱ ከምታስገኘው የተትረፈረፈ ምርት በእኩል መጠን ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። ዛሬም በተመሳሳይ ይሖዋ አገልጋዮቹ በሙሉ መንፈሳዊው ገነት ከሚያስገኛቸው በረከቶች በእኩል ደረጃ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።