‘ከርኩሳን መናፍስታዊ ኃይሎች ጋር መጋደል’
ምዕራፍ ስምንት
‘ከርኩሳን መናፍስታዊ ኃይሎች ጋር መጋደል’
1. ርኩሳን መናፍስት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ እኛን ይበልጥ የሚያሳስበን ለምንድን ነው?
ብዙ ሰዎች ርኩሳን መናፍስት አሉ በሚለው ሐሳብ ያሾፋሉ። ሆኖም ይህ የሚሾፍበት ነገር አይደለም። ሰዎች ይህን አመኑም አላመኑ ርኩሳን መናፍስት ያሉ ከመሆኑም በላይ በሁሉ ሰው ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ይሞክራሉ። የይሖዋ አምላኪዎችም ከዚህ ነፃ አይደሉም። እንዲያውም ዋነኛ የጥቃት ዒላማዎች ናቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚከተለው በማለት ይህን ሐቅ ያስገነዝበናል:- “ተጋድሎአችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም [የማይታዩ] ገዦች፣ ከሥልጣናትና ከኀይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው።” (ኤፌሶን 6:12) ሰይጣን ከሰማይ ወደ ምድር ስለተጣለና የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን አውቆ በጣም ስለተቆጣ በዛሬው ጊዜ ርኩሳን መናፍስታዊ ኃይሎች በሰዎች ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ከምንጊዜውም ይበልጥ የከፋ ሆኗል።—ራእይ 12:12
2. ከሰው በላይ ኃይል ካላቸው መናፍስታዊ ኃይሎች ጋር በምናደርገው ትግል ማሸነፍ የምንችለው እንዴት ነው?
2 ከሰው በላይ ኃይል ካላቸው መናፍስታዊ ኃይሎች ጋር ታግሎ ማሸነፍ ይቻላል? አዎን ይቻላል፤ ሆኖም ይህን ማድረግ የሚቻለው ሙሉ በሙሉ በይሖዋ በመታመን ነው። እሱን መስማትና ቃሉን መታዘዝ ይኖርብናል። ይህን ማድረጋችን በሰይጣን ቁጥጥር ሥር ባሉት ሰዎች ላይ ከሚደርሰው አካላዊ፣ ሥነ ምግባራዊና ስሜታዊ ጉዳት ሊጠብቀን ይችላል።—ያዕቆብ 4:7
በሰማያዊ ስፍራ ያሉ የዓለም ገዦች
3. ሰይጣን ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳው በእነማን ላይ ነው? እንዴትስ?
3 ይሖዋ በዓለም ላይ ያለውን ሁኔታ ከሰማይ ሆኖ በመመልከት ጥሩ አድርጎ ገልጾልናል። ለሐዋርያው ዮሐንስ ባሳየው ራእይ ላይ ሰይጣን እንደ “ታላቅ ቀይ ዘንዶ” ሆኖ ተገልጿል። ሰይጣን ቢችል ኖሮ በ1914 በሰማይ የተወለደውን የአምላክ መሲሐዊ መንግሥት ወዲያውኑ ለመዋጥ ተዘጋጅቶ ነበር። ሆኖም ይህን ማድረግ ስላልቻለ በምድር ላይ በሚገኙት የአምላክ መንግሥት ወኪሎች ላይ ኃይለኛ የተቃውሞ ማዕበል አስነስቷል። (ራእይ 12:3, 4, 13, 17) ሰይጣን ይህን ውጊያ የሚያካሂደው እንዴት ነው? የራሱን ሰብዓዊ ወኪሎች በመጠቀም ነው።
4. የሰብዓዊ መንግሥታት ኃይል ምንጭ ማን ነው? ይህንንስ እንዴት እናውቃለን?
