በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 2ለ

ሕዝቅኤል—ያሳለፈው ሕይወትና የኖረበት ዘመን

ሕዝቅኤል—ያሳለፈው ሕይወትና የኖረበት ዘመን

ሕዝቅኤል የሚለው ስም “አምላክ ያበረታል” የሚል ትርጉም አለው። የተናገራቸው ትንቢቶች በርካታ ማስጠንቀቂያዎችን የያዙ ቢሆንም የሕዝቅኤል መጽሐፍ አጠቃላይ መልእክት ከስሙ ትርጉም ጋር የሚስማማ ሲሆን ለአምላክ ንጹሕ አምልኮ ማቅረብ የሚፈልጉ ሰዎችን እምነት ያጠናክራል።

በዘመኑ የነበሩ ሌሎች ነቢያት

  • ኤርምያስ

    ከካህናት ቤተሰብ የመጣ ሲሆን በአብዛኛው ያገለገለው በኢየሩሳሌም ነበር (647-580 ዓ.ዓ.)

  • ሕልዳና

    የሕጉ መጽሐፍ በ642 ዓ.ዓ. በቤተ መቅደሱ ውስጥ በተገኘበት ወቅት ነቢዪት ሆና ታገለግል ነበር

  • ዳንኤል

    የነገሥታት ነገድ የሆነው የይሁዳ ነገድ አባል ሲሆን በ617 ዓ.ዓ. ወደ ባቢሎን ተወስዷል

  • ዕንባቆም

    በኢዮዓቄም ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ሳይሆን አይቀርም በይሁዳ ያገለግል ነበር

  • አብድዩ

    በኤዶም ላይ ትንቢት ተናግሯል፤ ይህ የሆነው ኢየሩሳሌም በጠፋችበት ጊዜ ሳይሆን አይቀርም

ትንቢት የተናገሩት መቼ ነበር? (ዓ.ዓ.)

ሕዝቅኤል በኖረበት ዘመን የተፈጸሙ ጉልህ ክንውኖች (ዓ.ዓ.)

  1. 643 ገደማ፦ ተወለደ

  2. 617፦ በግዞት ወደ ባቢሎን ተወሰደ

  3. 613፦ ትንቢት መናገር ጀመረ፤ ይሖዋን በራእይ ተመለከተ

  4. 612፦ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚፈጸመውን ክህደት በራእይ ተመለከተ

  5. 611፦ ኢየሩሳሌምን ማውገዝ ጀመረ

  6. 609፦ ሚስቱ ሞተች፤ የመጨረሻው የኢየሩሳሌም ከበባ ተጀመረ

  7. 607፦ ኢየሩሳሌም መጥፋቷን የሚገልጽ ዜና ደረሰው

  8. 593፦ ቤተ መቅደሱን በራእይ ተመለከተ

  9. 591፦ ናቡከደነጾር ግብፅን እንደሚወር ተነበየ፤ መጽሐፉን ጽፎ አጠናቀቀ

የይሁዳና የባቢሎን ነገሥታት

  1. 659-629፦ ኢዮስያስ ንጹሕ አምልኮ እንዲስፋፋ አደረገ፤ ሆኖም ከፈርዖን ኒካዑ ጋር ባደረገው ውጊያ ተገደለ

  2. 628፦ ኢዮዓካዝ ለሦስት ወር በመጥፎ ሁኔታ ከገዛ በኋላ ፈርዖን ኒካዑ ይዞ አሰረው

  3. 628-618፦ ክፉው ንጉሥ ኢዮዓቄም የፈርዖን ኒካዑ ገባር ንጉሥ ሆነ

  4. 625፦ ናቡከደነጾር የግብፅን ሠራዊት ድል አደረገ

  5. 620፦ ናቡከደነጾር ይሁዳን ለመጀመሪያ ጊዜ የወረረ ሲሆን ኢዮዓቄምን በኢየሩሳሌም ገባር ንጉሥ አድርጎ ሾመው

  6. 618፦ ኢዮዓቄም በናቡከደነጾር ላይ ዓመፀ፤ ሆኖም ባቢሎናውያን ተስፋይቱን ምድር ለሁለተኛ ጊዜ በወረሩበት ወቅት ሳይሆን አይቀርም ተገደለ

  7. 617፦ ክፉው ንጉሥ ዮአኪን (ኢኮንያን ተብሎም ይጠራል) ለሦስት ወር ያህል ከገዛ በኋላ ለናቡከደነጾር እጁን ሰጠ

  8. 617-607፦ ናቡከደነጾር ክፉና ወኔ ቢስ የሆነውን ሴዴቅያስን ገባር ንጉሥ አደረገው

  9. 609፦ ሴዴቅያስ በናቡከደነጾር ላይ ስላመፀ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ለሦስተኛ ጊዜ ወረረ

  10. 607፦ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ደመሰሳት፤ ሴዴቅያስንም በቁጥጥር ሥር ካዋለው በኋላ ዓይኑን አሳውሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው