በይሖዋ ዙፋን ፊት የቆሙ “እጅግ ብዙ ሰዎች”
ምዕራፍ 13
በይሖዋ ዙፋን ፊት የቆሙ “እጅግ ብዙ ሰዎች”
1. (ሀ) ከክርስትና ዘመን በፊት የነበሩት የአምላክ አገልጋዮችም ሆኑ 144, 000ዎቹ ሽልማታቸውን ከማግኘታቸው በፊት በእነርሱ ላይ መድረስ ያለበት ነገር ምንድን ነው?(ለ) ነገር ግን “ታላቁ መከራ” በሚጀምርበት ጊዜ የሚኖሩት “እጅግ ብዙ ሰዎች” ምን ለመሆን ይችላሉ?
ከአቤል ጀምሮ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የነበሩት ታማኝ የአምላክ አገልጋዮች የእርሱን ፈቃድ ማድረግን በሕይወታቸው ውስጥ አንደኛ ቦታ ቢሰጡትም ሁሉም መሞትና ትንሣኤን መጠበቅ ነበረባቸው። ከክርስቶስ ጋር በሰማያዊ መንግሥቱ የሚተባበሩት 144,000ዎችም ሽልማታቸውን ከማግኘታቸው በፊት መሞት አለባቸው። ሐዋርያው ዮሐንስ ግን በራእይ ከዚህ የተለየ ሁኔታ ተመልክቷል። “ከታላቁ መከራ” በሕይወት አልፈው ሞትን ሳይቀምሱ ለዘላለም የመኖር ዕድል የሚያገኙ “እጅግ ብዙ ሰዎች” አይቷል። — ራእይ 7:9–17
“እጅግ ብዙ ሰዎች” የተባሉትን ማንነት ለይቶ ማወቅ
2. በራእይ 7:9 ላይ የተጠቀሱት “እጅግ ብዙ ሰዎች” እነማን መሆናቸው በግልጽ ለመረዳት የተቻለው እንዴት ነው?
በማቴዎስ 25:31–46 በተገለጸው የኢየሱስ ምሳሌ የተጠቀሱት “በጎች” እና በዮሐንስ 10:16 ላይ የተጠቀሱት “ሌሎች በጎች” አሁን በሕይወት ያሉና በምድር ለዘላለም የመኖር ዕድል ያላቸው ሰዎች እንደሆኑ በ1923 ለመረዳት ተቻለ። በ1931 ላይ በሕዝቅኤል 9:1–11 ያሉት የጸሐፊ ቀለም ቀንድ የያዘው ሰው ግምባራቸው ላይ ምልክት ያደረገባቸው ሰዎች በማቴዎስ ምዕራፍ 25 ላይ ከተጠቀሱት “በጎች” ጋር አንድ እንደሆኑ ተገለጸ። ከዚያም በ1935 ላይ በራእይ 7:9–17 የተገለጹት “እጀግ ብዙ ሰዎች” ኢየሱስ ስለ በጎቹና ስለ ፍየሎቹ በተናገረው ምሳሌ ላይ ከተጠቀሱት “በጎች” ጋር አንድ መሆናቸውን ማስታዋል ተቻለ። እንደነዚህ ያሉት በግ መሰል ግለሰቦች መምጣት መጀመራቸውን ገና ከ1923 ጀምሮ መረዳት ቢቻልም ቁጥራቸው በፍጥነት ማደግ የጀመረው ከ1935 በኋላ ነው። በዛሬው ጊዜ መለኮታዊ ሞገስ ያገኙትና “የሌሎች በጎች” ክፍል የሆኑት የእነዚህ “እጅግ ብዙ ሰዎች” አባል ለመሆን የሚፈልጉ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ።
2 የእነዚህን “እጅግ ብዙ ሰዎች” ማንነት መረዳት ለብዙ ዓመታት አዳጋች ሆኖ ነበር። ነገር ግን ከዚህ ጋር የተያያዙ ሌሎች ትንቢቶች ትርጉማቸው በየጊዜው ግልጽ እየሆነ መሄዱ ማንነታቸውን ለማወቅ መንገዱን ጠርጓል።3. ‘በዙፋኑ ፊት መቆማቸው’ ሰማያዊ ክፍል መሆናቸውን የማያሳየው ለምንድን ነው?
3 እነዚህ “እጅግ ብዙ ሰዎች” በራእይ ምዕራፍ 7 መጀመሪያ አካባቢ ራእይ 7:9፤ መዝሙር 11:4፤ ከመዝሙር 100:1, 2 ጋር አወዳድር። በተጨማሪም በኪንግደም ኢንተርሊንየር ላይ ሉቃስ 1:74, 75 እና ሥራ 10:33 በግርክኛ ምን እንደሚል ተመልከት) በተመሳሳይም በማቴዎስ 25:31, 32 ላይ እንደተገለጸው “አሕዛብ ሁሉ” በክርስቶስ ዙፋን ፊት ለመሰብሰብ በሰማይ መሆን አያስፈልጋቸውም። እነዚህ “አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ሰዎች” ሰማያዊ ክፍል እንዳልሆኑ ራእይ 7:4–8ንና 14:1–4ን በመመልከት ለመረዳት ይቻላል። በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ከምድር ወደ ሰማይ የሚወሰዱት ሰዎች ትክክለኛ ቁጥራቸው ተገልጿል።
ከተጠቀሱት 144, 000 የመንፈሣዊ እሥራኤል አባላት የተለዩ እንደሆኑ ጥቅሶቹ ያሳያሉ። ዮሐንስ በራእይ ላይ እነዚህ “እጅግ ብዙ ሰዎች” በሰማይ ሆነው አላያቸውም። በአምላክ ዙፋን ፊት (በግሪክኛ ኢኖፕየን ቶው ትሮናው ማለትም “ከዙፋኑ ትዩዩ”) ለመሆን የግድ ሰማይ ውስጥ መገኘት አያስፈልጋቸውም። በዙፋኑ ፊት የቆሙት ሰማይ ሆኖ የሰውን ልጆች እንደሚያያቸው በተናገረው አምላክ አመለካከት ነው። (4. (ሀ) እነርሱ በሕይወት የሚሻገሩት “ታላቅ መከራ” ምንድን ነው? (ለ) በራእይ 7:11, 12 ላይ እንደተገለጸው “እጅግ ብዙ ሰዎች” የሚያደርጉትን ተመልክተው በአምልኮ የሚተባበሯቸው እነማን ናቸው?
4 ዮሐንስ “እጅግ ብዙ ሰዎች” የተባሉት እነማን መሆናቸውን ሲገልጽ “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው” ብሎ ጽፎአል። እነርሱ በሕይወት የሚያልፉት መከራ በምድር ፈጽሞ ታይቶ የማያውቅ “ታላቅ መከራ” ይሆናል። (ራእይ 7:13, 14፤ ማቴዎስ 24:21) ያንን እጅግ አስፈሪ የይሖዋ ቀን በሕይወት የሚያልፉት ሰዎች ያዳናቸው ማን ስለመሆኑ ምንም አይጠራጠሩም። ዮሐንስ በራእዩ ላይ እንዳየው መዳናቸውን ከአምላክና ከበጉ እንዳገኙ በምስጋና ሲገልጹ በሰማይ ያሉት ታማኝ ፍጥረታት ሁሉ “አሜን፣ በረከትና ክብር ጥበብም ምስጋናም ውዳሴም ኃይልም ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፣ አሜን” በማለት እውነተኛውን አንድ አምላክ ከእነርሱ ጋር አንድ ሆነው እንደሚያመልኩ አሳይተዋል። — ራእይ 7:11, 12
ከጥፋቱ ለመዳን ይበቁ እንደሆነ ለመወሰን ይፈተናሉ
5. (ሀ) ከጥፋቱ ከሚድኑት “እጅግ ብዙ ሰዎች” አንዱ ለመሆን ምን እንደሚያስፈልግ እንዴት ለማወቅ እንችላለን? (ለ) በዚህ አንቀጽ መጨረሻ ያሉትን ጥያቄዎች በመመለስ “ከታላቁ መከራ” በሕይወት ለማለፍ ምን እንደሚያስፈልግ ግለጽ።
5 “እጅግ ብዙ ሰዎች” ከጥፋቱ የሚድኑት ከይሖዋ የጽድቅ ሥርዓቶች ጋር በሚስማማ መንገድ ነው። እነዚህ ከጥፋቱ የሚድኑት ሰዎች ምን ልዩ ጠባዮች እንደሚያሳዩ ስለ እነርሱ የሚናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በግልጽ ያመለክታሉ። ስለሆነም ጽድቅ ወዳድ የሆኑ ሁሉ ለመዳን የሚያስችሉ እርምጃዎች ዛሬውኑ ሊወስዱ ይችላሉ። ከዚህ በታች ያሉትን ጥቅሶች ቀደም ሲል አይተናቸዋል። አሁን ግን በተጨማሪዎቹ ጥቅሶች አማካኝነት በጥንቃቄ መርምራቸውና ሁኔታህን ከእነዚህ ትንቢታዊ መግለጫዎች ጋር ለማስማማት ምን ማድረግ እንዳለብህ አስብ:-