4 በመቀጠል ዮሐንስ “በነገድ፣ በወገን፣ በቋንቋና በሕዝብም ሁሉ ላይ” ሥልጣን የተሰጠው ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉት አውሬ ተመልክቷል። ይህ አውሬ መላውን የዓለም የፖለቲካ ሥርዓት ይወክላል። ዮሐንስ “ዘንዶው [ሰይጣን ዲያብሎስ] የራሱን ኀይልና የራሱን ዙፋን እንዲሁም ታላቅ ሥልጣን ለአውሬው” እንደሰጠው ተገልጾለታል። (ራእይ 13:1, 2, 7) አዎን፣ የሰብዓዊ መንግሥታት ኃይልና ሥልጣን ምንጭ ሰይጣን ነው። በመሆኑም ሐዋርያው ጳውሎስ እንደጻፈው እውነተኞቹ ‘የዓለም ገዦች’ ሰብዓዊ መንግሥታትን በመቆጣጠር ላይ ያሉት ‘በሰማያዊ ስፍራ ያሉ ርኩሳን መናፍስት’ ናቸው። ይሖዋን ማምለክ የሚፈልጉ ሁሉ ይህ ምን ጥልቅ ትርጉም እንዳለው መረዳት ያስፈልጋቸዋል።—ሉቃስ 4:5, 6
5. በዛሬው ጊዜ የፖለቲካ ገዢዎች ወዴት እየተሰበሰቡ ነው?
5 ምንም እንኳ ብዙዎቹ የፖለቲካ ገዢዎች ሃይማኖተኞች እንደሆኑ ቢናገሩም ለይሖዋም ሆነ እሱ ለሾመው ንጉሥ ለኢየሱስ ክርስቶስ አገዛዝ የሚገዙ ብሔራት የሉም። ሁሉም ሥልጣናቸውን ላለማጣት ከፍተኛ ትግል ያደርጋሉ። በራእይ መጽሐፍ ላይ የሚገኘው ዘገባ እንደሚያመለክተው በዛሬው ጊዜ ‘ከአጋንንት አፍ የሚወጡ ቃላት’ የዓለምን ራእይ 16:13, 14, 16 NW፤ 19:17-19
ገዢዎች በአርማጌዶን ወደሚካሄደው ‘ሁሉን ወደሚችለው አምላክ ታላቅ የጦርነት ቀን’ እየሰበሰቧቸው ነው።—6. ሳናውቀው ለሰይጣን ሥርዓት ድጋፍ እንዳንሰጥ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?
6 ሰብዓዊውን ኅብረተሰብ የሚከፋፍሉ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሃይማኖታዊ ግጭቶች በየዕለቱ በሰዎች ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። እንዲህ ያሉ ግጭቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ በአብዛኛው ሰዎች በቃልም ሆነ በድርጊት ለራሳቸው ብሔር፣ ጎሳ፣ ቋንቋ ወይም ማኅበራዊ መደብ መወገናቸው አይቀርም። ሰዎች ራሳቸው በቀጥታ በግጭቱ ውስጥ ባይካፈሉም እንኳ ብዙውን ጊዜ ለአንዱ ወገን ያደላሉ። ይሁንና ከየትኛውም ሰው ሆነ ከየትኛውም ዓላማ ጎን ቢቆሙ በእርግጥ እየደገፉ ያሉት ማንን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ “መላው ዓለምም በክፉው ሥር እንደ ሆነ” በግልጽ ይናገራል። (1 ዮሐንስ 5:19) ታዲያ አንድ ግለሰብ እንደ ሌሎች ሰዎች የተሳሳተ ጎዳና ከመከተል መራቅ የሚችለው እንዴት ነው? ለአምላክ መንግሥት ሙሉ ድጋፍ በመስጠትና በዓለም ውስጥ ከሚቀሰቀሱ ግጭቶች ፍጹም ገለልተኛ በመሆን ነው።—ዮሐንስ 17:15, 16
ክፉው የሚጠቀምባቸው የረቀቁ ዘዴዎች
7. ሰይጣን የሐሰት ሃይማኖትን በረቀቀ መንገድ እንደተጠቀመበት የሚያሳየው ምንድን ነው?
7 በታሪክ ዘመናት ሁሉ ሰይጣን ስድብንና ዛቻን እንዲሁም አካላዊ ጥቃትን መሣሪያ በማድረግ ሰዎችን ከእውነተኛው አምልኮ ለማራቅ ሲጥር ቆይቷል። በተጨማሪም ሌሎች የረቀቁና መሠሪ የሆኑ ዘዴዎችን ተጠቅሟል። የሐሰት ሃይማኖትን እንደ መሣሪያ በመጠቀምና ሰዎች አምላክን እያገለገሉ እንዳሉ ሆኖ እንዲሰማቸው በማድረግ አብዛኛው የሰው ዘር በጨለማ ውስጥ እንዲዳክር አድርጓል። እነዚህ ሰዎች ስለ አምላክ ትክክለኛ እውቀት ስላላገኙና ለእውነት ፍቅር ስለሌላቸው ምስጢራዊና ስሜታዊ በሆኑ የሃይማኖት ሥርዓቶች ወይም በአንዳንድ 2 ተሰሎንቄ 2:9, 10) ይሁንና በእውነተኛ አምልኮ ይካፈሉ የነበሩ አንዳንዶች እንኳ “አታላይ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት እንደሚከተሉ” ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል። (1 ጢሞቴዎስ 4:1) ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?
