በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 3

ኢየሱስ በገሊላ ያከናወነው ታላቅ አገልግሎት

‘ኢየሱስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርቧል” እያለ ይሰብክ ጀመር።’—ማቴዎስ 4:17

ኢየሱስ በገሊላ ያከናወነው ታላቅ አገልግሎት

በዚህ ክፍል ውስጥ

ምዕራፍ 20

በቃና የፈጸመው ሁለተኛ ተአምር

ኢየሱስ የአንድን ባለሥልጣን ልጅ 26 ኪሎ ሜትር ገደማ ከሚሆን ርቀት ላይ ፈወሰው።

ምዕራፍ 21

በናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ

ኢየሱስ፣ ባደገበት ከተማ የነበሩት ሰዎች ሊገድሉት የሞከሩት ምን ስለተናገረ ነው?

ምዕራፍ 22

አራት ደቀ መዛሙርት ሰው አጥማጆች ሊሆኑ ነው

ዓሣ አጥማጆች የሆኑትን ደቀ መዛሙርቱን ለየት ያለ የማጥመድ ሥራ እንዲያከናውኑ ጠራቸው።

ምዕራፍ 23

ኢየሱስ በቅፍርናሆም ታላላቅ ሥራዎችን አከናወነ

ኢየሱስ አጋንንትን ሲያስወጣ የአምላክ ልጅ መሆኑን ለሰዎች እንዳይናገሩ ይከለክላቸው ነበር። ለምን?

ምዕራፍ 24

በገሊላ በስፋት ሰበከ

ሰዎች ፈውስ ለማግኘት ሲሉ ወደ ኢየሱስ መጡ፤ እሱ ግን አገልግሎቱ የላቀ ዓላማ እንዳለው ገለጸላቸው።

ምዕራፍ 25

በሥጋ ደዌ የተያዘን ሰው በርኅራኄ ፈወሰ

ኢየሱስ ያደረገው ቀላል የሚመስል ሆኖም ትልቅ ትርጉም ያለው ነገር ለሚፈውሳቸው ሰዎች ከልብ እንደሚያስብ ያሳያል።

ምዕራፍ 26

“ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል”

ኢየሱስ በኃጢአትና በበሽታ መካከል ምን ዝምድና እንዳለ አሳይቷል?

ምዕራፍ 27

ማቴዎስ ተጠራ

ኢየሱስ በኃጢአታቸው ከሚታወቁ ሰዎች ጋር የተመገበው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 28

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የማይጾሙት ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ስለ አቁማዳ ምሳሌ በመናገር መልስ ሰጥቷቸዋል።

ምዕራፍ 29

በሰንበት መልካም ሥራ መሥራት ይፈቀዳል?

ኢየሱስ ለ38 ዓመት ሕመምተኛ ሆኖ የኖረውን ሰው በመፈወሱ አይሁዳውያን ስደት ያደረሱበት ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 30

ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው

አይሁዳውያን ኢየሱስ ራሱን ከይሖዋ ጋር እኩል እንዳደረገ ቢሰማቸውም ኢየሱስ፣ አምላክ ከእሱ እንደሚበልጥ በግልጽ ተናግሯል።

ምዕራፍ 31

በሰንበት እሸት መቅጠፍ

ኢየሱስ “የሰንበት ጌታ” እንደሆነ የተናገረው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 32

በሰንበት የተፈቀደው ምንድን ነው?

በሌላ ጊዜ የማይስማሙት ሰዱቃውያን እና ፈሪሳውያን በአንድ ጉዳይ ላይ ግንባር ፈጠሩ።

ምዕራፍ 33

የኢሳይያስን ትንቢት መፈጸም

ኢየሱስ፣ የፈወሳቸውን ሰዎች ስለ ማንነቱ ወይም ስላደረጋቸው ነገሮች ለሌሎች እንዳይናገሩ ያዘዛቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 34

ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያት መረጠ

በሐዋርያ እና በደቀ መዝሙር መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

ምዕራፍ 35

ታዋቂው የተራራ ስብከት

ኢየሱስ በሰጠው ንግግር ላይ ያሉት ቁልፍ ነጥቦች ማብራሪያ።

ምዕራፍ 36

አንድ መቶ አለቃ ትልቅ እምነት አሳየ

ይህ የጦር መኮንን ያደረገው ነገር ኢየሱስን አስገርሞታል፤ ምን ይሆን ያደረገው?

ምዕራፍ 37

ኢየሱስ የአንዲት መበለትን ልጅ ከሞት አስነሳ

ይህን ተአምር የተመለከቱት ሰዎች ድርጊቱ ምን ትርጉም እንዳለው ስለተገነዘቡ በጣም ተደነቁ።

ምዕራፍ 38

ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ጥያቄ አቀረበ

መሲሑ ኢየሱስ መሆኑን መጥምቁ ዮሐንስ የጠየቀው ለምንድን ነው? ተጠራጥሮ ነው?

ምዕራፍ 39

መልእክቱን ለማይቀበል ትውልድ ወዮለት

ኢየሱስ፣ በፍርድ ቀን የአገልግሎቱ ማዕከል ከሆነችው ከቅፍርናሆም ይልቅ ለሰዶም እንደሚቀልላት ተናግሯል።

ምዕራፍ 40

ይቅርታ ስለ ማግኘት የተሰጠ ትምህርት

ኢየሱስ፣ ምናልባት ዝሙት አዳሪ ለሆነችው ሴት ኃጢአቷ ይቅር እንደተባለ ሲነግራት የአምላክን ሕግ መጣስ ስህተት እንዳልሆነ መግለጹ ነው?

ምዕራፍ 41

ተአምራት የፈጸመው በማን ኃይል ነው?

የኢየሱስ ወንድሞች፣ አእምሮውን እንደሳተ ተሰምቷቸው ነበር።

ምዕራፍ 42

ኢየሱስ ፈሪሳውያንን ገሠጻቸው

‘የነቢዩ ዮናስ ምልክት’ ምንድን ነው?

ምዕራፍ 43

ስለ መንግሥቱ የተነገሩ ምሳሌዎች

ኢየሱስ የመንግሥተ ሰማያትን ገጽታዎች ለማብራራት ስምንት ምሳሌዎች ተናገረ።

ምዕራፍ 44

ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ አሰኘው

ኢየሱስ ነፋሱንና ማዕበሉን ጸጥ በማሰኘት ወደፊት በመንግሥቱ ሥር ስለሚኖረው ሕይወት ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቷል።

ምዕራፍ 45

በአጋንንት ላይ ያለው ኃይል

በርካታ አጋንንት በአንድ ሰው ላይ ሊያድሩ ይችላሉ?

ምዕራፍ 46

የኢየሱስን ልብስ በመንካቷ ተፈወሰች

በዚህ ወቅት በተፈጸመው ልብ የሚነካ ሁኔታ ኢየሱስ ኃይሉንና ርኅራኄውን አሳይቷል።

ምዕራፍ 47

አንዲት ልጅ ከሞት ተነሳች!

ኢየሱስ፣ የሞተችው ልጅ ተኝታለች ሲል ሰዎቹ ሳቁበት። እነሱ የማያውቁት፣ እሱ ግን የሚያውቀው ምን ነገር አለ?

ምዕራፍ 48

ተአምራት ቢፈጽምም በናዝሬት እንኳ ተቀባይነት አላገኘም

የናዝሬት ሰዎች ኢየሱስን ያልተቀበሉት በትምህርቱ ወይም በፈጸማቸው ተአምራት የተነሳ ሳይሆን በሌላ ምክንያት ነው።

ምዕራፍ 49

በገሊላ መስበክና ሐዋርያቱን ማሠልጠን

‘መንግሥተ ሰማያት ቀርቧል’ ሲባል ምን ማለት ነው?

ምዕራፍ 50

ስደት ቢኖርም ለመስበክ መዘጋጀት

ኢየሱስ፣ ሞትን እንዳይፈሩ ለሐዋርያቱ የነገራቸው ቢሆንም ስደት ሲያጋጥማቸው እንዲሸሹ ያበረታታቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 51

በልደት ግብዣ ላይ የተፈጸመ ግድያ

የሰሎሜ ጭፈራ ሄሮድስን በጣም ስላስደሰተው የጠየቀችውን ማንኛውንም ነገር እንደሚሰጣት ቃል ገባላት። ያቀረበችው ጥያቄ ግን ዘግናኝ ነው፤ ምን ብላ ይሆን?

ምዕራፍ 52

በጥቂት ዳቦና ዓሣ ሺዎችን መመገብ

ኢየሱስ የፈጸመው ተአምር በጣም አስገራሚ በመሆኑ በአራቱም ወንጌሎች ላይ ሰፍሯል።

ምዕራፍ 53

የተፈጥሮ ኃይሎችን መቆጣጠር የሚችል ገዢ

ኢየሱስ በውኃ ላይ ሲራመድና ነፋሱን ጸጥ ሲያሰኝ ሐዋርያቱ ምን ትምህርት አገኙ?

ምዕራፍ 54

ኢየሱስ—“ሕይወት የሚያስገኘው ምግብ”

ሕዝቡ ወደ ኢየሱስ ለመምጣት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ኢየሱስ የወቀሳቸው ለምንድ ነው?

ምዕራፍ 55

የኢየሱስ ንግግር ብዙዎችን አስደነገጠ

ኢየሱስ የተናገረው ነገር በጣም የሚዘገንን በመሆኑ በርካታ ደቀ መዛሙርቱ ትተውት ሄዱ።

ምዕራፍ 56

ሰውን የሚያረክሰው ምንድን ነው?

ወደ አፉ የሚገባው ነው ወይስ ከአፉ የሚወጣው?

ምዕራፍ 57

ኢየሱስ አንዲትን ልጅና መስማት የተሳነውን ሰው ፈወሰ

ሴትየዋ፣ ኢየሱስ ሕዝቧን ከቡችሎች ጋር ሲያነጻጽራቸው ቅር ያልተሰኘችው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 58

ዳቦውን አበዛ፤ ስለ እርሾ አስጠነቀቀ

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት፣ ኢየሱስ ስለ እርሾ ሲናገር ምን ማለቱ እንደሆነ በኋላ ላይ ገባቸው።

ምዕራፍ 59

የሰው ልጅ ማን ነው?

የመንግሥቱ ቁልፎች ምንድን ናቸው? የሚጠቀምባቸው ማን ነው? የሚጠቀምባቸውስ እንዴት ነው?

ምዕራፍ 60

በተአምራዊ ሁኔታ ተለወጠ—ክርስቶስ በክብሩ ታየ

ኢየሱስ በተአምራዊ ሁኔታ የተለወጠው እንዴት ነው? የራእዩ ትርጉምስ ምንድን ነው?

ምዕራፍ 61

ኢየሱስ ጋኔን የያዘውን ልጅ ፈወሰ

ጋኔን የያዘውን ልጅ መፈወስ ያልተቻለው በእምነት ማነስ ምክንያት እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። እምነት ያነሰው ማን ነው? ልጁ፣ አባቱ ወይስ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት?

ምዕራፍ 62

ስለ ትሕትና የተሰጠ ጠቃሚ ትምህርት

አዋቂ ወንዶች ከትናንሽ ልጆች ጠቃሚ ትምህርት አገኙ።

ምዕራፍ 63

ኢየሱስ ማሰናከልንና ኃጢአትን በተመለከተ ምክር ሰጠ

በወንድሞች መካከል ከባድ አለመግባባት ቢፈጠር ሊወሰዱ የሚገባቸውን ሦስት እርምጃዎች ገለጸ።

ምዕራፍ 64

ይቅር ባይ የመሆን አስፈላጊነት

ኢየሱስ፣ ይቅር ባይ ያልሆነውን ባሪያ ምሳሌ በመጠቀም አምላክ ሌሎችን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ መሆናችንን ምን ያህል አክብዶ እንደሚመለከተው ገልጿል።

ምዕራፍ 65

ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዝ የሰጠው ትምህርት

ኢየሱስ፣ አንድ ሰው የእሱ ተከታይ እንዳይሆን እንቅፋት ሊሆኑበት የሚችሉ አመለካከቶችን ከሦስት ሰዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ገልጿል።