በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 13ሀ

የተለያዩ ቤተ መቅደሶች፣ የተለያዩ ትምህርቶች

የተለያዩ ቤተ መቅደሶች፣ የተለያዩ ትምህርቶች

ሕዝቅኤል በራእይ ያየው ቤተ መቅደስ፦

  • ሕዝቅኤል በባቢሎን ለነበሩ አይሁዳውያን ግዞተኞች ስለዚህ ቤተ መቅደስ ተናግሯል

  • ብዙ መሥዋዕቶች የሚቀርቡበት መሠዊያ አለው

  • ይሖዋ ለንጹሕ አምልኮ ያወጣውን መሥፈርት ጎላ አድርጎ ይገልጻል

  • ትኩረታችን በ1919 በጀመረው መንፈሳዊ ተሃድሶ ላይ እንዲያርፍ ያደርጋል

ታላቁ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ፦

  • ጳውሎስ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ አብራርቶታል

  • አንድ መሥዋዕት ብቻ “ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ” የቀረበበት መሠዊያ አለው (ዕብ. 10:10)

  • የማደሪያ ድንኳኑና ሌሎቹ ቤተ መቅደሶች ጥላ የሆኑለትን መንፈሳዊ እውነታ ማለትም ይሖዋ በክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት ለንጹሕ አምልኮ ያደረገውን ዝግጅት ያመለክታል

  • ትኩረታችን ክርስቶስ ታላቅ ሊቀ ካህናት በመሆን ከ29 እስከ 33 ዓ.ም. ባከናወነው ሥራ ላይ እንዲያርፍ ያደርጋል