ተአምራት ሊማረኩ ይችላሉ። (8. ይሖዋን የምናመልክ ብንሆንም እንኳ ሰይጣን አታልሎ ወደ ሐሰት ሃይማኖት ሊያስገባን የሚችለው እንዴት ነው?
8 ሰይጣን ደካማ ጎናችንንም እንደ መሣሪያ አድርጎ ይጠቀምበታል። አሁንም የሰው ፍርሃት አለብን? ካለብን ዘመዶቻችን ወይም ጎረቤቶቻችን ከሐሰት ሃይማኖት በመነጩ ልማዶች እንድንካፈል ተጽዕኖ ሲያደርጉብን በቀላሉ እጅ ልንሰጥ እንችላለን። ኩራት አለብን? ካለብን ምክር ሲሰጠን ወይም ሌሎች የእኛን ሐሳብ ሳይቀበሉ ሲቀሩ ቅር ልንሰኝ እንችላለን። (ምሳሌ 15:10፤ 29:25፤ 1 ጢሞቴዎስ 6:3, 4) አስተሳሰባችንን በማስተካከል የክርስቶስን ምሳሌ ከመከተል ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና መልካም ማድረግ ብቻ በቂ ነው በሚል አነጋገራቸው ጆሯችንን የሚኮረኩሩልንን ሰዎች አስተሳሰብ መከተል ሊቀናን ይችላል። (2 ጢሞቴዎስ 4:3) አምላክ በቃሉና በድርጅቱ በኩል በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ይሖዋን አናምልክ እንጂ የሌላ ሃይማኖት አባል ብንሆን ወይም ደግሞ የራሳችንን ሃይማኖት ብንከተል ሰይጣን ግድ አይሰጠውም።
9. ሰይጣን የራሱን ዓላማ ለማሳካት የሰዎችን የጾታ ፍላጎት እንደ መሣሪያ አድርጎ የሚጠቀምበት እንዴት ነው?
9 ከዚህም በላይ ሰይጣን ሰዎችን መሠሪ በሆኑ ዘዴዎች በማታለል የተፈጥሮ ፍላጎቶቻቸውን ተገቢ ባልሆነ መንገድ ለማርካት እንዲነሳሱ ያደርጋል። ሰዎች ያላቸውን የጾታ ፍላጎት ለዚህ ዓላማ ተጠቅሞበታል። የመጽሐፍ ቅዱስን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች የማይቀበሉ ብዙ ሰዎች ባልተጋቡ ሰዎች መካከል የሚደረገውን የጾታ ግንኙነት ምንም ስህተት እንደሌለበት ወይም አንድ ሰው ለአካለ መጠን እንደደረሰ የሚያሳይበት መንገድ እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል። ስለተጋቡ ሰዎችስ ምን ለማለት ይቻላል? ብዙዎች ምንዝር ይፈጽማሉ። 1 ቆሮንቶስ 6:9, 10፤ ገላትያ 6:7, 8
ትዳር ያላቸው ሌሎች በርካታ ሰዎች ደግሞ ምንዝር ባይፈጽሙም እንኳ ከትዳር ጓደኛቸው ተፋተው ወይም ተለያይተው ከሌላ ሰው ጋር እንዳሻቸው መሆን ይፈልጋሉ። ሰይጣን፣ ሰዎች የሚፈጽሙት ድርጊት በራሳቸውና በሌሎች ላይ በተለይ ደግሞ ከይሖዋና ከልጁ ጋር ባላቸው ዝምድና ረገድ የሚያስከትለውን ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ መዘዝ ቸል እንዲሉና ለጊዜያዊ ደስታ ብቻ ያደሩ እንዲሆኑ ለማድረግ የረቀቁ ዘዴዎችን ይጠቀማል።—10. ሰይጣን ለጾታ ብልግናና ለዓመጽ ያለንን አመለካከት ለማዛባት የሚሞክረው በምን መንገድ ነው?
