በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መከራ የማይኖርባት ምድር

መከራ የማይኖርባት ምድር

ክፍል 2

መከራ የማይኖርባት ምድር

1, 2. ብዙ ሰዎች ምን የተለየ አመለካከት አላቸው?

ይሁን እንጂ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ፈጽሞ የተለየ አመለካከት አላቸው። የወደፊቱ ጊዜ ለሰው ልጆች አስደናቂ እንደሚሆንላቸው ይታያቸዋል። እዚችው ምድር ላይ ከክፋትና ከመከራ ሙሉ በሙሉ ነፃ የሆነ ዓለም ይመጣል እያሉ ይናገራሉ። መጥፎ የሆነው ነገር በሙሉ በቅርቡ ተወግዶ አዲስ የሆነ ዓለም እንደሚቋቋም እርግጠኞች ናቸው። እንዲያውም ይህ አዲስ ዓለም አሁንም እንኳን መሠረቱ የተጣለ መሆኑን ይናገራሉ!

2 እነዚህ ሰዎች አዲሱ ዓለም ከጦርነት፣ ከጭካኔ፣ ከወንጀል፣ ከፍትሕ መዛባትና ከድህነት ነፃ እንደሚሆን ያምናሉ። ይህ መጪ ዓለም በሽታ፣ ኀዘን፣ እንባና ሞትም እንኳን ሳይቀር የማይኖርበት ዓለም ይሆናል። በዚያን ጊዜ ሰዎች ወደ ፍጽምና ደረጃ ይደርሱና በምድራዊ ገነት ለዘላለም በደስታ ይኖራሉ። የሞቱትም እንኳን ሳይቀሩ ትንሣኤ አግኝተው ለዘላለም የመኖር አጋጣሚ ሊኖራቸው ነው!

3, 4. እነዚህ ሰዎች ስለያዙት አመለካከት እርግጠኞች የሆኑት ለምንድን ነው?

3 የወደፊቱን ጊዜ እንደዚህ አድርጎ መመልከቱ እንዲሁ ቅዠትና የሕልም እንጀራ ብቻ ነውን? በፍጹም አይደለም። ይህ ገነት ወደፊት መምጣቱ የማይቀር ለመሆኑ ጠንካራ መሠረት ባለው እምነት ላይ የተመሠረተ ነው። (ዕብራውያን 11:1) ይህን ያህል እርግጠኞች የሆኑት ለምንድን ነው? ምክንያቱም ይህን ተስፋ የሰጠው ሁሉን ማድረግ የሚችለው የጽንፈ ዓለሙ ፈጣሪ ስለሆነ ነው።

4 የአምላክን ተስፋዎች በሚመለከት መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው ይላል:- “እናንተም እግዚአብሔር ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ ዕወቁ፤ ሁሉ ደርሶላችኋል፤ ከእርሱም አንድ ነገር አልቀረም።” “ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም . . . እርሱ ያለውን አያደርገውምን?” “የሠራዊት ጌታ [ይሖዋ አዓት] እንዲህ ብሎ ምሎአል:- እንደተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፣ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።”—ኢያሱ 23:14፤ ዘኁልቁ 23:19፤ ኢሳይያስ 14:24

5. የትኞቹ ጥያቄዎች መልስ ያስፈልጋቸዋል?

5 ይሁን እንጂ የአምላክ ዓላማ መከራ የሌለበት ምድራዊ ገነት ለማቋቋም ከሆነ መጀመሪያውኑ መጥፎ ነገሮች እንዲፈጸሙ የፈቀደው ለምንድን ነው? ብልሽቱን ለማስተካከል እስከ አሁን ድረስ ለስድስት ሺህ ዓመት የቆየውስ ለምንድን ነው? እነዚህ ያለፉት በመከራ የተሞሉ መቶ ዘመናት ሁሉ አምላክ በእርግጥ ስለ እኛ ምንም ደንታ እንደሌለው፤ እንዲያውም አምላክ እንደሌለ ያመለክቱ ይሆን?

[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]