በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጀመሪያው መቶ ዘመን የክርስቲያን ጉባኤ

የመጀመሪያው መቶ ዘመን የክርስቲያን ጉባኤ

የመጀመሪያው መቶ ዘመን የክርስቲያን ጉባኤ

በ33 እዘአ በጰንጠቆስጤ ዕለት መንፈስ ቅዱስ በ120 የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ላይ ወረደና በብዙ ቋንቋዎች የአምላክን ድንቅ ነገሮች መናገር ጀመሩ። በዚህ ጊዜ የክርስቲያን ጉባኤ መቋቋሙ ነበር። በዚህ ቀን 3,000 የሚያክሉ አዳዲስ ደቀ መዛሙርት ተጠመቁ።—ሥራ ምዕራፍ 2

ሐዋርያትና ሌሎች ደቀ መዛሙርት የአምላክን ቃል በድፍረት መናገራቸውን በቀጠሉ መጠን በተለያዩ ስፍራዎች የነበሩ ጉባኤዎች በቁጥር ጨመሩ። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደተመዘገበው ስብከቱ በሜዲትራንያን አካባቢ በሙሉ ከባቢሎንና ሰሜን አፍሪካ እስከ ሮምና ምናልባትም እስከ እስፓኝ ድረስ በፍጥነት ተስፋፋ።—ሮሜ 15:18–29፤ ቆላስይስ 1:23፤ 1 ጴጥሮስ 5:13

ደቀ መዛሙርት የሚሆኑ ሰዎች በተገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ ጉባኤዎች ይቋቋሙ ነበር። ብቃት ያላቸው የጐለመሱ ወንዶች ሽማግሌዎች ወይም የበላይ ተመልካቾች ሆነው በመሾም በየጉባኤዎቹ የትክክለኛ ትምህርትና ምግባር ደረጃ እንዲጠበቅ ያደርጉ ነበር። ይሁን እንጂ እነዚህ ሽማግሌዎች የቀሳውስት ቡድን ሆነው አልተቋቋሙም። የአምላክ መንግሥት አገልጋዮችና የሥራ ባልደረቦች ነበሩ።—ሥራ 14:23፤ 20:28፤ 1 ቆሮንቶስ 3:5፤ 5:13፤ ቆላስይስ 4:11፤ 1 ጢሞቴዎስ 3:1–15፤ ዕብራውያን 13:17፤ 1 ጴጥሮስ 5:1–4

ሐዋርያትና የእነርሱ የቅርብ የሥራ ባልደረቦች የነበሩ ደቀ መዛሙርት የአስተዳደር አካል አባሎች በመሆን አገልግለዋል። በስብከቱ ሥራም ሌሎችን እየመሩ ተሳትፈዋል። በኢየሩሳሌም ጉባኤ የተነሱትን ችግሮች ፈትተዋል። አዳዲስ አማኞችን እንዲያበረታቱ ብቃት ያላቸውን ወንድሞች ወደ ሰማርያና ወደ አንጾኪያ ልከዋል። ስለመገረዝ ክርክር በተነሳ ጊዜ ተገቢ ውሳኔ ላይ ደርሰው ውሳኔያቸውን ሁሉም ጉባኤዎች እንዲጠብቁ ልከውላቸዋል። ሆኖም እነዚህ ሰዎች ከጠቅላላው ጉባኤ ጋር አብረው የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ እንጂ በሌሎች ላይ አለቃ ሆነው የሚገዙ አልነበሩም።—ሥራ 4:33፤ 6:1–7፤ 8:14–25፤ 11:22–24፤ 15:1–32፤ 16:4, 5፤ 1 ቆሮንቶስ 3:5–9፤ 4:1, 2፤ 2 ቆሮንቶስ 1:24

የቀድሞዎቹ ደቀ መዛሙርት ክርስቲያኖች ተብለው መጠራት ጀመሩ። ይህንንም ስያሜ ያገኙት በመለኮታዊ አመራር ነበር። እንደዚሁም ከሌሎች ልዩ የሚያደርጉአቸው ትምህርቶች ነበሩአቸው። እነዚህም ትምህርቶች የሐዋርያት ትምህርቶች ወይም የጤናማ ቃላት ሥርዓት ተብለው ይጠሩ ነበር። በተጨማሪም ይህ ቅዱስ ጽሑፋዊ ትምህርት እውነት ተብሎ ይጠራ ነበር።—ዮሐንስ 17:17፤ ሥራ 2:42፤ 11:26፤ ሮሜ 6:17፤ 1 ጢሞቴዎስ 4:6፤ 6:1, 3፤ 2 ጢሞቴዎስ 1:13፤ 2 ጴጥሮስ 2:2፤ 2 ዮሐንስ 1, 4, 9

