የጥምቀትህ ትርጉም
ምዕራፍ አሥራ ሁለት
የጥምቀትህ ትርጉም
1. ጥምቀት እያንዳንዳችን ልናስብበት የሚገባ ጉዳይ የሆነው ለምንድን ነው?
በ29 ከክርስቶስ ልደት በኋላ፣ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ ውኃ ውስጥ በመጥለቅ ተጠመቀ። ይህ ሲሆን ይሖዋ ይመለከት የነበረ ከመሆኑም በላይ በድርጊቱ መደሰቱን ገልጿል። (ማቴዎስ 3:16, 17) በዚህ መንገድ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ሊከተሉት የሚገባ ምሳሌ ትቷል። ከዚያ ሦስት ዓመት ተኩል ያህል ቆይቶ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሚከተለውን መመሪያ ሰጠ:- “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል፤ ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው።” (ማቴዎስ 28:18, 19) ኢየሱስ እዚህ ላይ በሰጠው መመሪያ መሠረት ተጠምቀሃል? ካልተጠመቅክ ይህን እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀህ ነው?
2. ከጥምቀት ጋር በተያያዘ መልስ ማግኘት የሚያሻቸው ጥያቄዎች የትኞቹ ናቸው?
2 የተጠመቅክም ሆንክ ገና ለመጠመቅ እየተዘጋጀህ ያለህ፣ ይሖዋን ለማገልገልና ጽድቅ በሚሰፍንበት አዲስ ዓለም ውስጥ ለመኖር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የጥምቀትን ትርጉም በትክክል መረዳት እንደሚያስፈልገው መገንዘብ ይኖርብሃል። መልስ ከሚያሻቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:- ዛሬ ያለው ክርስቲያናዊ ጥምቀት ከኢየሱስ ጥምቀት ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው? “በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም” መጠመቅ ሲባል ምን ማለት ነው? ክርስቲያናዊ ጥምቀት ከያዘው ትርጉም ጋር በሚስማማ መንገድ መኖር ምን ማድረግን ይጠይቃል?
ዮሐንስ ያከናወነው ጥምቀት
3. የዮሐንስ ጥምቀት ለእነማን ብቻ የተወሰነ ነበር?
3 ኢየሱስ ከመጠመቁ ከስድስት ወራት ገደማ በፊት አጥማቂው ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” እያለ ይሰብክ ነበር። (ማቴዎስ 3:1, 2) በዚያ አካባቢ የነበሩ ሰዎች ዮሐንስ የተናገረውን በመስማት እርምጃ ወስደዋል። ኃጢአታቸውን በመናዘዝ ንስሐ የገቡ ከመሆኑም በላይ በዮርዳኖስ ወንዝ ለመጠመቅ ወደ ዮሐንስ ይሄዱ ነበር። ይህ ጥምቀት ለአይሁዶች ብቻ የተወሰነ ነበር።—ሉቃስ 1:13-16፤ የሐዋርያት ሥራ 13:23, 24
4. በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት አይሁዳውያን በአስቸኳይ ንስሐ መግባት ያስፈለጋቸው ለምን ነበር?
