በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለሥራው የገንዘብ ድጋፍ የሚገኘው በፈቃደኛነት ከሚሰጥ መዋጮ ነው

ለሥራው የገንዘብ ድጋፍ የሚገኘው በፈቃደኛነት ከሚሰጥ መዋጮ ነው

ለሥራው የገንዘብ ድጋፍ የሚገኘው በፈቃደኛነት ከሚሰጥ መዋጮ ነው

ቀደም ሲል የተገለጸው ሥራ በሙሉ የሚከናወነው በፈቃደኛ ሠራተኞች ነው። ይህም ለሥራው የሚያስፈልገውን ወጪ ቀንሶታል። ከቤት ወደ ቤት የሚደረገው አገልግሎትና ጽሑፍ የማደል ሥራ የሚከናወነው የይሖዋ ምሥክሮች በሚሰጡት የፈቃደኝነት አገልግሎት ነው። ለሥራው የሚያስፈልጋቸውን ወጪ የሚሸፍኑት ራሳቸው ናቸው። በዲያቆናት እየታገዙ ጉባኤውን የሚያስተዳድሩት ሽማግሌዎች ለሚሰጡት አገልግሎት ምንም ዓይነት ክፍያ አይሰጣቸውም። ወጪያቸውን ራሳቸው ይችላሉ።

የአስተዳደር አካሉ አባሎችና ሌሎች በመጽሐፍ ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች ዝግጅትና ሕትመት ሥራ በሙሉ ጊዜያቸው የሚሠሩ ሁሉ ከመኝታና ከምግብ እንዲሁም ለግል ወጪ መተኪያ ከሚሰጣቸው መጠነኛ ገንዘብ በስተቀር ምንም ነገር አያገኙም። የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የሆኑት ተጓዥ የበላይ ተመልካቾችም ሁኔታ እንደዚያው ነው።

ለጽሑፎች የሚከፈለው መጠነኛ መዋጮ አብዛኛውን ጊዜ የጥሬ ዕቃዎችን፣ የማምረቻና የመላኪያ መሠረታዊ ወጪዎች ከመሸፈን አያልፍም። ሌሎች ወጪዎችን በሙሉ የሚሸፈነው የይሖዋ ምስክሮች በሚሰጡት የገንዘብ እርዳታና አንዳንዶች በሚያደርጉት ሕጋዊ ኑዛዜ ነው።

በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎች በሙሉ በጉባኤም ይሁን በትልልቅ ስብሰባዎች የገንዘብ እርዳታ ለመስጠት የሚፈልጉ ሁሉ እርዳታቸውን የሚጨምሩባቸው ሳጥኖች ይዘጋጃሉ። ገንዘብ ለመሰብሰብ እየዞረ የሚጠይቅ ሰው የለም። የማኅበረተኛነት ክፍያ ወይም አሥራት አይጠየቅም። በቅዱሳን ጹሑፎች እንደተገለጸው እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ሊሰጥ ይችላል።—2 ቆሮንቶስ 8:12፤ 9:7

● ለይሖዋ ምሥክሮች ሥራ የሚያስፈልገው የገንዘብ ድጋፍ የሚገኘው እንዴት ነው?