በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል ሁለት

‘መቅደሴን አርክሰሻል’—ንጹሕ አምልኮ ተበከለ

‘መቅደሴን አርክሰሻል’—ንጹሕ አምልኮ ተበከለ

ሕዝቅኤል 5:11

ፍሬ ሐሳብ፦ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ለመንፈሳዊም ሆነ ለሥነ ምግባራዊ ብክለት ተዳረጉ

ይሖዋ እስራኤላውያን ‘ልዩ ንብረቶቹ’ ስለሆኑ ይወዳቸውና ይንከባከባቸው ነበር። (ዘፀ. 19:5) እነሱ ግን ስሙ በተጠራበት ቤተ መቅደስ ውስጥ የሐሰት አማልክትን በማምለክ ውለታ ቢስ መሆናቸውን አሳዩ። የይሖዋን ልብ በእጅጉ ያሳዘኑ ከመሆኑም ሌላ ስሙን አሰድበዋል። እስራኤላውያን እንዲህ ያለ ያዘቀጠ ድርጊት ሊፈጽሙ የቻሉት ለምንድን ነው? ሕዝቅኤል ስለ ኢየሩሳሌም ጥፋት ከተናገረው ትንቢት ምን እንማራለን? እስራኤላውያን በዙሪያቸው ካሉት ብሔራት ጋር ከነበራቸው ግንኙነትስ ምን ትምህርት እናገኛለን?

በዚህ ክፍል ውስጥ

ምዕራፍ 5

“የሚሠሯቸውን ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ተመልከት”

ሕዝቅኤል መላው ብሔር የደረሰበትን ያዘቀጠ መንፈሳዊ ሁኔታ የሚያሳዩ ትእይንቶችን ተመለከተ።

ምዕራፍ 6

“አሁን ፍጻሜሽ ደርሷል”

ሕዝቅኤል ያሳያቸው ትንቢታዊ ድራማዎች በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጣውን የይሖዋ ቁጣ የሚያሳዩ ናቸው።

ምዕራፍ 7

ብሔራት “እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ”

የይሖዋን ስም ያቃለሉትም ሆኑ ሕዝቡን ያሳደዱት ወይም የበከሉት ብሔራት የእጃቸውን ማግኘታቸው አይቀርም። እስራኤል ከእነዚህ ብሔራት ጋር ከነበራት ግንኙነት ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?