4 እነዚያ አይሁዶች በአስቸኳይ ንስሐ መግባት ያስፈልጋቸው ነበር። በ1513 ከክርስቶስ ልደት በፊት አባቶቻቸው በሲና ተራራ ከይሖዋ አምላክ ጋር ብሔራዊ ቃል ኪዳን ገብተው ነበር። ይሁን እንጂ በሠሯቸው ከባድ ኃጢአቶች የተነሳ ይህ ቃል ኪዳን ያስከተለባቸውን ኃላፊነት ሳይወጡ በመቅረታቸው ቃል ኪዳኑ ኰንኗቸዋል። በመሆኑም አይሁዳውያኑ በኢየሱስ ዘመን በአደገኛ ሁኔታ ላይ ይገኙ ነበር። ሚልክያስ በትንቢት የተናገረው “ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን” ቀርቦ ነበር። በ70 ከክርስቶስ ልደት በኋላ የሮማ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን፣ ቤተ መቅደሷንና ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አይሁዶችን በደመሰሰበት ወቅት ይመጣል ተብሎ የተነገረው “ቀን” መጥቷል። ለእውነተኛው አምልኮ ቅንዓት የነበረው አጥማቂው ዮሐንስ “ለጌታ የተገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት” ከዚህ ጥፋት አስቀድሞ ተልኳል። ሕዝቡ በሙሴ ሕግ ቃል ኪዳን ላይ ከፈጸሙት ኃጢአት ንስሐ መግባትና ይሖዋ የላከላቸውን ልጁን ኢየሱስን ለመቀበል ዝግጁ መሆን አስፈልጓቸው ነበር።—ሚልክያስ 4:4-6፤ ሉቃስ 1:17፤ የሐዋርያት ሥራ 19:4
5. (ሀ) ኢየሱስ ሊጠመቅ ሲል ዮሐንስ ጥያቄ ያነሳው ለምንድን ነው? (ለ) የኢየሱስ ጥምቀት ምን ያመለክታል?
5 ለመጠመቅ ወደ ዮሐንስ ከመጡት አንዱ ኢየሱስ ነበር። ሆኖም ማቴዎስ 3:13-15) ኢየሱስ ምንም ኃጢአት ስለሌለበት በውኃ መጠመቁ ለኃጢአት ንስሐ መግባቱን ሊያመለክት አይችልም። በተጨማሪም ራሱን ለይሖዋ የወሰነ ሕዝብ አባል ስለነበረ ሕይወቱን ለአምላክ መወሰን አያስፈልገውም። ከዚህ ይልቅ በ30 ዓመቱ መጠመቁ የሰማያዊ አባቱን ተጨማሪ ፈቃድ ለማድረግ ራሱን ለእርሱ ማቅረቡን የሚያመለክት በዓይነቱ ልዩ የሆነ እርምጃ ነበር።
ኢየሱስ መጠመቅ ያስፈለገው ለምንድን ነው? ኢየሱስ የሚናዘዘው አንድም ኃጢአት እንደሌለው ዮሐንስ ያውቅ ስለነበር “ይህማ አይሆንም፤ እኔ ባንተ መጠመቅ ሲያስፈልገኝ እንዴት አንተ ወደ እኔ ትመጣለህ?” ሲል ተናግሯል። ይሁንና የኢየሱስ ጥምቀት ሌላ ነገር የሚያመለክት ነበር። ስለሆነም ኢየሱስ “ግድ የለም ፍቀድልኝ፤ ይህን በማድረግ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” ብሎ መለሰለት። (6. ኢየሱስ፣ አምላክ ለእሱ ያለውን ፈቃድ የመፈጸሙን ጉዳይ ምን ያህል አክብዶ ተመልክቶታል?
6 አምላክ ለክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ፈቃድ ከመንግሥቱ ጋር የተያያዘ ሥራን ማከናወንን የሚጨምር ነበር። (ሉቃስ 8:1) በተጨማሪም ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወቱን ቤዛና የአዲሱ ቃል ኪዳን መሠረት አድርጎ መስጠትን የሚያካትት ነበር። (ማቴዎስ 20:28፤ 26:26-28፤ ዕብራውያን 10:5-10) ኢየሱስ ጥምቀቱ ያለውን ትርጉም አክብዶ ተመልክቶታል። ትኩረቱ በሌሎች ነገሮች እንዲሰረቅ አልፈቀደም። የአምላክን መንግሥት የመስበኩን ሥራ ዋነኛ ተግባሩ በማድረግ እስከ ምድራዊ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ በታማኝነት የአባቱን ፈቃድ ፈጽሟል።—ዮሐንስ 4:34
የክርስቲያን ደቀ መዛሙርት የውኃ ጥምቀት
7. በ33 ከዋለው የጰንጠቆስጤ ዕለት አንስቶ ክርስቲያኖች ከጥምቀት ጋር በተያያዘ ምን እንዲያከናውኑ ታዘዋል?
