ብቸኛውን እውነተኛ አምላክ ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርገው
ምዕራፍ ሁለት
ብቸኛውን እውነተኛ አምላክ ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርገው
1. ብቸኛው እውነተኛ አምላክ ማን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ምንም እንኳ ብዙ አማልክት ቢኖሩም ‘ለእኛ ግን አንድ አምላክ አብ አለን’ ሲል ይናገራል። (1 ቆሮንቶስ 8:5, 6) ይህ “አንድ አምላክ” ሁሉን ነገር የፈጠረው ይሖዋ ነው። (ዘዳግም 6:4፤ ራእይ 4:11) ኢየሱስ ‘አምላኬና አምላካችሁ’ ሲል ጠርቶታል። (ዮሐንስ 20:17) ይህ የኢየሱስ አባባል ጥንት ሙሴ ‘እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ሲል ከተናገረው ቃል ጋር ይስማማል። (ዘዳግም 4:35) ይሖዋ ከጣዖታት፣ እንደ አምላክ ከሚታዩ ሰዎች፣ ባላጋራው ከሆነውና “የዚህ ዓለም አምላክ” ተብሎ ከተጠራው ከሰይጣን ዲያብሎስም ሆነ ከሌሎች የሚመለኩ ነገሮች ሁሉ እጅግ የላቀ አምላክ ነው። (2 ቆሮንቶስ 4:3, 4) ከእነዚህ ሁሉ በተለየ መልኩ ይሖዋ ‘ብቻ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ’ ኢየሱስ ተናግሯል።—ዮሐንስ 17:3 የ1954 ትርጉም
2. ስለ አምላክ የምናገኘው ትምህርት በሕይወታችን ላይ ምን ለውጥ ሊያመጣ ይገባዋል?
2 አድናቂ የሆኑ ሰዎች አስደሳች ስለሆኑት የአምላክ ባሕርያት እንዲሁም እስካሁን ስላደረጋቸውና ወደፊት ስለሚያደርጋቸው ነገሮች ሲማሩ ወደ እሱ ለመቅረብ ይነሳሳሉ። ለይሖዋ ያላቸው ፍቅር እያደገ ሲሄድ እሱን ከፍ ከፍ ለማድረግ ይገፋፋሉ። እንዴት? አንደኛው መንገድ ስለ እሱ ለሌሎች በመናገር ነው። ሮሜ 10:10 “የምትድነውም በአፍህ መስክረህ ነው” ሲል ይገልጻል። ሌላው መንገድ ደግሞ በቃልም ሆነ በተግባር እሱን በመምሰል ነው። ኤፌሶን 5:1 “እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን ምሰሉ” ይላል። ይህን በተሟላ ሁኔታ ማድረግ እንድንችል የይሖዋን ትክክለኛ ማንነት ማወቅ ያስፈልገናል።
3. የአምላክ ዋና ዋና ባሕርያት ምንድን ናቸው?
3 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጉልህ የሆኑትን የአምላክ ባሕርያት ለይተው የሚጠቅሱ በርካታ መግለጫዎች አሉ። አራቱ የአምላክ ዋና ዋና ባሕርያት ጥበብ፣ ፍትሕ፣ ኃይልና ፍቅር ናቸው። ‘ጥበብ የእግዚአብሔር ነው።’ (ኢዮብ 12:13) “እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳል።” (መዝሙር 37:28) ‘ኃይሉ ታላቅ ነው።’ (ኢሳይያስ 40:26) “እግዚአብሔር ፍቅር ነው።” (1 ዮሐንስ 4:8) ይሁንና ከአራቱ ዋና ዋና ባሕርያቱ መካከል አምላክን ይበልጥ የሚገልጸው ከሁሉ የላቀ ባሕርይ የትኛው ነው?
“እግዚአብሔር ፍቅር ነው”
4. አምላክ ጽንፈ ዓለምንም ሆነ ሕያዋን ፍጥረታትን በሙሉ እንዲፈጥር ያነሳሳው ዋነኛ ባሕርይ ምንድን ነው?
4 ይሖዋ ጽንፈ ዓለሙንም ሆነ የማሰብ ችሎታ ያላቸውን መንፈሳዊና ሰብዓዊ ፍጥረታት እንዲፈጥር ያነሳሳው ምን እንደሆነ አስብ። ጥበቡ ወይም ኃይሉ ነው? አይደለም፤ አምላክ ሲፈጥር እነዚህን ባሕርያቱን የተጠቀመባቸው ቢሆንም ለመፍጠር የተነሳሳው ግን በእነዚህ ባሕርያት ተገፋፍቶ አይደለም። ፍትሑም ቢሆን የሕይወትን ስጦታ ለሌሎች እንዲያጋራ አያስገድደውም። ከዚህ ይልቅ የማሰብ ችሎታ ያላቸውን ፍጥረታት በመፍጠር የሕይወትን ጣዕም እንዲቀምሱ ለማድረግ ያነሳሳው ታላቅ ፍቅሩ ነው። ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች በገነት ውስጥ ለዘላለም መኖር የሚችሉበትን ዝግጅት ያደረገው በፍቅር ተገፋፍቶ ነው። (ዘፍጥረት 1:28፤ 2:15) የአዳም ኃጢአት በሰው ዘር ላይ ያስከተለው እርግማን የሚወገድበትን ዝግጅት እንዲያደርግ የገፋፋውም ፍቅር ነው።
5. መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጸው ይሖዋ የየትኛው ባሕርይ ተምሳሌት ነው? ለምንስ?
5 ስለዚህ ከአምላክ ባሕርያት ሁሉ እጅግ የላቀው ፍቅር ነው። ይሖዋ ሁለንተናው ፍቅር ነው። ጥበቡ፣ ፍትሑና ኃይሉ በጣም አስፈላጊ ባሕርያት ቢሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ ጥበብ ነው፣ ፍትሕ
ነው ወይም ኃይል ነው አይልም። ይሖዋ ፍቅር እንደሆነ ግን ይናገራል። አዎን፣ ይሖዋ የፍቅር ተምሳሌት ነው። ይህ ፍቅር በስሜት ሳይሆን በመሠረታዊ ሥርዓት የሚመራ ነው። የአምላክ ፍቅር በእውነትና በጽድቅ መሠረታዊ ሥርዓቶች የሚመራ ነው። ይህ የፍቅር ዓይነት በራሱ በይሖዋ አምላክ ላይ እንደታየው ከሌሎች የፍቅር ዓይነቶች ሁሉ የላቀ ነው። ሙሉ በሙሉ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ የፍቅር ዓይነት ሲሆን ምንጊዜም በተግባር የሚገለጽ ነው።6. አምላክ ከእኛ የላቀ ቢሆንም እንኳ እሱን እንድንመስል የሚያስችለን ምንድን ነው?
6 እንዲህ ያለውን አምላክ እንድንመስል የሚያስችለን ይህ ግሩም የሆነ የፍቅር ባሕርይ ነው። ፍጽምና የጎደለንና ስህተት መሥራት የሚቀናን ሰዎች በመሆናችን በፍጹም አምላክን መምሰል እንደማንችል ሆኖ ይሰማን ይሆናል። ሆኖም የይሖዋን ታላቅ ፍቅር የሚያሳይ ሌላ ምሳሌ ተመልከት:- ያለብንን የአቅም ገደብ የሚያውቅ ከመሆኑም በላይ ከእኛ ፍጽምና አይጠብቅም። ምን ያህል ከፍጽምና የራቅን እንደሆንን በሚገባ ያውቃል። (መዝሙር 51:5) መዝሙር 130:3, 4 “እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአትን ብትቆጣጠር፣ ጌታ ሆይ፤ ማን ሊቆም ይችላል? ነገር ግን በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለ” የሚለው በዚህ ምክንያት ነው። አዎን፣ ይሖዋ ‘ሩኅሩኅ ቸር አምላክ ለቁጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ’ ነው። (ዘፀአት 34:6) “ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ።” (መዝሙር 86:5) ይህ ምንኛ የሚያጽናና ነው! ይህን ዕጹብ ድንቅ የሆነ አምላክ ማገልገል እንዲሁም ፍቅርና ምሕረት የሚንጸባረቅበትን እንክብካቤውን ማግኘት እንዴት የሚያስደስት ነው!
7. የይሖዋ ፍቅር በፍጥረት ሥራዎቹ ላይ የተንጸባረቀው እንዴት ነው?
7 የይሖዋ ፍቅር በፍጥረት ሥራዎቹ ላይም ተንጸባርቋል። ይሖዋ ለእኛ ደስታ ሲል የፈጠራቸውን ውብ ተራሮች፣ ደኖች፣ ሐይቆች፣ ውቅያኖሶችና እነዚህን የመሳሰሉ በርካታ ድንቅ ነገሮችን አስብ። የሚያረካ ጣዕም ያላቸውና በሕይወት ለመቀጠል የሚያስችሉ የተለያዩ ሮሜ 8:22) ሆኖም ይሖዋ በገነት ውስጥ ምን እንደሚያደርግልን አስብ! መዝሙራዊው “አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤ የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ [ትክክለኛ] ፍላጎት ታረካለህ” በማለት ማረጋገጫ ይሰጠናል።—መዝሙር 145:16
ምግቦችን ሰጥቶናል። በተጨማሪም ይሖዋ ሥፍር ቁጥር የሌላቸውን ውብና ጥሩ መዓዛ ያላቸው አበቦች እንዲሁም አስደናቂ የሆኑ የተለያዩ እንስሳትን ፈጥሮልናል። ይህን የማድረግ ግዴታ ባይኖርበትም እንኳ ለሰው ልጆች ደስታ የሚሰጡ ነገሮችን ፈጥሯል። እርግጥ ነው፣ ፍጽምና ስለሚጎድለንና በዚህ ክፉ ዓለም ውስጥ ስለምንኖር አምላክ ለእኛ ሲል ከፈጠራቸው ነገሮች የተሟላ ደስታ ማግኘት አንችልም። (8. ይሖዋ ለእኛ ያለውን ፍቅር የሚያሳየው ከሁሉ የላቀ ምሳሌ ምንድን ነው?
8 ይሖዋ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር የሚያሳየው ከሁሉ የላቀ ምሳሌ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና” ሲል ይገልጻል። (ዮሐንስ 3:16) ይሖዋ ይህን ያደረገው ሰዎች ጥሩ ስለሆኑ ነው? ሮሜ 5:8 “ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል” ሲል መልስ ይሰጠናል። አዎን፣ አምላክ ፍጹም የሆነው ልጁ ሕይወቱን ለእኛ ቤዛዊ መሥዋዕት አድርጎ በመስጠት ከኃጢአትና ከሞት ኩነኔ እንዲዋጀን ወደ ምድር ልኮታል። (ማቴዎስ 20:28) ይህም አምላክን የሚወዱ ሰዎች የዘላለም ሕይወት ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ከፍቷል። መጽሐፍ ቅዱስ ‘እግዚአብሔር ለማንም አያዳላም፤ ነገር ግን እርሱን የሚፈሩትንና ጽድቅን የሚያደርጉትን ሁሉ ከየትኛውም ወገን ቢሆኑ ይቀበላቸዋል’ ስለሚል አምላክ ፈቃዱን ማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ ፍቅሩን ያሳያል።—የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35
9. ይሖዋ ልጁን ለእኛ ቤዛ አድርጎ መስጠቱ በእኛ ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይገባል?
9 ይሖዋ ልጁን ለእኛ ቤዛ አድርጎ በመስጠት የዘላለም ሕይወት ማግኘት 2 ቆሮንቶስ 5:15) ኢየሱስ የይሖዋን ፍቅርና ርኅራኄ በመኮረጅ ረገድ ግሩም ምሳሌ በመሆኑ የእሱን ፈለግ መከተል እጅግ አስደሳች ነው! ኢየሱስ ትሑት ለሆኑ ሰዎች ያቀረበው የሚከተለው ግብዣ ይህን ያሳያል:- “እናንት ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ። ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀላል ነውና።”—ማቴዎስ 11:28-30
የምንችልበትን መንገድ መክፈቱ በአሁኑ ጊዜ ሕይወታችንን እንዴት እንድንጠቀምበት ሊገፋፋን ይገባል? ለእውነተኛው አምላክ ለይሖዋ ያለንን ፍቅር ሊያጠነክረው እንዲሁም የአምላክ ወኪል የሆነውን ኢየሱስን እንድንሰማው ሊገፋፋን ይገባል። “በሕይወት ያሉትም ለሞተላቸው [ለኢየሱስ] . . . እንጂ ከእንግዲህ ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ።” (ለሌሎች ፍቅር ማሳየት
10. ለክርስቲያን ባልንጀሮቻችን ፍቅር ማሳየት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው?
10 ይሖዋና ኢየሱስ ለእኛ ያላቸውን ዓይነት ፍቅር ለክርስቲያን ባልንጀሮቻችን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ይህን ማድረግ የምንችልባቸውን የተለያዩ መንገዶች ተመልከት:- “ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፣ በደልን አይቈጥርም። ፍቅር ከእውነት ጋር እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም። ፍቅር ሁልጊዜ ይታገሣል፤ ሁልጊዜ ያምናል፤ ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል። ፍቅር ከቶ አይወድቅም።”—1 ቆሮንቶስ 13:4-8፤ 1 ዮሐንስ 3:14-18፤ 4:7-12
11. ከክርስቲያን ባልንጀሮቻችን በተጨማሪ ለማን ፍቅር ማሳየት ይኖርብናል? እንዴትስ?
11 ከክርስቲያን ባልንጀሮቻችን በተጨማሪ ለማን ፍቅር ማሳየት ይኖርብናል? እንዴትስ? ኢየሱስ “ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ ማቴዎስ 28:19, 20) ይህም አምላክ ወደፊት ስለሚያመጣው አዲስ ዓለም የሚገልጸውን ምሥራች ክርስቲያን ባልንጀሮቻችን ላልሆኑ ሰዎች መናገርን ይጨምራል። ኢየሱስ እንደሚከተለው ብሎ በመናገር ፍቅራችን ለእምነት አጋሮቻችን ብቻ የተወሰነ መሆን እንደሌለበት በግልጽ አመልክቷል:- “የሚወዷችሁን ብቻ የምትወዱ ከሆነ ምን ዋጋ ታገኛላችሁ? ቀራጮችስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁን ብቻ እጅ የምትነሡ ከሆነ ከሌሎች በምን ትሻላላችሁ? አሕዛብስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?”—ማቴዎስ 5:46, 47፤ 24:14፤ ገላትያ 6:10
በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው” ሲል ተናግሯል። (‘በይሖዋ ስም መሄድ’
12. የአምላክ ስም ለእሱ ብቻ የሚገባ ነው የምንለው ለምንድን ነው?
12 እውነተኛውን አምላክ ከፍ ከፍ ማድረግ የሚቻልበት ሌላው ወሳኝ መንገድ ይሖዋ የተባለውን ልዩ የሆነ ስሙን ማወቅ፣ መጠቀምና ለሌሎች ማስተማር ነው። መዝሙራዊው “ሰዎች ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣ በምድር ሁሉ ላይ አንተ ብቻ ልዑል እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ ነው” በማለት ልባዊ ምኞቱን ገልጿል። (መዝሙር 83:18 NW) ይሖዋ የሚለው ስም “ይሆናል” የሚል ትርጉም አለው። ይሖዋ የዓላማ አምላክ ከመሆኑም በላይ ዓላማውን ምንጊዜም ዳር ያደርሳል። ሰዎች ውጥናቸው ዳር ይድረስ አይድረስ እርግጠኛ መሆን ስለማይችሉ በዚህ ስም ሊጠራ የሚገባው እውነተኛው አምላክ ብቻ ነው። (ያዕቆብ 4:13, 14) ከአፉ የወጣው ቃሉ ሳይፈጸም እንደማይቀር በእርግጠኝነት ሊናገር የሚችለው ይሖዋ ብቻ ነው። (ኢሳይያስ 55:11) ብዙዎች የአምላክን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲመለከቱና የስሙ ትርጉም ምን እንደሆነ ሲረዱ በጣም ይደሰታሉ። (ዘፀአት 6:3 የ1879 ትርጉም) ይሁንና በዚህ እውቀት ሊጠቀሙ የሚችሉት ‘በይሖዋ ስም ለዘላለም የሚሄዱ’ ከሆነ ብቻ ነው።—ሚክያስ 4:5 NW
13. የይሖዋን ስም ማወቅና በስሙ መሄድ ምንን ይጨምራል?
መዝሙር 9:10 የአምላክን ስም በተመለከተ “ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል” በማለት ይገልጻል። ይህ እንዲሁ ይሖዋ የሚለውን ስም ከማወቅ የበለጠ ነገርን ይጨምራል፤ አንድ ሰው ይሖዋ የሚለውን መጠሪያ ስላወቀ ብቻ በእሱ ይታመናል ማለት አይደለም። የአምላክን ስም ማወቅ ሲባል ይሖዋ ምን ዓይነት አምላክ እንደሆነ በሚገባ መረዳት፣ ሥልጣኑን ማክበር፣ ትእዛዙን መፈጸምና በሁሉም ነገር በእሱ መታመን ማለት ነው። (ምሳሌ 3:5, 6) በተመሳሳይም በይሖዋ ስም መሄድ ሲባል ሕይወታችንን ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ በመጠቀም ራሳችንን ለእሱ መወሰንንና ከአምላኪዎቹ አንዱ በመሆን እሱን መወከልን ያመለክታል። (ሉቃስ 10:27) ይህን እያደረግክ ነው?
1314. ይሖዋን ለዘላለም ማገልገል ከፈለግን ግዴታችን እንደሆነ ተሰምቶን ከማገልገል በተጨማሪ ምን ነገር ያስፈልገናል?
