በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ኢየሱስ ተወለደ—የትና መቼ?

ኢየሱስ ተወለደ—የትና መቼ?

ምዕራፍ 5

ኢየሱስ ተወለደ—የትና መቼ?

የሮማ ግዛት ንጉሠ ነገሥት የነበረው አውግስጦስ ቄሣር እያንዳንዱ ሰው ይመዘገብ ዘንድ ወደ ትውልድ ከተማው እንዲመለስ ትእዛዝ አወጣ። ስለዚህ ዮሴፍ ወደ ትውልድ ቦታው ወደ ቤተ ልሔም ተጓዘ።

ለመመዝገብ ወደ ቤተ ልሔም የመጡ ብዙ ሰዎች ስለነበሩ ዮሴፍና ማርያም በአንድ ጋጥ ውስጥ ከማረፍ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም። ኢየሱስ የተወለደው በዚህ የአህዮችና የሌሎች እንስሳት ማደሪያ ውስጥ ነበር። ማርያም በጨርቅ ጠቀለለችውና የእንስሳቱ ምግብ በሚቀመጥበት ግርግም ላይ አስተኛችው።

አውግስጦስ ቄሣር ሕዝቡ እንዲመዘገብ የሚያዝ ሕግ እንዲያወጣ ያደረገው አምላክ እንደሆነ አያጠራጥርም። ይህም ይመጣል ተብሎ የተስፋ ቃል የተሰጠበት ገዢ በዚህች ከተማ ይወለዳል ብለው ቅዱሳን ጽሑፎች ከብዙ ዘመናት በፊት በትንቢት በተናገሩት መሠረት ኢየሱስ በቤተ ልሔም ከተማ እንዲወለድ ሁኔታውን አመቻችቷል።

ይህ ትልቅ ነገር የተፈጸመበት ሌሊት ነበር! ውጪ በሜዳ ላይ ተሰብስበው በነበሩ እረኞች ዙሪያ አንድ ደማቅ ብርሃን አንጸባረቀ። ይህ ብርሃን የይሖዋ ክብር ነበር! የይሖዋም መልአክ እንዲህ አላቸው:- “እነሆ፣ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።” በድንገት ሌሎች ብዙ መላእክት ተገለጡና “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ” ብለው ዘመሩ።

መላእክቱ ሲሄዱ እረኞቹ እንዲህ ሲሉ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ:- “እንግዴህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።” በፍጥነት ሄዱና ኢየሱስን መልአኩ በነገራቸው ቦታ አገኙት። እረኞቹ መልአኩ ምን እንዳላቸው ሲነግሯቸው የሰሙት ሰዎች ሁሉ ተደነቁ። ማርያም ይህን የሚባለውን ነገር ሁሉ በልቧ ይዛ ትጠብቀው ነበር።

በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ የተወለደው ታኅሣሥ 25 ቀን (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ታኅሣሥ 29 ቀን) ነው ብለው ያምናሉ። ሆኖም በቤተ ልሔም ታኅሣሥ ዝናብና ቅዝቃዜ ያለበት ወቅት ነው። በዚያ ወቅት ላይ ሌሊት እረኞች ከመንጎቻቸው ጋር በሜዳ አያድሩም ነበር። በተጨማሪም የሮማው ቄሣር በወቅቱ በእሱ ላይ ለማመፅ ይዳዱ የነበሩትን እነዚህን ሰዎች በጣም በሚቀዘቅዘው የክረምት ወቅት ለመመዝገብ እንዲሄዱ አያዛቸውም ነበር። ኢየሱስ የተወለደው በመከር ወራት (መስከረም​— ኅዳር) መጀመሪያ አካባቢ እንደነበረ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። ሉቃስ 2:​1-20፤ ሚክያስ 5:​2

▪ ዮሴፍና ማርያም ወደ ቤተ ልሔም የሄዱት ለምን ነበር?

▪ ኢየሱስ በተወለደበት ሌሊት ምን አስደናቂ ነገር ተፈጽሟል?

▪ ኢየሱስ ታኅሣሥ 25 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ታኅሣሥ 29) እንዳልተወለደ እንዴት እናውቃለን?