7 የመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በዮሐንስ በውኃ የተጠመቁ ሲሆን የሰማያዊው መንግሥት አባላት ይሆኑ ዘንድ ወደ ኢየሱስ እንዲሄዱ ተነግሯቸዋል። (ዮሐንስ 3:25-30) እነዚህ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ በሰጣቸው መመሪያ አንዳንድ ሰዎችን ያጠመቁ ሲሆን ይህ ጥምቀት ከዮሐንስ ጥምቀት ጋር ተመሳሳይ ትርጉም ነበረው። (ዮሐንስ 4:1, 2) ነገር ግን በ33 ከዋለው የጰንጠቆስጤ ዕለት ጀምሮ “በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም” እንዲያጠምቁ የተሰጣቸውን ተልእኮ መፈጸም ጀመሩ። (ማቴዎስ 28:19) ይህ ምን ትርጉም እንዳለው መመርመርህ በእጅጉ ይጠቅምሃል።
8. ‘በአብ ስም’ መጠመቅ ሲባል ምን ማለት ነው?
8 ‘በአብ ስም’ መጠመቅ ሲባል ምን ማለት ነው? ስሙን፣ ቦታውን፣ ሥልጣኑን፣ ዓላማውንና ሕጎቹን መቀበል ማለት ነው። ይህ ምን ነገሮችን እንደሚያካትት ተመልከት። (1) ስሙን በተመለከተ ዘፀአት 6:3 [የ1879 ትርጉም] “በስሜም እግዚእ ይሖዋ አልታወቅሁላቸውም” ይላል። (2) ቦታውን በተመለከተ 2 ነገሥት 19:15 “እግዚአብሔር ሆይ፤ . . . አምላክ አንተ ብቻ ነህ” ሲል ይገልጻል። (3) ሥልጣኑን በተመለከተ ራእይ 4:11 “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤ ክብርና ሞገስ፣ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና፤ በፈቃድህም ተፈጥረዋልና፤ ሆነዋልምና” ይላል። (4) በተጨማሪም ይሖዋ እኛን ከኃጢአትና ከሞት ለመታደግ ዓላማ ያለው ሕይወት ሰጪ አምላክ መሆኑን አምነን መቀበል ይኖርብናል። “ማዳን የእግዚአብሔር ነው።” (መዝሙር 3:8፤ 36:9) (5) ዋነኛው ሕግ ሰጪ ይሖዋ መሆኑን አምነን መቀበል ያስፈልገናል። “እግዚአብሔር ዳኛችን ነው፤ እግዚአብሔር ሕግ ሰጪያችን ነው፤ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው።” (ኢሳይያስ 33:22) ይሖዋ ይህ ሁሉ ሥልጣን ያለው አምላክ በመሆኑ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ” የሚል ማሳሰቢያ ተሰጥቶናል።—ማቴዎስ 22:37
9. ‘በወልድ ስም’ መጠመቅ ማለት ምን ማለት ነው?
9 ‘በወልድ ስም’ መጠመቅ ሲባል ምን ማለት ነው? የኢየሱስ ክርስቶስን ስም፣ ቦታና ሥልጣን ማወቅ ማለት ነው። ኢየሱስ የተባለው ማቴዎስ 16:16፤ ቈላስይስ 1:15, 16) ዮሐንስ 3:16 ይህን ልጅ አስመልክቶ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን [ሊቤዥ የሚችለውን የሰው ዘር] እንዲሁ ወዶአልና” ይላል። ኢየሱስ ታማኝነቱን ጠብቆ በመሞቱ አምላክ ከሞት በማስነሳት ተጨማሪ ሥልጣን ሰጥቶታል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደገለጸው አምላክ ኢየሱስን በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ‘እጅግ ከፍ በማድረግ’ ከእሱ ቀጥሎ ያለውን ከፍተኛ ቦታ ሰጥቶታል። ‘ጒልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም መንበርከክ፣ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ መመስከር ያለበት’ በዚህ ምክንያት ነው። (ፊልጵስዩስ 2:9-11) ይህም ከይሖዋ የሚመነጩትን የኢየሱስ ትእዛዛት መታዘዝ ማለት ነው።—ዮሐንስ 15:10
ስሙ “ይሖዋ አዳኝ ነው” የሚል ትርጉም አለው። የአምላክ አንድያ ልጅ ማለትም የአምላክ ፍጥረት መጀመሪያ በመሆኑ የላቀ ቦታ ሊኖረው ችሏል። (10. “በመንፈስ ቅዱስ ስም” መጠመቅ ሲባል ምን ማለት ነው?
10 “በመንፈስ ቅዱስ ስም” መጠመቅ ሲባል ምን ማለት ነው? መንፈስ ቅዱስ የሚጫወተውን ሚና እንዲሁም የሚያከናውነውን ተግባር መረዳትና መቀበል ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስ ምንድን ነው? ይሖዋ ዓላማውን ዳር ለማድረስ የሚጠቀምበት ኃይል ነው። ኢየሱስ ተከታዮቹን “እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ [“ረዳት፣” NW] ይሰጣችኋል፤ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው” ብሏቸዋል። (ዮሐንስ 14:16, 17) ይህ መንፈስ ምን ማከናወን እንዲችሉ ይረዳቸዋል? ኢየሱስ “መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” ሲል ነግሯቸው ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 1:8) ከዚህም በተጨማሪ ይሖዋ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲጻፍ አድርጓል። “ትንቢት ከእግዚአብሔር የተላኩ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናገሩት እንጂ ከቶ በሰው ፈቃድ የመጣ አይደለም።” (2 ጴጥሮስ 1:21) ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና መንፈስ ቅዱስ የሚጫወተውን ሚና አምነን እንቀበላለን። እንዲሁም ይሖዋ ‘የመንፈስ ፍሬን’ ይኸውም ‘ፍቅርን፣ ደስታን፣ ሰላምን፣ ትዕግሥትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ ታማኝነትን፣ ገርነትንና ራስን መግዛትን’ ማፍራት እንድንችል እንዲረዳን መጠየቃችን መንፈስ ቅዱስ የሚጫወተውን ሚና አምነን እንደተቀበልን የምናሳይበት ሌላው መንገድ ነው።—ገላትያ 5:22, 23
11. (ሀ) በዘመናችን የጥምቀት ትክክለኛ ትርጉም ምንድን ነው? (ለ) ጥምቀት ከመሞትና ከሞት ከመነሳት ጋር ሊመሳሰል የሚችለው እንዴት ነው?
11 ኢየሱስ በሰጠው መመሪያ መሠረት ከ33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ጀምሮ የተጠመቁት የመጀመሪያዎቹ አማኞች አይሁዶችና ወደ አይሁድ ሃይማኖት የተለወጡ ሰዎች ነበሩ። ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ክርስቲያን ደቀ መዝሙር የመሆኑ ውድ አጋጣሚ ለሣምራውያንም ተከፈተ። በ36 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ጥሪው ከዚያም አልፎ ያልተገረዙ አሕዛብን እንዲያካትት ተደረገ። ሣምራውያንና አሕዛብ ከመጠመቃቸው በፊት የልጁ ደቀ መዛሙርት ሆነው ይሖዋን ለማገልገል በግል ራሳቸውን ለእርሱ መወሰን ነበረባቸው። ክርስቲያናዊ ጥምቀት እስከ ዛሬም ድረስ ትርጉሙ ይኸው ሆኖ ቆይቷል። ጥምቀት ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ መቀበርን የሚያመለክት በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ውኃ ውስጥ መጥለቅ አንድ ሰው ራሱን ለአምላክ በመወሰን ለሚወስደው እርምጃ ተስማሚ ተምሳሌት ነው። በምትጠመቅበት ጊዜ ውኃ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መጥለቅህ ለቀድሞ አኗኗርህ መሞትህን ያመለክታል። ከውኃው ውስጥ መውጣትህ ደግሞ የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ሕያው እንደሆንክ ያሳያል። ይህን “አንድ ጥምቀት” እውነተኛ ክርስቲያኖች በሙሉ ሊጠመቁት ይገባል። በዚህ መንገድ ክርስቲያን የይሖዋ ምሥክሮች ወይም በአምላክ የተሾሙ አገልጋዮች ይሆናሉ።— ኤፌሶን 4:5፤ 2 ቆሮንቶስ 6:3, 4
12. ክርስቲያናዊ ጥምቀት ከምን ጋር ይመሳሰላል? እንዴትስ?