14 ይሖዋን ለዘላለም ማገልገል ከፈለግን አገልግሎታችንን የምናከናውነው ግዴታችን እንደሆነ ተሰምቶን ብቻ መሆን የለበትም። ሐዋርያው ጳውሎስ ይሖዋን ለብዙ ዓመታት ያገለገለውን ጢሞቴዎስን “ለአምላክ የማደርን ባሕርይ ግብህ አድርገህ ራስህን አሠልጥን” ሲል አጥብቆ አሳስቦታል። (1 ጢሞቴዎስ 4:7 NW) አንድ ሰው ለአንድ አካል ያለው ከልብ የመነጨ አድናቆት ለዚያ አካል ያደረ እንዲሆን ያነሳሳዋል። ‘ለአምላክ ያደሩ መሆን’ የሚለው አገላለጽ ለይሖዋ አምልኮታዊ አክብሮት ማሳየትን ያመለክታል። ለእሱም ሆነ ለመንገዶቹ ባለን ከፍ ያለ ግምት ተገፋፍተን ከእሱ ጋር የምንመሠርተውን የጠበቀ ወዳጅነት ያሳያል። ሁሉም ሰው የአምላክን ስም እንዲያከብር የማድረግ ምኞት እንዲያድርብን ያደርጋል። በእውነተኛው አምላክ በይሖዋ ስም ለዘላለም መሄድ ከፈለግን በሕይወታችን ውስጥ ለአምላክ የማደርን ባሕርይ ማዳበር ይኖርብናል።—መዝሙር 37:4፤ 2 ጴጥሮስ 3:11
15. ለይሖዋ ብቻ የተወሰነ አምልኮ ማቅረብ የምንችለው እንዴት ነው?
15 አምላክን ተቀባይነት ባለው መንገድ ማገልገል የምንፈልግ ከሆነ ይሖዋ “ቀናተኛ አምላክ” ማለትም እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ ዘፀአት 20:5) ይሖዋን የምንወድ ከሆነ ሰይጣን አምላኩ የሆነለትን ይህን ክፉ ዓለም መውደድ የለብንም። (ያዕቆብ 4:4፤ 1 ዮሐንስ 2:15-17) ይሖዋ እያንዳንዳችን ምን ዓይነት ሰው ለመሆን እየጣርን እንዳለን በሚገባ ያውቃል። (ኤርምያስ 17:10) ጽድቅን ከልባችን የምንወድ ከሆነ ይሖዋ ይህን የሚገነዘብ ከመሆኑም በላይ በየዕለቱ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች በጽናት መቋቋም እንድንችል ይረዳናል። ከፍተኛ ኃይል ባለው ቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት በመደገፍ በዚህ ዓለም ውስጥ እጅግ ተስፋፍቶ በሚገኘው ክፋት ላይ ድል እንድንቀዳጅ ያስችለናል። (2 ቆሮንቶስ 4:7) በተጨማሪም ገነት በምትሆነው ምድር ላይ የዘላለም ሕይወት የማግኘት ተስፋችን ሁልጊዜ ብሩህ ሆኖ እንዲታየን ይረዳናል። ይህ እንዴት ያለ አስደናቂ ተስፋ ነው! ይህን ተስፋ ከልብ ማድነቅና ይህ ተስፋ እውን እንዲሆን የሚያደርገውን እውነተኛውን አምላክ ይሖዋን በፈቃደኝነት ማገልገል ይኖርብናል።
በመሆኑ ለእሱ ብቻ የተወሰነ አምልኮ ማቅረብ ይኖርብናል። (16. በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎች ጋር በመተባበር ምን ማድረግ ይኖርብሃል?
16 በምድር ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች “ኑና ከእኔ ጋር እግዚአብሔርን አክብሩት፤ ስሙንም በአንድነት ከፍ ከፍ እናድርግ” ሲል የጻፈው መዝሙራዊ ያቀረበውን ግብዣ በደስታ ተቀብለዋል። (መዝሙር 34:3) ይሖዋ ይህን እያደረጉ ካሉት ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች አንዱ እንድትሆን ይጋብዝሃል።
የክለሳ ውይይት
• ይሖዋ ምን ዓይነት አምላክ ነው? ስለ ባሕርያቱ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘታችን የሚጠቅመን እንዴት ነው?
• ለሌሎች ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
• የይሖዋን ስም ማወቅና በስሙ መሄድ ምን ነገሮችን ይጨምራል?
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 14 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]
ይሖዋ በታላቅ ፍቅሩ በመገፋፋት ‘እጁን ዘርግቶ የሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ፍላጎት ያረካል’