10 ሌላው የሰዎች የተፈጥሮ ፍላጎት ደግሞ መዝናናት ነው። መዝናኛው ጤናማ እስከሆነ ድረስ አካልን፣ አእምሮንና ስሜትን ሊያድስ ይችላል። ሆኖም ሰይጣን የምንዝናናበትን ነገር መሣሪያ አድርጎ በመጠቀም በረቀቀ ዘዴ አስተሳሰባችን ከአምላክ አስተሳሰብ የተለየ እንዲሆን ለማድረግ ቢሞክር ምን እርምጃ እንወስዳለን? ለምሳሌ ያህል፣ ይሖዋ የጾታ ብልግናንና ዓመጽን እንደሚጠላ እናውቃለን። በፊልሞች፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ወይም በቲያትሮች እንዲህ ያሉ ነገሮች በሚቀርቡበት ጊዜ ዝም ብለን መመልከታችንን እንቀጥላለን? ሰይጣን ወደ ጥልቁ የሚጣልበት ጊዜ እየተቃረበ ሲሄድ እነዚህ ነገሮች ይበልጥ የተበላሹና ያዘቀጡ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደሚጥር አትዘንጋ። “ክፉዎችና አታላዮች . . . እየሳቱና እያሳቱ፣ በክፋትም ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ።” (2 ጢሞቴዎስ 3:13፤ ራእይ 20:1-3) ስለዚህ በሰይጣን የተንኮል ዘዴዎች እንዳንታለል ምንጊዜም ንቁዎች መሆን ያስፈልገናል።—ዘፍጥረት 6:13፤ መዝሙር 11:5፤ ሮሜ 1:24-32
11. ስለ መናፍስታዊ ድርጊት ትክክለኛውን ነገር የሚያውቅ ሰውም እንኳ ካልተጠነቀቀ ወጥመድ ውስጥ ሊገባ የሚችለው በምን መንገዶች ነው?
11 በማንኛውም ዓይነት መናፍስታዊ ድርጊት ተካፋይ የሚሆኑ ይኸውም የሚያሟርቱ፣ የሚጠነቁሉ ወይም ከሙታን ጋር ለመገናኘት የሚሞክሩ ሁሉ በይሖዋ ፊት የተጠሉ መሆናቸውንም እናውቃለን። ዘዳግም 18:10-12) ስለሆነም ጠንቋዮችን ለመጠየቅ ፈጽሞ አናስብም፤ እንዲሁም ቤታችን መጥተው አጋንንታዊ ድርጊት እንዲፈጽሙ አንፈቅድላቸውም። ይሁን እንጂ በቴሌቪዥን ቢታዩ ወይም በኢንተርኔት ቢያጋጥሙን የሚናገሩትን ዝም ብለን እናዳምጣለን? አንድ ጠንቋይ ምንም ዓይነት ሕክምና እንዲያደርግልን ባንፈቅድም እንኳ ልጅ በምንወልድበት ጊዜ ከክፉ ይጠብቀዋል ብለን በማሰብ እጁ ላይ ክታብ እናስራለን? መጽሐፍ ቅዱስ በድግምት ሰውን ማፍዘዝን እንደሚያወግዝ እያወቅን አንድ የሥነ ልቦና ባለሙያ አእምሯችንን እንዲቆጣጠር እንፈቅድለታለን?—ገላትያ 5:19-21
(12. (ሀ) ሙዚቃ ስህተት እንደሆኑ የምናውቃቸውን ሐሳቦች እንድናስብ ተጽዕኖ ሊያደርግብን የሚችለው እንዴት ነው? (ለ) የአንድ ሰው አለባበስ፣ የፀጉር አበጣጠርም ሆነ አነጋገር ይሖዋ የማይወዳቸውን ሰዎች የአኗኗር ዘይቤ እንደሚያደንቅ ሊያሳይ የሚችለው እንዴት ነው? (ሐ) በሰይጣን ስውር ዘዴዎች እንዳንታለል የምንፈልግ ከሆነ ምን ማድረግ ይኖርብናል?