በዮሐንስ 10:16 የተጠቀሱት “ሌሎች በጎች ”
አንድ ሰው የኢየሱስን ድምጽ መስማት አለበት ሲባል ምን ማለት ነው? (ዮሐንስ 10:27፤ ማቴዎስ 9:9፤ ኤፌሶን 4:17–24)
ክርስቶስን እንደ እረኛችን አድርገን መቀበላችንን እንዴት ልናሳይ እንችላለን? (ማቴዎስ 23:10, 11)
ኢየሱስ ስለ በጎችና ስለ ፍየሎች በተናገረው ምሳሌ ላይ የተጠቀሱት “በጎች ” (በጎቹ መልካም የሚያደርጉላቸው የክርስቶስ “ወንድሞች” እነማን ናቸው? (ዕብራውያን 2:10, 11፤ 3:1)
“በጎቹ” በምድር ካሉት የክርስቶስ ወንድሞች ጎን የቆሙ መሆናቸውን እንዲያሳዩ የሚጠየቁት በምን ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ጊዜ ነው? በየትኛውስ ሥራ በታማኝነት ይደግፏቸዋል? (ራእይ 12:12, 17፤ ማቴዎስ 24:14፤ 28:19, 20)
የጸሐፊ ቀለም ቀንድ የያዘው ሰው ከጥፋት እንዲድኑ ምልክት ያደረገባቸው ሰዎች (ሕዝቅኤል 9:1–11 )
እነዚህ ሰዎች በምሳሌያዊቱ ኢየሩሳሌም ይኸውም በሕዝበ ክርስትና ውስጥ የሚደረጉትን አስጸያፊ ድርጊቶች እንደማይስማሙባቸው የሚያሳዩት እንዴት ነው? (ራእይ 18:4, 5)
ከአስመሳይ ክርስቲያኖች የሚለያቸውና ለመዳን የሚያበቃቸው “ምልክት” ምን ምን ነገሮችን ይጨምራል? (1 ጴጥሮስ 3:21፤ ማቴዎስ 7:21–27፤ ዮሐንስ 13:35)
6. ዮሐንስ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ስለተባሉት የሰጠው መግለጫ ከጥፋቱ የዳኑበትን ምክንያት ለማወቅ የሚረዳን እንዴት ነው?
6 በራእይ 7:9–15 ላይ ያለው ስለ “እጅግ ብዙ ሰዎች” የተሰጠው መግለጫ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ዝርዝር ማብራሪያዎችንም ይጨምርልናል። ጥቅሶቹ “እጅግ ብዙ ሰዎች” “ከታላቁ መከራ” በኋላ የሚኖራቸውን ሁኔታና አቋም ሲገልጹ ከጥፋቱ ለመዳን ያበቋቸውንም ነገሮች ሳይጠቅሱ አላለፉም።
7. “ከታላቁ መከራ” በፊት ምን ያደርጋሉ? ይህን እንደሚያደርጉ የሚያሳየውስ ምንድን ነው?
ዮሐንስ 1:29፤ 1 ዮሐንስ 2:2) በዚያ መስዋዕት መሠረት በእምነት ራሳቸውን ለአምላክ ወስነዋል፣ ይህንንም በውኃ በመጠመቅ አሳይተዋል። ነጩ ልብሳቸው እንደሚያመለክተውም በአሁኑ ጊዜ በአምላክ ፊት ንጹሕ አቋም ይዘው ይኖራሉ። በአምላክ ልጅ ላይ ያላቸውን እምነት በሕዝብ ፊት ከማሳወቅ ወደኋላ አላሉም። (ማቴዎስ 10:32, 33) ከዚህ ሁሉ ጋር በመስማማት በአምላክ ቤተ መቅደስ ወይም በጽንፈ ዓለማዊው የአምልኮ ቤቱ ውስጥ አምላክን ቀንና ሌሊት እንደሚያመልኩት ተገልጿል። በዚህ መንገድ የእውነተኛው አምልኮ ታማኝ ደጋፊዎችና የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ታሪክ አስመዝግበዋል። — ኢሳይያስ 2:2, 3
7 ከልዩ ልዩ ብሔሮች፣ ጐሳዎች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች የተውጣጡ ቢሆኑም በዙፋኑ ፊት እንደ አንድ ሆነው እንደቆሙና በዙፋኑ የተቀመጠው ይሖዋ የአጽናፈ ዓለም የበላይ ገዥ መሆኑን እየተናገሩ እንደሚያወድሱት ተገልጿል። በአኗኗራቸው የይሖዋ አገዛዝ ታማኝ ደጋፊዎች መሆናቸውን አስመስክረዋል። “ልብሳቸውን አጥበው በበጉ ደም አነጹ” መባሉ የአምላክ በግ የሆነው የኢየሱስ መስዋዕት ኃጢአታቸውን ማስተሰረይ የሚችል መሆኑን እንደሚያምኑ ያመለክታል። (8. ይህ ዕውቀት እንዲጠቅመን ከተፈለገ ምን ማድረግ አለብን?