በፍቅር የተሳሠሩ ዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር ነበሩ። በሌሎች አገሮች ስለሚኖሩ የእምነት መሰሎቻቸው ሁኔታም ያስቡ ነበር። ወደ ውጭ አገሮች በሚሄዱባቸው ጊዜያት የእምነት ወንድሞቻቸው በቤታቸው ተቀብለው ያስተናግዱአቸው ነበር። ከዓለም የተለዩ ቅዱስ ሕዝብ በመሆን ከፍተኛ የሆነ የሥነ ምግባር ደረጃ ጠብቀዋል። የይሖዋን ቀን በሐሳባቸው አቅርበው በመመልከት እምነታቸውን ለሕዝብ ሁሉ በቅንዓት ይገልጹ ነበር።—ዮሐንስ 13:34, 35፤ 15:17–19፤ ሥራ 5:42፤ 11:28, 29፤ ሮሜ 10:9, 10, 13–15፤ ቲቶ 2:11-14፤ ዕብራውያን 10:23፤ 13:15፤ 1 ጴጥሮስ 1:14-16፤ 2:9–12፤ 5:9፤ 2 ጴጥሮስ 3:11–14፤ 3 ዮሐንስ 5–8

ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ይመጣል ተብሎ የተነገረለት ክህደት በሁለተኛውና በሦስተኛው መቶ ዘመናት መስፋፋት ጀመረ። ይህም በትምህርት፣ በሥነ ምግባር፣ በአደረጃጀትና ከዓለም ጋር ባለው አቋም ረገድ የቀድሞውን ክርስቲያን ጉባኤ ንጽሕና ያልጠበቁ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶችን አፍርቷል።—ማቴዎስ 13:24–30, 37–43፤ 2 ተሰሎንቄ ምዕራፍ 2

ሆኖም በሥርዓቱ መደምደሚያ ላይ እውነተኛው አምልኰ ተመልሶ እንደሚቋቋም ኢየሱስ ተናግሮ ነበር። ይህ የንፁሕ አምልኮ ተመልሶ መቋቋም ኢየሱስ ይህን ትንቢት ከተናገረ ከ1,900 ዓመታት በኋላ ዛሬ የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም በሙሉ በሚፈጽሙት ሥራ ላይ ሊታይ እንደሚቻል ያምናሉ። የሚቀጥሉት ገጾች የይሖዋ ምሥክሮች ለምን እንዲህ ብለው እንደሚያምኑ ይገልጻሉ።

● የክርስቲያን ጉባኤ የተመሠረተው እንዴት ነበር? ያደገውስ እንዴት ነው?

● ጉባኤው ቁጥጥር ይደረግለት የነበረው እንዴት ነበር?

● የመጀመሪያ መቶ ዘመን ክርስቲያኖችን በግልጽ ለይቶ የሚያሳውቃቸው ምን ነበር?

[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ ካርታ]

ጥቁር ባሕር

የካስፒያን ባሕር

ታላቁ ባሕር

ቀይ ባሕር

የፋርስ ባሕረ ሰላጤ

በመጀመሪያው መቶ ዘመን ምሥራቹ የተዳረሰባቸው አካባቢዎች

ኢጣልያ

ሮም

ግሪክ

ማልታ

ቀርጤስ

ቆጵሮስ

ቢታንያ

ገላትያ

እስያ

ቀጰዶቅያ

ኪልቂያ

ሶርያ

እስራኤል

ኢየሩሳሌም

መስጴጦምያ

ባቢሎን

በእነዚህ አካባቢዎች ይኖሩ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች አማኞች ሆነዋል

እልዋሪቆን

ሜዶን

ጳርቴና

ኤላም

ዓረቢያ

ልብያ

ግብጽ

ኢትዮጵያ

[በገጽ 7 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

የቀድሞ ክርስቲያኖች የአምላክን ቃል በድፍረት ሰብከዋል

ክርስቲያኖች በተጓዙበት ሁሉ በእምነት ወንድሞቻቸው ቤት ይስተናገዱ ነበር