በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 10ለ

‘በደረቁት አጥንቶች’ እና ‘በሁለቱ ምሥክሮች’ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?

‘በደረቁት አጥንቶች’ እና ‘በሁለቱ ምሥክሮች’ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?

በ1919 ሁለት ተዛማጅ የሆኑ ትንቢቶች ማለትም ‘ስለደረቁት አጥንቶች’ እና ‘ስለ ሁለቱ ምሥክሮች’ የሚናገሩት ራእዮች ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል። ‘ስለደረቁት አጥንቶች’ የሚገልጸው ራእይ ረጅም ጊዜ (በርካታ መቶ ዘመናት) የሚሸፍን ሲሆን ይህ ጊዜ የሚያበቃው እጅግ ብዙ የሆኑ የአምላክ ሕዝቦች ወደ ሕይወት ሲመለሱ ነው። (ሕዝ. 37:2-4፤ ራእይ 11:1-3, 7-13) ስለ ‘ሁለቱ ምሥክሮች’ የሚናገረው ትንቢት ደግሞ አጭር ጊዜ (ከ1914 መገባደጃ እስከ 1919 መጀመሪያ) የሚሸፍን ሲሆን ይህ ጊዜ የሚያበቃው ጥቂት የአምላክ አገልጋዮችን ያቀፈ ቡድን ወደ ሕይወት ሲመለስ ነው። ሁለቱም ትንቢቶች ምሳሌያዊ የሆነን ትንሣኤ የሚያመለክቱ ናቸው፤ እንዲሁም ሁለቱም ትንቢቶች ይሖዋ በ1919 ቅቡዓን አገልጋዮቹ ‘በእግራቸው እንዲቆሙ፣’ ከታላቂቱ ባቢሎን ምርኮ ነፃ እንዲወጡና መልሶ በተቋቋመው ጉባኤ ውስጥ እንዲሰበሰቡ ባደረገበት ጊዜ ዘመናዊ ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል።—ሕዝ. 37:10

ይሁን እንጂ በሁለቱ ትንቢቶች ፍጻሜ መካከል አንድ ወሳኝ ልዩነት እንዳለ ልብ ማለት ያስፈልጋል። ‘ስለደረቁት አጥንቶች’ የሚናገረው ትንቢት የሚተነብየው ሁሉም ቅቡዓን ቀሪዎች ወደ ሕይወት ስለመመለሳቸው ነው። ስለ ‘ሁለቱ ምሥክሮች’ የሚናገረው ትንቢት ግን የሚተነብየው ጥቂት ቅቡዓን ቀሪዎች ማለትም በድርጅቱ ውስጥ ግንባር ቀደም ሆነው ሥራውን ይመሩ የነበሩትና “ታማኝና ልባም ባሪያ” ሆነው የተሾሙት ቅቡዓን ወደ ሕይወት ስለመመለሳቸው ነው።—ማቴ. 24:45፤ ራእይ 11:6 *

‘በአጥንቶች የተሞላ ሸለቆ’​—ሕዝ. 37:1

  1. ከ100 ዓ.ም. በኋላ

    በሁለተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. የቅቡዓን ክርስቲያኖች ጉባኤ በምሳሌያዊ ሁኔታ ከተገደለ ወዲህ ‘ሸለቆው በአጥንቶች ተሞልቷል’

  2. 1919 መጀመሪያ

    1919፦ የደረቁት አጥንቶች ሕያው ሆኑ፤ ይህ የሆነው ይሖዋ ሁሉም ቅቡዓን ክርስቲያኖች ከታላቂቱ ባቢሎን ወጥተው መልሶ በተቋቋመው ጉባኤ ውስጥ እንዲሰበሰቡ ባደረገበት ወቅት ነው

‘ሁለት ምሥክሮች’​—ራእይ 11:3

  1. 1914 መገባደጃ

    ‘ማቅ ለብሶ’ መስበክ

    1914፦ ‘ሁለቱ ምሥክሮች’ ለሦስት ዓመት ተኩል “ማቅ ለብሰው” ሰብከዋል። በዚህ ጊዜ ማብቂያ ላይ በምሳሌያዊ ሁኔታ ተገደሉ

  2. ምሳሌያዊ ሞት

  3. 1919 መጀመሪያ

    1919፦ ‘ሁለቱ ምሥክሮች’ ሕያው ሆኑ፤ ይህ የሆነው በድርጅቱ ውስጥ ግንባር ቀደም ሆነው ሥራውን ይመሩ የነበሩትን ጥቂት ቅቡዓን ወንድሞች ያቀፈው ቡድን “ታማኝና ልባም ባሪያ” ሆኖ ሲሾም ነው

^ አን.4 በመጋቢት 2016 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን “የአንባቢያን ጥያቄዎች” የሚለውን ዓምድ ተመልከት።