8 ያንተ ሁኔታ ከእነዚህ ትንቢታዊ ዝርዝር መግለጫዎች ጋር ይስማማልን? ሕይወትህን እዚህ ላይ ከተገለጹት ሁኔታዎች ጋር የበለጠ ለማስማማት ስትል ልታሻሽላቸው የሚያስፈልጉህ ነገሮች ይኖራሉን? ካሉ ያን ማድረግ ያለብህ አሁን ነው!
በመንፈሳዊ ገነት ውስጥ መኖር
9. “እጅግ ብዙ ሰዎች” በአሁኑም ጊዜ ቢሆን የሚያገኟቸውን አስደሳች መንፈሳዊ በረከቶች ዮሐንስ እንዴት አድርጐ ይገልጻቸዋል?
9 “እጅግ ብዙ ሰዎች” ከተባሉት አንዱ በመሆን ከመጪው ጥፋት ለመዳን ተስፋ ከሚያደርጉት መካከል ነህን? ሕይወትህን ከይሖዋ ራእይ 7:16, 17) ይህ በአንተ ላይ የተፈጸመው እንዴት ነው?
የጽድቅ መንገዶች ጋር አስማምተህ ከሆነ መንፈሳዊ ገነት በሚል በትክክል ወደተጠሩት አስቀድሞም ተስፋ ወደተሰጠባቸው ሁኔታዎች ገብተህ መደሰት እንደጀመርህ አያጠራጥርም። ለሐዋርያው ዮሐንስ የሚከተለው መግለጫ ተሰጥቶታል:- “ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፣ ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሙም፣ ፀሐይም ትኩሳትም ከቶ አይወርድባቸውም። በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፣ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፣ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።” (10. (ሀ) በመንፈሳዊ መንገድ ሲታይ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ‘ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፣ አይጠሙም’ የሚለው ቃል እውነት የሆነው እንዴት ነው? (ለ) ይህ በራስህ ላይ ተፈጽሞ አይተኸዋልን?
10 በመልካሙ እረኛ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅራዊ ጥበቃ ሥር ከመሆንህ በፊት ጽድቅን ተርበህና ተጠምተህ ነበርን? (ከማቴዎስ 5:6 ጋር አወዳድር) ሁኔታህ እንደዚያ ከነበረ ምኞትህ ይሖዋ ብቻ በልጁ በኩል ሊፈጽመው የሚችል ነገር ነበር። ስለ ይሖዋ የጽድቅ መንገዶች ይኸውም ክፉዎቹን ለማጥፋት ዓላማ እንዳለው ነገር ግን ይገባናል በማንለው ደግነት ተገፋፍቶ የአዳም ልጆች እንዲድኑ ዝግጅት ያደረገ መሆኑን በተማርህ ጊዜ በሕይወትህ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ደስታ ተሰምቶሃል። በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውና በድርጅቱ አማካኝነት የሚቀርበው መንፈሣዊ ምግብና ውኃ እርካታህ እንዲቀጥል አድርጓል። (ኢሳይያስ 65:13, 14) በክርስቶስ በኩል ራስህን ለአምላክ ወስነህ ከሆነ ደግሞ በሕይወትህ ውስጥ እውነተኛ ዓላማ አለህ ማለት ነው። (ከዮሐንስ 4:32–34 ጋር አወዳድር) በጉ “እጅግ ብዙ ሰዎችን” ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭ ስለሚመራቸው ገነት በምትሆነዋ ምድር ላይ አስደሳቹን ዘላለማዊ ሕይወት የማግኘቱ ዕድል ከፊትህ ተዘርግቶልሃል።
11. (ሀ) “ከእንግዲህ ወዲያ ፀሐይም ትኩሳትም” የማይወርድባቸው በምን መንገድ ነው? (ለ) ይህስ ለአንተ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
11 “እጅግ ብዙ ሰዎች” ምንም መስጋት እንደማያስፈልጋቸው የሚተማመኑ “በጎች” እንደመሆናቸው መጠን መልካሙ እረኛ ከክፉ ነገር ሁሉ እየጠበቀ በጥሩ ሁኔታ ይመራቸዋል። በምሳሌያዊ አነጋገር ሕዝቅኤል 38:22, 23፤ ከመዝሙር 11:6 እና 85:3, 4 ጋር አወዳድር።
“ፀሐይም ትኩሳትም አይወርድባቸውም” የተባለው በዚህ ምክንያት ነው። ይህ ሲባል ግን “እጅግ ብዙ ሰዎች” ከተባሉት አንዱ ስትሆን ከዓለም ስደት አይደርስብህም ማለት አይደለም። ከዚህ ይልቅ አባባሉ አምላክን ባለማስደሰት የቁጣ ትኩሳት ከሚያሳድሩበት አንዱ ከመሆን ትድናለህ ማለት ነው። በተጨማሪም በክፉዎች ላይ መለኮታዊ ቁጣ በሚዘንብበት ጊዜ አንተን አያጠፋህም። ይህ መልካም ዝምድና ለዘላለም ሊቀጥል ይችላል። —12. አሁንም እንኳን ቢሆን ከዓይኖችህ ዕንባ የጠፋው እንዴት ነው?
12 በእርግጥ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ከተባሉት መካከል የምትገኝ ከሆነ ለመደሰት የሚያበቁ ብዙ አስደናቂ ምክንያቶች አሉህ! ክፉዎች ፈጽሞ ሲደመሰሱ፣ የራስህም አእምሮና ሰውነት ከሁሉም የኃጢአት ውጤቶች ሲላቀቁ የማየት አስደናቂ ተስፋ አለህ። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ሰዎች አምላክን ባለማወቃቸው ጠንቅ የሚደርስባቸው ኀዘን አንተን አይነካም። ይሖዋ አምላኩ የሆነለት ሕዝብ ብቻ የሚመጣለትን ደስታ ማግኘት ጀምረሃል። (መዝሙር 144:15) በዚህ መንገድ “እግዚአብሔር እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል” የሚለው ተስፋ ከአሁን ጀምሮ እየተፈጸመልህ ነው።
13. የሺው ዓመት የክርስቶስ ግዛት ጀምሮ ወደፊት እየገፋ ሲሄድ የመንፈሳዊ ገነት ደስታ እንዲጨምር የሚያደርጉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
13 “እጅግ ብዙ ሰዎች” የአሁኑን የነገሮች ሥርዓት ፍጻሜ በሕይወት እንደሚሻገሩ ሁሉ መንፈሳዊ ገነትም እንደዚሁ ይሻገራል። ከእነርሱ አንዱ ከሆንህ የክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ጀምሮ ወደፊት እየገፋ ሲሄድ በሰቡ መንፈሣዊ ነገሮች ግብዣ መደሰትህን ትቀጥላለህ። የማይወድቀው የአምላክ ዓላማ ታላቅ ፍጻሜውን አግኝቶ ስታይ ስለ አምላክ ያለህ ዕውቀት ጥልቅ እየሆነ ይሄዳል። ከአንተ ጋር በእውነተኛ አምልኮ የሚተባበሩ ቁጥራቸው እያደገ የሚሄድ ሰዎች ከሞት ይነሳሉ። በዚያን ጊዜ እነርሱን ከሚቀበሉት መካከል ስትሆን ደስታህ የላቀ ይሆናል። በዚያን ጊዜ የሚገኙት ሥጋዊ በረከቶች የይሖዋ ፍቅር መግለጫ ተደርገው ስለሚታዩ ለታማኞቹ የአምላክ አገልጋዮች ውድ ነገሮች ይሆኑላቸዋል። — ኢሳይያስ 25:6–9፤ ያዕቆብ 1:17
የክለሳ ውይይት
● መጽሐፍ ቅዱስ “እጅግ ብዙ ሰዎች” የተባሉትን ከየትኛው ልዩ ሁኔታ ጋር አያይዞ ይጠቅሳቸዋል? እንዴትስ?
● መለኮታዊ ሞገስን ካገኙት “እጅግ ብዙ ሰዎች” አንዱ ለመሆን ከፈለግን አሁን ምን ማድረግ አለብን?
● የመንፈሳዊ ገነትን በረከቶች ምን ያህል ከፍ አድርገህ ትመለከታቸዋለህ?
[የግርጌ ማስታወሻ]