አምላክ ክፋት እንዲቀጥል በመፍቀዱ ምን ተምረናል?
ምዕራፍ 7
አምላክ ክፋት እንዲቀጥል በመፍቀዱ ምን ተምረናል?
1. (ሀ) ይሖዋ ዓመጸኞቹን በዔደን ውስጥ ወዲያው ቢያጠፋቸው ኖሮ እርምጃው እኛን እንዴት ይነካን ነበር? (ለ) ይሖዋ እንደዚያ በማድረግ ፈንታ ምን ፍቅራዊ ዝግጅት አድርጎልናል?
በሕይወታችን ውስጥ ምንም ዓይነት ችግሮች ቢደርሱብን አምላክ እንድንወለድ መፍቀዱ ፍትሕ የጐደለው ነገር አይደለም። የመጀመሪያዎቹን ሰዎች ፍጹማን አድርጎ በመፍጠር መኖሪያቸውን ገነት አድርጐላቸው ነበር። በእርሱ ላይ እንዳመጹ ወዲያውኑ ቢያጠፋቸው ኖሮ አሁን ያለው የሰው ዘር ባልኖረም ነበር። ሕመም፣ ድህነትና የወንጀል ድርጊቶችም እንደዚሁ አይኖሩም ነበር። አዳምና ሔዋን የሚወልዷቸው ሁሉ አለፍጽምናን የሚወርሱ ቢሆኑም ከመሞታቸው በፊት ልጆች እንዲወልዱ ይሖዋ በምሕረቱ ፈቀደላቸው። ይሖዋ እምነት ያላቸው የሰው ዘሮች ሁሉ አዳም ያሳጣቸውን ነገር ይኸውም ከፍተኛ ደስታ የሚገኝበትን የዘላለም ሕይወት በክርስቶስ በኩል እንዲመጣላቸው ዝግጅት አደረገ። — ዘዳግም 32:4, 5፤ ዮሐንስ 10:10
2. ይህ ሁሉ የተደረገው ለእኛ መዳን ብቻ ታስቦ ነውን?
2 ይህ የይሖዋ ዝግጅት ለእያንዳንዳችን የሚያመጣልን ጥቅም መለኪያ የለውም። ይሁን እንጂ ነገሩ ከግል መዳናችን የበለጠ ክብደት የነበረውን ዓላማ እንደሚመለከት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመዘገቡት ሐሳቦች ይገልጹልናል።
ለታላቁ ስሙ ሲል
3. ይሖዋ ለምድርና ለሰው ልጆች የነበረው ዓላማ መፈጸሙ ምንን የሚነካ ነበር?
3 ይሖዋ ስለ ሰውና ስለ ምድር ያወጣው ዓላማ መፈጸሙ ስሙን ይኸውም በእርግጥ የአጽናፈ ዓለም ሉዓላዊ ገዥና እውነትን የሚናገር አምላክ መሆኑን የሚመለከት ነበር። ይሖዋ የመጨረሻውን ከፍተኛ ቦታ የያዘ እንደ መሆኑ በጽንፈ ዓለም የሚገኙ ሁሉ ሰላምና ደኅንነት ማግኘታቸው የተመካው ለስሙ የሚገባውን ሙሉ አክብሮት በማሳየታቸውና እርሱን በመታዘዛቸው ላይ ነው።
4. የይሖዋ ዓላማ ምን ነበር?
4 አምላክ አዳምንና ሔዋንን ከፈጠረ በኋላ መከናወን ያለበት አንድ ሥራ ሰጣቸው። ገነትን በማስፋፋት ምድርን ሁሉ በቁጥጥራቸው ሥር እንዲያደርጉ ብቻ ሳይሆን በዘሮቻቸው እንዲሞሉአትም ጭምር ዓላማው መሆኑን ግልጽ አደረገላቸው። (ዘፍጥረት 1:28) ታዲያ በእነርሱ ኃጢአት የተነሳ ይህ ዓላማ ሊከሽፍና የአምላክ ስም ሊሰደብ ይሆን?
5. (ሀ) በዘፍጥረት 2:17 መሠረት መልካሙንና ክፉውን ከሚያስታውቀው ዛፍ የሚበላ መቼ ይሞታል ተብሎ ነበር? (ለ) ይሖዋ ምድር በሰዎች እንድትሞላ የነበረውን ዓላማ ሳይለቅ ይህን ቃል የፈጸመው እንዴት ነው?
