በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለከሳሾቹ መልስ ሰጠ

ለከሳሾቹ መልስ ሰጠ

ምዕራፍ 30

ለከሳሾቹ መልስ ሰጠ

የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች ኢየሱስን የሰንበትን ሕግ ጥሰሃል ብለው በከሰሱት ጊዜ “አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ” ብሎ መለሰላቸው።

ምንም እንኳ ፈሪሳውያን ቢወነጅሉትም ኢየሱስ ያደረገው ነገር በሰንበት ሕግ ከተከለከሉት ሥራዎች የሚመደብ አይደለም። የመስበክና የመፈወስ ሥራው አምላክ እንዲያከናውነው የሰጠው ሥራ ነው። የአምላክን ምሳሌ በመከተል ሥራውን በየዕለቱ ያከናውን ነበር። ይሁን እንጂ አይሁዶች የሰጣቸው መልስ ከበፊቱ ይበልጥ አናደዳቸው፤ ሊገድሉትም ፈለጉ። ለምን ይሆን?

አሁን ሊገድሉት የፈለጉት የሰንበትን ሕግ ጥሷል የሚል አስተሳሰብ ስላደረባቸው ብቻ ሳይሆን የአምላክ ልጅ ነኝ ብሎ በመናገር አምላክን ሰድቧል ብለው ስላሰቡ ጭምር ነበር። ይሁን እንጂ ኢየሱስ የፍርሃት ስሜት አላደረበትም። ከአምላክ ጋር ስላለው ውድ ዝምድና ተጨማሪ መልስ ሰጣቸው። “አብ ወልድን ይወዳልና፣ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል” አላቸው።

ኢየሱስ በመቀጠል “አብ ሙታንን እንደሚያነሣ” አለ፤ “እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።” በእርግጥም ወልድ በመንፈሣዊ ሁኔታ ሙታንን እያስነሳ ነበር! ኢየሱስ ‘ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን ከሞት ወደ ሕይወት ተሻግሯል’ አላቸው። በመቀጠልም እንዲህ ብሏል:- “ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።”

ምንም እንኳ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ኢየሱስ ቃል በቃል ከሞት ያስነሳው ሰው ስለመኖሩ የሚናገር ታሪክ ባይኖርም ቃል በቃል የሙታን ትንሣኤ እንደሚፈጸም ለከሳሾቹ ነግሯቸዋል። “በመታሰቢያ መቃብር ያሉት ሁሉ ድምፁን ሰምተው የሚወጡበት ሰዓት ይመጣልና በዚህ አትደነቁ” አላቸው።​—NW

እስከዚህ ጊዜ ድረስ ኢየሱስ በአምላክ ዓላማ ውስጥ የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና በሕዝብ ፊት እንዲህ ግልጽና ጉልህ በሆነ መንገድ ተናግሮ አያውቅም ነበር። ሆኖም የኢየሱስ ከሳሾች ከእርሱም ሌላ ስለ እነዚህ ነገሮች ምሥክርነት የሰጣቸው ሰው ነበር። “እናንተ ወደ ዮሐንስ ልካችኋል እርሱም ለእውነት መስክሮአል” ሲል ኢየሱስ ወደ ኋላ መለስ ብሎ አስታውሷቸዋል።

ከሁለት ዓመት በፊት አጥማቂው ዮሐንስ ከእሱ በኋላ ስለሚመጣው ሰው ለእነዚህ የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች ነግሯቸው ነበር። ኢየሱስ እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች በእስር ላይ ለሚገኘው ለዮሐንስ በአንድ ወቅት የነበራቸውን ከፍ ያለ ግምት እንዲያስታውሱ በማድረግ “እናንተም ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ” አላቸው። ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች እንዲያስታውሱ ያደረገው እነርሱን ለመርዳትና ለማዳን ነበር። ሆኖም ዮሐንስ በሰጠው ምሥክርነት ብቻ አልተመካም።

“ይህ የማደርገው ሥራ፣ [በዚያው ወቅት የፈጸመውን ተአምር ጨምሮ] አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራል።” ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ “የላከኝ አብም እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል” ሲል ተናገረ። ለምሳሌ ያህል ኢየሱስ በተጠመቀበት ጊዜ አምላክ “የምወደው ልጄ ይህ ነው” ሲል ስለ ኢየሱስ መስክሮአል።

በእርግጥም የኢየሱስ ከሳሾች እሱን አንቀበልም የሚሉበት ምንም ምክንያት አልነበራቸውም። እንመረምራቸዋለን የሚሏቸው ቅዱሳን ጽሑፎች እንኳ ስለ እርሱ ይመሰክራሉ! ኢየሱስ እንዲህ ሲል ደመደመ:- “ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና። መጻሕፍትን ካላመናችሁ ግን ቃሌን እንዴት ታምናላችሁ?” ዮሐንስ 5:​17-47፤ 1:​19-27፤ ማቴዎስ 3:​17

▪ የኢየሱስ ሥራ ከሰንበት ሕግ ጋር የማይቃረነው ለምንድን ነው?

▪ ኢየሱስ በአምላክ ዓላማ ውስጥ የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና የገለጸው እንዴት ነው?

▪ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ መሆኑን ለማስረዳት ማን የሰጠውን ምሥክርነት ጠቅሷል?