በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይህን ብሮሹር መጠቀም የሚቻልበት መንገድ

ይህን ብሮሹር መጠቀም የሚቻልበት መንገድ

ይህን ብሮሹር መጠቀም የሚቻልበት መንገድ

ይህ ብሮሹር መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት እንዲረዳ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ታዲያ በዚህ ብሮሹር እንዴት መጠቀም ይቻላል? የሚከተለውን ፕሮግራም እንድትከተል ሐሳብ እናቀርባለን:- በእያንዳንዱ ትምህርት መጀመሪያ ላይ ጥያቄዎች ቀርበዋል። ከእያንዳንዱ ጥያቄ ጎን መልሶቹ የሚገኙበት አንቀጽ ቁጥር በቅንፍ ውስጥ ሰፍሮ ታገኛለህ። በመጀመሪያ ጥያቄዎቹን በሙሉ አንብብ። የጥያቄዎቹ መልስ ምን እንደሆነ አስብ። ከዚያም እያንዳንዱን አንቀጽ ካነበብክ በኋላ ጥቅሶቹን ከመጽሐፍ ቅዱስህ አውጥተህ ተመልከት። ትምህርቱን አንብበህ ስትጨርስ ወደ ጥያቄዎቹ ተመለስና መጽሐፍ ቅዱስ ለእያንዳንዱ ጥያቄ የሰጠውን መልስ ለማስታወስ ሞክር። ሙሉውን ብሮሹር ከጨረስክ በኋላ ወደ ኋላ ተመልሰህ ጥያቄዎቹን በሙሉ እንደገና ከልስ።