ዘፍጥረት 2:17) አምላክ ቃሉን በመጠበቅ አዳም ኃጢአት በሠራበት በዚያው ዕለት ሕግ ተላላፊዎቹን ለጥያቄ አቅርቦ የሞት ፍርድ በየነባቸው። ከቅጣቱ በምንም መንገድ ሊያመልጡ አይችሉም። ከፍርድ አንጻር ሲታይ አዳምና ሔዋን በአምላክ ፊት በዚያው ቀን ሞተዋል። (ከሉቃስ 20:37, 38 ጋር አወዳድር) ነገር ግን ይሖዋ ምድር በሰው እንድትሞላ የተናገረውን ዓላማ ለማስፈጸም ሲል ቃል በቃል ከመሞታቸው በፊት ልጆች ወልደው ቤተሰብ እንዲመሰርቱ ፈቀደላቸው። ያም ሆነ ይህ በአምላክ ዘንድ አንድ ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን ስለሆነ አዳም በ930 ዓመቱ በሞተ ጊዜ ዕድሜው ከአንድ “ቀን” አላለፈም። (ዘፍጥረት 5:3-5፤ ከመዝሙር 90:4ና ከ2 ጴጥሮስ 3:8 ጋር አወዳድር።) እንግዲያው ይሖዋ ቅጣቱ ስለሚፈጸምበት የጊዜ ገደብ የተናገረው ቃል እውነት ሆኖአል፤ ምድር በአዳም ዘሮች እንድትሞላ ያወጣውም ዓላማ አልከሸፈም። ሆኖም በዚህ ምክንያት ኃጢአተኛ ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ እንዲኖሩ ተፈቀደላቸው ማለት ነው።
5 አዳም ባለመታዘዝ መልካምንና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ ቢበላ ‘በዚያው ቀን’ እንደሚሞት ይሖዋ አስጠንቅቆት ነበር። (6, 7. (ሀ) ይሖዋ ክፉዎች ለተወሰነ ጊዜ እንዲኖሩ የሚፈቅድበት ምክንያት ምን መሆኑን ዘጸአት 9:15, 16 የሚጠቁምልን እንዴት ነው? (ለ) ከፈርዖን ጋር በተያያዘ የይሖዋ ኃይል የታየውና ስሙ የታወቀው እንዴት ነው? (ሐ) እንግዲያው የአሁኑ ክፉ ሥርዓት ሲደመደም ውጤቱ ምን ይሆናል?
6 ይሖዋ በሙሴ ዘመን ለግብጹ መሪ የተናገረው ቃልም ክፉዎች ለተወሰነ ጊዜ እንዲኖሩ አምላክ ለምን እንደፈቀደ የሚያመለክት ተጨማሪ ሐሳብ ይሰጠናል። እስራኤላውያን ግብጽን ለቀው እንዳይሄዱ ፈርዖን በከለከለ ጊዜ አምላክ ወዲያውኑ አላጠፋውም። ይሖዋ አገሪቱን በአሥር መቅሰፍቶች በመምታት ኃይሉን በሚያስደንቅና በተለያዩ መንገዶች አሳየ። ሰባተኛውን መቅሰፍት እንደሚያመጣ ሲያስጠነቅቅ እርሱንና ሕዝቡን ከምድር ገጽ በቀላሉ ሊደመስሳቸው ይችል እንደነበር ለፈርዖን ነገረው። ቢሆንም ይሖዋ እንዲህ አለው:- “ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ፤ ስሜ በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ [ስል እስከ አሁን አኑሬሃለሁ።]” — ዘጸአት 9:15, 16
7 ይሖዋ እሥራኤልን ከግብጽ ባዳነ ጊዜ በእርግጥም ስሙ በሰፊው ታውቋል። ዛሬ ከ3,500 ዓመታት በኋላም ቢሆን ይሖዋ ያደረገው ነገር አልተረሳም። ይሖዋ የሚለው የግል ስሙ ብቻ ሳይሆን ስለዚህ ስም ባለቤት የሚገልጸው እውነት ጭምር ታውቋል። ይህም ይሖዋ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ለአገልጋዮቹ ሲል እርምጃ የሚወስድ አምላክ ነው የሚል ስም አትርፎለታል። ሁሉን ማድረግ የሚያስችል ኃይል ስላለው ዓላማውን ምንም ነገር ሊበግረው እንደማይችል የሚያሳይ እርምጃ ነው። የሚታየውንና የማይታየውን ክፉ ሥርዓት ለመደምሰስ በቅርቡ ይሖዋ የሚወስደው እርምጃ ከዚያ ይበልጥ አስደናቂ ይሆናል። በዚያን ቀን የሚያሳየው ሁሉን ማድረግ የሚያስችለው ኃይሉና የሚወስደው እርምጃ ለይሖዋ ስም የሚያመጣለት ክብር በአጽናፈ ዓለም ታሪክ ውስጥ የማይረሳ ሆኖ ይኖራል። የሚያስከትላቸው ጥቅሞችም ፍጻሜ አይኖራቸውም። — ሕዝቅኤል 38:23፤ ራእይ 19:1, 2
‘የአምላክ ጥበብ እንዴት ጥልቅ ነው!’
8. ጳውሎስ ምን ተጨማሪ ነገሮችን እንድናስታውስ ያሳስበናል?
8 ሐዋርያው ጳውሎስ ለሮማውያን በጻፈው ደብዳቤ ላይ “በእግዚአብሔር ዘንድ ዓመፃ አለ ወይ?” የሚል ጥያቄ አንስቷል። ከዚያም የአምላክን ምሕረት አጥብቆ በመግለጽና ይሖዋ ለፈርዖን የተናገረውን በመጥቀስ መልስ ሰጠ። በተጨማሪም እኛ ሰዎች በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ የሸክላ ዕቃ መሆናችንን የሚያስታውስ ሐሳብ ጠቀሰ። ሠራተኛው ሸክላውን ለፈለገው ዓላማ ቢጠቀምበት ያጉረመርማልን? ጳውሎስ የሚከተለውን ሐሳብ ጨምሯል:- “ነገር ግን እግዚአብሔር ቁጣውን ሊያሳይ ኃይሉንም ሊገልጥ ወዶ [ሳለ] አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው በምሕረት ዕቃዎች ላይ የክብሩን ባለጠግነት ይገልጥ ዘንድ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎች በብዙ ትዕግስት ከቻለ እንዴት ነው? የምህረቱ ዕቃዎችም ከአይሁድ ብቻ አይደሉም፤ ነገር ግን ከአሕዛብ ደግሞ የጠራን እኛ ነን።” —9. (ሀ) “ለጥፋት የተዘጋጁት የቁጣ ዕቃዎች” እነማን ናቸው? (ለ) ይሖዋ ያን ያህል በጠላትነት እያዩት በጣም የታገሰው ለምንድን ነው? የመጨረሻውስ ውጤት ለሚያፈቅሩት ሁሉ መልካም የሚሆንላቸው እንዴት ነው?
9 ይሖዋ በዘፍጥረት 3:15 ላይ የተመዘገበውን ትንቢታዊ ቃል ከተናገረበት ጊዜ አንስቶ ሰይጣንና ዘሮቹ “ለጥፋት የተዘጋጁ የቁጣ ዕቃዎች” ሆነዋል። በዚያ ጊዜ ሁሉ ይሖዋ ትዕግስቱን አሳይቷል። ክፉዎች በይሖዋ መንገዶች ቀልደዋል፤ አገልጋዮቹን አሳደዋል፤ ልጁንም እስከ መግደል ደርሰዋል። ይሖዋ ግን ራሱን በጣም ገታ። ይህም ለአገልጋዮቹ ዘላቂ ጥቅም አምጥቶላቸዋል። በአምላክ ላይ ማመጽ የሚያመጣውን አስከፊ ውጤት ፍጥረታት በሙሉ ለማየት አጋጣሚ አግኝተዋል። በዚህም ላይ የኢየሱስ ሞት ታዛዥ የሰው ልጆችን ለማዳንና ‘የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ’ የሚያስችል መሠረት አስገኝቷል። — 1 ዮሐንስ 3:8፤ ዕብራውያን 2:14, 15
10. ባለፉት 1,900 ዓመታት ይሖዋ ለክፉዎች ጊዜ መስጠቱን የቀጠለው ለምንድን ነው?
10 ኢየሱስ ሞቶ ከተነሳ ከ1,900 ዓመታት በላይ አልፈዋል። በዚህ ሁሉ ጊዜ ይሖዋ “የቁጣን ዕቃዎች” ባለማጥፋት ተጨማሪ ትዕግስት አድርጓል። ለምን ይሆን? ምክንያቱም በሁለተኛ ደረጃ የሴቲቱ ዘር ተብለው የሚጠሩትን ይኸውም በሰማያዊ መንግሥት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚወርሱትን ሲያዘጋጅ ስለነበረ ነው። (ገላትያ 3:29) ሐዋርያው ጳውሎስ “የምሕረት ዕቃዎች” ብሎ የጠራው እነዚህን ቁጥራቸው 144,000 የሆነውን ሰዎች ነው። በመጀመሪያ አይሁዳውያን ግለሰቦች የዚህን ቡድን አባላት እንዲሞሉ ጥሪ ቀረበላቸው። በኋላ የተገረዙ ሣምራውያን በመጨረሻም አሕዛብ ወደ ቡድኑ አባልነት ተጨመሩ። ይሖዋ ማንንም እንዲያገለግለው ሳያስገድድ ነገር ግን ፍቅራዊ ዝግጅቶቹን በአድናቆት ለሚቀበሉት ታላቅ በረከቶች በመስጠት በብዙ ትዕግስት ዓላማውን አከናውኗል። ያንን ሰማያዊ ቡድን የማዘጋጀቱ ሥራ አሁን ተገባዷል።
11. በአሁኑ ጊዜ ከይሖዋ ትዕግስት እየተጠቀሙ ያሉት ሌሎች ሰዎች እነማን ናቸው?
11 ይሁን እንጂ የምድር ነዋሪዎች ሁኔታስ እንዴት ነው? አምላክ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ በቢልዮን የሚቆጠሩ ሙታን ተነስተው የአምላክ መንግሥት ምድራዊ ተገዥዎች ይሆናሉ። ከዚህም በተጨማሪ በተለይ ከ1935 ወዲህ ይሖዋ ከሁሉም ብሔራት “እጅግ ብዙ ሰዎች” ለመዳን እንዲሰበሰቡ አድርጓል። — ራእይ 7:9, 10፤ ዮሐንስ 10:16
12. (ሀ) በዚህ ምክንያት ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝተናል? (ለ) ይሖዋ እነዚህን ነገሮች እንዴት አድርጐ እንደያዘ ስትመለከት እንዴት ይሰማሃል?
12 ታዲያ ይህ ሁሉ አድራጎት ፍትሕ የጐደለው ነውን? በፍጹም አይደለም! ይሖዋ ከዓላማው ጋር በሚስማማ መንገድ ለአንዳንዶች ርኅራኄውን ለማሳየት ብሎ “የቁጣ ዕቃዎችን” ማለትም የክፉዎችን መጥፋት እስከ ዛሬ ስላቆየው ማንም ሰው በእርሱ ላይ ቢያማርር እንዴት ትክክለኛ ሊሆን ይችላል? እንዲያውም የዓላማው ምስጢር እየተገለጠ በሄደ መጠን ስለ ራሱ ስለ ይሖዋ ብዙ ትምህርት ለማግኘት ችለናል። በዚሁ ሳቢያ ሊገለጡ የቻሉትን ጠባዮች ይኸውም ፍትሑን፣ ምሕረቱን፣ ትዕግስቱንና የጥበቡን ብዛት የበለጠ ለመረዳት ችለናል። ይሖዋ በእርሱ ላይ ለተነሳው ጥያቄ መልስ የሰጠበት የጥበብ መንገድ አገዛዙ ከሁሉ የተሻለ ለመሆኑ ለዘላለም ምሥክር ሆኖ ይኖራል። ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር በመስማማት “የእግዚአብሔር ባለጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው! ለመንገዱ ፍለጋ የለውም!” እንላለን። —ለአምላክ ያደርን መሆናችንን የምናሳይበት አጋጣሚ
13. (ሀ) በራሳችን ላይ መከራ ቢደርስ ምን አጋጣሚ ይኖረናል? (ለ) ጥበብ ባለበት መንገድ ምላሽ ለመስጠት ምን ሊረዳን ይችላል?
13 አምላክ እስከ አሁን ድረስ ክፉዎችን ስላላጠፋቸውና እንደሚመጣ አስቀድሞ የተነገረለትን የሰው ዘር የተሐድሶ ዘመን ገና ስላላመጣው በግላችን ላይ መከራ የሚያስከትሉብን ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ። እንደዚህ ያለ ሁኔታ ሲደርስብን ምን እናደርጋለን? እነዚህ ሁኔታዎች የይሖዋን ስም ከስድብ ለማንጻትና ዲያብሎስን ውሸታም ለማድረግ የሚያስችሉ አጋጣሚዎች ይዘዋል። እነዚህ አጋጣሚዎች ይታዩናልን? “ልጄ ሆይ፣ ጠቢብ ሁን፣ ልቤንም ደስ አሰኘው፣ ለሚሰድበኝ መልስ መስጠት ይቻለኝ ዘንድ” የሚለውን ምክር ማስታወሳችን እንደዚያ ለማድረግ የበለጠ ኃይል ይሰጠናል። (ምሳሌ 27:11) ይሖዋን የሚሰድበው ሰይጣን ሰዎች ሀብታቸው ቢወድምባቸው ወይም ሥጋዊ ስቃይ ቢደርስባቸው በአምላክ ላይ ያማርራሉ፣ እንዲያውም ይሰድቡታል ባይ ነው። (ኢዮብ 1:9-11፤ 2:4, 5) በመከራ ጊዜ ለአምላክ ታማኝ ሆነን በመቆም የሰይጣን አባባል ትክክል እንዳልሆነ ብናሳይ የይሖዋን ልብ እናስደስታለን። ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ርኅራኄ አዘል ፍቅር እንዳለውና ታማኝነታችንን ካረጋገጥን ለኢዮብ ዋጋውን እንደሰጠው ሁሉ እኛንም በጊዜው አትረፍርፎ እንደሚክሰን ሙሉ በሙሉ ለመተማመን እንችላለን። — ያዕቆብ 5:11፤ ኢዮብ 42:10-16
14. ፈተና ሲደርስብን በይሖዋ ላይ እምነት ጥለን ብንታገስ ምን ሌሎች ጥቅሞች ይመጡልናል?
ዕብራውያን 5:8, 9፤ 12:11፤ ያዕቆብ 1:2-4
14 አስጨናቂ ፈተናዎች ሲደርሱብን በይሖዋ ላይ እምነት ጥለን ብንታገስ ዋጋ የማይተመንላቸው ጠባዮች ለማፍራት እንችላለን። ኢየሱስ ከደረሱበት መከራዎች ድሮ ባላወቀው መንገድ “መታዘዝን ተማረ።” እኛም ትዕግስትና ጽናት መኰትኰትን፤ እንዲሁም የይሖዋን የጽድቅ መንገዶች በጥልቅ ማድነቅን ልንማር እንችላለን። ታዲያ ይህን ማሰልጠኛ በትዕግስት እንቀበላለንን? —15. መከራን በትዕግስት በምንቋቋምበት ጊዜ ሌሎች እንዴት ሊጠቀሙ ይችላሉ?
15 ምን እንደምናደርግ ሌሎች ይመለከታሉ። ለጽድቅ ባለን ፍቅር ምክንያት የሚደርስብንን መከራ ሁሉ የሚያዩ አንዳንድ ሰዎች እውነተኞቹ የክርስቶስ “ወንድሞች” እነማን እንደሆኑ ለመረዳት ይችላሉ። ከወንድሞቹ ጋር በአምልኮ አንድ በመሆንም የዘላለም ሕይወትን በረከቶች ለመውረስ ከተዘጋጁት መካከል ሊሰለፉ ይችላሉ። (ማቴዎስ 25:34-36, 40, 46) ይሖዋና ልጁ ሰዎች ይህንን አጋጣሚ እንዲያገኙ ይፈልጋሉ። እኛስ እንፈልጋለንን? ሰዎቹ ይህንን አጋጣሚ እንዲያገኙ ስንል መከራ ለመቀበል ፈቃደኞች ነንን?
16. ለዚህ ዓይነቱ መከራ ያለን አመለካከት ከአንድነት ጋር የተያያዘው እንዴት ነው?
16 እንግዲያው በሕይወታችን የሚደርሱብን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ለይሖዋ ያደርን መሆናችንን ለማሳየትና ፈቃዱን ለመፈጸም እንደሚያስችሉ አጋጣሚዎች አድርገን ብንመለከት እንዴት ጥሩ ነው! እንደዚህ ማድረጋችን ከአምላክና ከክርስቶስ ጋር አንድ ለመሆን ወደፊት እየተጓዝን ነው ማለት ነው። ኢየሱስ እውነተኛ ክርስቲያኖች በሙሉ ወደዚህ አንድነት እንዲደርሱ ጸልዩአል። — ዮሐንስ 17:20, 21
የክለሳ ውይይት
● ይሖዋ ክፋት እንዲቀጥል ቢፈቅድም ለራሱ ስም ተገቢውን ክብር ያሳየው እንዴት ነው?
● አምላክ “ለቁጣ ዕቃዎች” ጊዜ መስጠቱ ምሕረቱ ወደ እኛ እንዲደርስ ያስቻለው እንዴት ነው?
● በራሳችን ላይ የሚደርሱትን መከራዎች ምን ለማደረግ ጥሩ አጋጣሚ እንደሆኑ አድርገን ለማየት መሞከር አለብን?
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]