1 ጴጥሮስ 3:21) መርከቡ ኖኅ አምላክ የሰጠውን ሥራ በታማኝነት እንደፈጸመ የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ነበር። የመርከቡ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ “በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም በውሃ ተጥለቅልቆ ጠፋ።” (2 ጴጥሮስ 3:6) ሆኖም ኖኅና ቤተሰቡ ማለትም ‘ስምንት ሰዎች ከጥፋት ውሃው ተርፈዋል።’—1 ጴጥሮስ 3:20
12 ይህ ዓይነቱ ጥምቀት በአምላክ ፊት ለመዳን የሚያበቃ ትልቅ ዋጋ አለው። ለምሳሌ ያህል ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ ኖኅ ራሱና ቤተሰቡ ከጥፋት ውኃ የዳኑበትን መርከብ እንደሠራ ከገለጸ በኋላ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ይህም ውሃ አሁን የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ያድናችኋል፤ ይህም የሰውነትን እድፍ በማስወገድ ሳይሆን በንጹሕ ኀሊና በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርብ መማፀኛ ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው።” (13. አንድ ክርስቲያን በጥምቀት አማካኝነት ከምን ይድናል?
13 በአሁኑ ጊዜ ከሞት በተነሳው በክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት ራሳቸውን ለይሖዋ የወሰኑ ሰዎች ይህን እርምጃ መውሰዳቸውን ለማሳየት ይጠመቃሉ። አምላክ ለዘመናችን ያለውን ፈቃድ የሚፈጽሙ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ካለው ክፉ ዓለም ድነዋል። (ገላትያ 1:3, 4) አሁን ካለው ክፉ ሥርዓት ጋር አብሮ የመጥፋት ዕጣ አይጠብቃቸውም። ከዚህ ጥፋት የተጠበቁ ከመሆናቸውም በላይ በአምላክ ፊት በጎ ሕሊና ማግኘት ችለዋል። ሐዋርያው ዮሐንስ “ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል” በማለት ለአምላክ አገልጋዮች ዋስትና ሰጥቷል።—1 ዮሐንስ 2:17
ኃላፊነቶቻችንን መፈጸም
14. ጥምቀት በራሱ ለመዳን ዋስትና የማይሆነው ለምንድን ነው?
14 መጠመቅ ብቻውን ለመዳን ዋስትና ይሆናል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው። ጥምቀት ዋጋ የሚኖረው አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ራሱን ለይሖዋ ከወሰነና ከዚያ በኋላ እስከ መጨረሻው ድረስ የአምላክን ፈቃድ ካደረገ ብቻ ነው። “እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።”—ማቴዎስ 24:13
15. (ሀ) በአሁኑ ጊዜ አምላክ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች ያለው ፈቃድ ምንድን ነው? (ለ) ክርስቲያን ደቀ መዝሙር መሆን በሕይወታችን ውስጥ ምን ቦታ ሊሰጠው ይገባል?