12 መጽሐፍ ቅዱስ ዝሙትንና ማንኛውንም ዓይነት ርኩሰት የሚያበረታታ ወሬ በመካከላችን ሊሰማ እንደማይገባ ይገልጻል። (ኤፌሶን 5:3-5) ነገር ግን አንድ ደስ የሚል ዘፈን ወይም የሚነሽጥ ውዝዋዜ ወይም ቀስቃሽ ሙዚቃ ይህንን መልእክት በሚያስተላልፍ መንገድ ተቀነባብሮ ቢቀርብስ? ሳይጋቡ የጾታ ግንኙነት ማድረግን፣ ለደስታ ሲባል ዕፅ መውሰድን ወይም ሌሎች የኃጢአት ድርጊቶችን የሚያበረታቱ ዜማዎችን እናንጐራጉር ይሆን? ወይም እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉትን ሰዎች አኗኗር መከተል እንደሌለብን ብናውቅም አለባበሳቸውን፣ የፀጉር አበጣጠራቸውን ወይም አነጋገራቸውን በመኮረጅ እነርሱን የመምሰል አዝማሚያ እንዳለን እናሳያለን? ሰይጣን ሰዎችን በማባበል የእሱን ብልሹ አስተሳሰብ እንዲያንጸባርቁ ለማድረግ የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች እንዴት የረቀቁ ናቸው! (2 ቆሮንቶስ 4:3, 4) በሰይጣን ስውር ዘዴዎች እንዳንታለል ከፈለግን ይህን ዓለም ከመከተል መራቅ ይኖርብናል። ‘የዚህ ጨለማ ዓለም ገዥዎች’ እነማን እንደሆኑ ዘወትር ማስታወስና የሚያሳድሩብንን ተጽዕኖ ለመቋቋም በቁርጠኝነት መጋደል ያስፈልገናል።—1 ጴጥሮስ 5:8
አሸናፊ ለመሆን መታጠቅ
13. ፍጽምና የጎደለን ሰዎች ብንሆንም እንኳ ሰይጣን የሚገዛውን ዓለም ማሸነፍ የምንችለው እንዴት ነው?
13 ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት ለሐዋርያቱ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሏቸዋል። (ዮሐንስ 16:33) እነሱም አሸናፊዎች መሆን ይችላሉ። ከ60 ዓመት ገደማ በፊት ሐዋርያው ዮሐንስ “ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በስተቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማነው?” ሲል ጽፎ ነበር። (1 ዮሐንስ 5:5) እንዲህ ያለውን እምነት የምናሳየው የኢየሱስን ትእዛዛት በማክበርና ልክ እንደ ኢየሱስ በአምላክ ቃል ላይ በመታመን ነው። ሌላስ ምን ያስፈልጋል? በኢየሱስ የራስነት ሥልጣን በሚመራው ጉባኤ ውስጥ ታቅፈን መኖር አለብን። ኃጢአት ስንሠራ ከልብ ንስሐ መግባትና በኢየሱስ መሥዋዕት አማካኝነት የአምላክን ይቅርታ ለማግኘት መጣር ይኖርብናል። ፍጽምና የጎደለንና ስሕተት የምንሠራ ብንሆንም እንኳ በዚህ መንገድ እኛም አሸናፊዎች መሆን እንችላለን።—መዝሙር 130:3, 4
14. ኤፌሶን 6:13-17ን አንብብና በዚህ አንቀጽ ውስጥ የሚገኙትን ጥያቄዎችና ጥቅሶች በመጠቀም እያንዳንዱ መንፈሳዊ የጦር ዕቃ የሚያስገኝልህን ጥቅም መርምር።
ኤፌሶን 6:13-17ን አውጣና ስለዚህ የጦር ዕቃ የተሰጠውን መግለጫ አንብብ። ከዚያም ከታች የቀረቡትን ጥያቄዎች በመመለስ እያንዳንዱ የጦር ዕቃ እንዴት ጥበቃ ሊያስገኝልህ እንደሚችል አስብ።
14 አሸናፊዎች መሆን እንድንችል “የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ” መልበስ ያስፈልገናል። እባክህ‘እውነትን የታጠቀ ወገብ’
እውነትን የምናውቅ ብንሆንም እንኳ አዘውትሮ ማጥናት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ ማሰላሰልና መሰብሰብ ጥበቃ ሊያስገኝልን የሚችለው እንዴት ነው? (1 ቆሮንቶስ 10:12, 13፤ 2 ቆሮንቶስ 13:5፤ ፊልጵስዩስ 4:8, 9)
‘የጽድቅ ጥሩር’
እዚህ ላይ የተጠቀሰው የማን የጽድቅ መሥፈርት ነው? (ራእይ 15:3)
አንድ ሰው የይሖዋን የጽድቅ መሥፈርቶች አለመከተሉ መንፈሳዊ ጉዳት ሊያስከትልበት የሚችለው እንዴት እንደሆነ በምሳሌ አስረዳ። (ዘዳግም 7:3, 4፤ 1 ሳሙኤል 15:22, 23)
‘የሰላምን ወንጌል የተጫሙ እግሮች’
አምላክ ሰላምን ለማምጣት ስላደረገው ዝግጅት ለሌሎች ለመንገር እግሮቻችን ዘወትር ወደ ሰዎች እንዲወስዱን ማድረጋችን ጥበቃ የሚያስገኝልን እንዴት ነው? (መዝሙር 73:2, 3፤ ሮሜ 10:15፤ 1 ጢሞቴዎስ 5:13)
‘የእምነት ጋሻ’
የጸና እምነት ካለን ጥርጣሬ ወይም ፍርሃት እንዲያድርብን ሊያደርጉ የሚችሉ ተጽዕኖዎች ሲያጋጥሙን ምን ምላሽ እንሰጣለን? (2 ነገሥት 6:15-17፤ 2 ጢሞቴዎስ 1:12)
‘የመዳን ራስ ቁር’
የመዳን ተስፋ አንድ ሰው ከልክ በላይ ስለ ቁሳዊ ሀብት በማሰብ ወጥመድ ውስጥ እንዳይገባ ሊረዳው የሚችለው እንዴት ነው? (1 ጢሞቴዎስ 6:7-10, 19)
‘የመንፈስ ሰይፍ’
በእኛም ሆነ በሌሎች መንፈሳዊነት ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ለመቋቋም ዘወትር በምን ልንታመን ይገባናል? (መዝሙር 119:98፤ ምሳሌ 3:5, 6፤ ማቴዎስ 4:3, 4)
በመንፈሳዊ ውጊያ ለማሸነፍ አስፈላጊ የሆነው ሌላው ነገር ምንድን ነው? ይህንንስ ምን ያህል ልንጠቀምበት ይገባል? ለእነማንስ? (ኤፌሶን 6:18, 19)
15. በመንፈሳዊው ውጊያ የማጥቃት እርምጃ መውሰድ የምንችለው እንዴት ነው?
15 የክርስቶስ ወታደሮች እንደመሆናችን መጠን መንፈሳዊ ውጊያ የሚያካሂድ የአንድ ትልቅ ሠራዊት አባሎች ነን። ዘወትር ንቁ ከሆንና የተሟላውን የአምላክ የጦር ትጥቅ በደንብ ከተጠቀምንበት በጦርነቱ ከሚወድቁት ተሸናፊዎች መካከል አንሆንም። ከዚህ ይልቅ አብረውን አምላክን ለሚያገለግሉት የብርታት ምንጭ እንሆንላቸዋለን። በውጊያው የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ ይኸውም ሰይጣን በጣም የሚቃወመውን የአምላክን መንግሥት ምሥራች ለማስፋፋት ዝግጁ እንሆናለን።
የክለሳ ውይይት
• የይሖዋ አምላኪዎች በዓለም ውስጥ ከሚቀሰቀሱ ግጭቶች ፍጹም ገለልተኛ የሚሆኑት ለምንድን ነው?
• ሰይጣን ክርስቲያኖችን ለመንፈሳዊ ውድቀት ለመዳረግ የሚጠቀምባቸው አንዳንድ የረቀቁ ዘዴዎች ምንድን ናቸው?
• አምላክ ያዘጋጀልን መንፈሳዊ የጦር ትጥቅ በምናደርገው መንፈሳዊ ውጊያ ከጉዳት ሊጠብቀን የሚችለው እንዴት ነው?
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 76 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]
ብሔራት ወደ አርማጌዶን እየተሰበሰቡ ነው