ክፍል ሦስት
‘እሰበስባችኋለሁ’—ንጹሕ አምልኮ መልሶ እንደሚቋቋም በትንቢት ተነገረ
ፍሬ ሐሳብ፦ በሕዝቅኤል ትንቢት ውስጥ የሚገኙ ንጹሕ አምልኮ መልሶ እንደሚቋቋም የሚገልጹ ተስፋዎች
በእስራኤል ውስጥ ክህደት ስለተስፋፋ አንድነቷ ክፉኛ ተናግቷል። እስራኤል ንጹሕ አምልኮን ያረከሰች ከመሆኑም ሌላ የአምላክን ስም አጉድፋለች፤ ስለዚህ ድርጊቷ ያስከተለባትን መዘዝ እየተቀበለች ነው። እንዲህ ባለው ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ይሖዋ ሕዝቅኤልን ተስፋ ሰጪ የሆኑ ትንቢቶችን እንዲናገር አነሳሳው። ይሖዋ ምስል ከሳች የሆኑ አገላለጾችንና አስደናቂ ራእዮችን በመጠቀም በግዞት ያሉትን እስራኤላውያን ብቻ ሳይሆን ንጹሕ አምልኮ መልሶ ሲቋቋም ማየት የሚናፍቁትን ሁሉ የሚያጽናና ሐሳብ አስነግሯል።
በዚህ ክፍል ውስጥ
ምዕራፍ 8
“አንድ እረኛ . . . አስነሳለሁ”
ይሖዋ ሕዝቅኤልን በመንፈሱ በመምራት ስለ መሲሑ ማለትም ንጹሕ አምልኮን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መልሶ ስለሚያቋቁመው እረኛና ገዢ ትንቢት እንዲናገር አድርጓል።
ምዕራፍ 14
“የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው”
በግዞት የነበሩት አይሁዳውያን ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ካየው ራእይ ምን ትምህርት አግኝተው መሆን አለበት? ይህ ራእይ እኛንስ ምን ያስተምረናል?