15 አምላክ ለኢየሱስ የነበረው ፈቃድ ሰብዓዊ ሕይወቱን የሚጠቀምበትንም መንገድ የሚያጠቃልል ነበር። ሕይወቱ በሞት አማካኝነት መሥዋዕት ሆኖ መቅረብ ነበረበት። እኛም ሰውነታችንን ለአምላክ እንደ መሥዋዕት አድርገን ማቅረብና የአምላክን ፈቃድ በመፈጸም የራስን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ የሚጠይቅ አኗኗር መከተል ይኖርብናል። (ሮሜ 12:1, 2) አልፎ አልፎም እንኳ ቢሆን በዙሪያችን ያለው ዓለም የሚያደርጋቸውን ነገሮች ሆን ብለን ብናደርግ ወይም አምላክን ለይስሙላ ያህል ብቻ እያገለገልን የግል ጥቅማችንን ብናሳድድ የአምላክን ፈቃድ እየፈጸምን ነው ብለን አፋችንን ሞልተን መናገር አንችልም። (1 ጴጥሮስ 4:1-3፤ 1 ዮሐንስ 2:15, 16) አንድ አይሁዳዊ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ አለብኝ ብሎ ኢየሱስን በጠየቀው ጊዜ ኢየሱስ ንጹሕ ሥነ ምግባር ይዞ የመኖርን አስፈላጊነት የገለጸ ቢሆንም ክርስቲያን ደቀ መዝሙር ወይም የኢየሱስ ተከታይ መሆን ከዚያ ይበልጥ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁሟል። ይህ ጉዳይ በሕይወት ውስጥ ከሁሉ የላቀ ቦታ የሚሰጠው ነገር መሆን አለበት። ቁሳዊ ነገሮችን ከዚህ ማስቀደም ተገቢ አይሆንም።—ማቴዎስ 19:16-21
16. (ሀ) ሁሉም ክርስቲያኖች ከመንግሥቱ ጋር በተያያዘ ምን ኃላፊነት አለባቸው? (ለ) በገጽ 116 እና 117 ላይ በሚገኘው ሥዕላዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው የመንግሥቱን ሥራ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማከናወን የሚቻልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው? (ሐ) በምሥክርነቱ ሥራ በሙሉ ልብ መሳተፋችን ምን ያሳያል?
16 አምላክ ለኢየሱስ የነበረው ፈቃድ ከመንግሥቱ ጋር የተያያዘ በጣም አስፈላጊ የሆነ ሥራ መሥራትን እንደሚጨምር ማስታወስ ይኖርብናል። ኢየሱስ ራሱ ንጉሥ እንዲሆን ተቀብቶ ነበር። ይሁን እንጂ ምድር ላይ ሳለ ስለ መንግሥቱ በቅንዓት ይመሠክር ነበር። እኛም ተመሳሳይ የምሥክርነት ሥራ ተሠጥቶናል። በዚህ ሥራ በሙሉ ልባችን የምንሳተፍበት በቂ ምክንያት አለን። እንደዚህ በማድረግ የይሖዋን ሉዓላዊነት እንደምንደግፍና ለሰዎች ፍቅር እንዳለን እናሳያለን። (ማቴዎስ 22:36-40) ከዚህም በላይ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ከሆኑት በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር አንድ እንደሆንን እናሳያለን። ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን በዚህ መንግሥት ምድራዊ ግዛት ሥር ወደሚገኘው የዘላለም ሕይወት ግብ ለመድረስ በቆራጥነት ወደፊት እንገሰግሳለን።
የክለሳ ውይይት
• በኢየሱስ ጥምቀትና በአሁኑ ጊዜ ባለው ጥምቀት መካከል ምን ተመሳሳይነትና ልዩነት አለ?
• “በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም” መጠመቅ ሲባል ምን ማለት ነው?
• ክርስቲያናዊ ጥምቀት የሚያስከትላቸውን ኃላፊነቶች መፈጸም ምንን ይጨምራል?
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 116 እና 117 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]
መንግሥቱን ለማወጅ የሚያስችሉ አንዳንድ መንገዶች
ከቤት ወደ ቤት
ለዘመዶች
ለሥራ ባልደረቦች
ለትምህርት ቤት ጓደኞች
መንገድ ላይ
ፍላጎት ያሳዩትን ተመልሶ በማነጋገር
በቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት