በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ልንረዳዎት እንፈልጋለን

ልንረዳዎት እንፈልጋለን

ልንረዳዎት እንፈልጋለን

ይህ ብሮሹር የተዘጋጀው ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ሥራና እርስዎ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀትዎን እንዲያዳብሩ ለመርዳት የይሖዋ ምሥክሮች ስለሚያደርጉአቸው ዝግጅቶች በይበልጥ እንዲያውቁ ለማስቻል ተብሎ ነው። የይሖዋ ምሥክሮች እቤትዎ ድረስ መጥተው ወይም መንገድ ላይ ወይም በሌሎች ቦታዎች አግኝተው እርስዎን አነጋግረው ይሆናል። ምናልባትም ከይሖዋ ምሥክሮች አንዱ እያስጠናዎት ይሆናል።

ስለ አምላክ መንግሥት የሚገልጸው መልእክታቸው በዓለም በሙሉ የሚሰበክ መሆኑን ያውቁ ነበርን? ይህ ሊሆን የቻለው ለምንድን ነው? ፈጣሪያችን የሆነው አምላክ ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ ሕዝቦች እሱን በማምለክ አንድ እንዲሆኑ ስለሚፈልግ ነው። አምላክ ስለ ዘመናችን የሚከተለውን ትንቢት ተናግሯል:- “ብዙዎች አሕዛብ ሄደው:- ‘ኑ፣ ወደ እግዚአብሔር [ይሖዋ አዓት ] ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፣ በጐዳናውም እንሄዳለን’ ይላሉ።”—ኢሳይያስ 2:2, 3

የይሖዋ ምሥክሮች ስለ አምላክ መንገዶች ለመናገር የሚያደርጉአቸው እንቅስቃሴዎችና ሥራዎች የዚህ ትንቢት ፍጻሜ ናቸው። የሚቀጥሉት ገጾች ይህ ሥራ በአሁኑ ጊዜ ለምን አስፈላጊ እንደሆነና እርስዎም ከዚህ ሥራ እንዴት ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ይገልጹልዎታል።