የአምላክን ቃል ጠበቅ አድርገህ ያዝ
ምዕራፍ 3
የአምላክን ቃል ጠበቅ አድርገህ ያዝ
1. (ሀ) የጥንቶቹ እስራኤላውያን የአምላክን ቃል እውነተኛነት ያዩት እንዴት ነው? (ለ) ስለዚህስ ጉዳይ መነጋገር ለምን አስፈለገ?
“እናንተም [ይሖዋ (አዓት)] ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ እወቁ፤ ሁሉ ደርሶላችኋል።” ይህ ቃል እስራኤላውያን በተስፋይቱ ምድር ከተቀመጡ በኋላ ኢያሱ ለእስራኤል ሽማግሌዎች የተናገራቸው ማሳሰቢያ ነው። ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላ በነበሩት ዓመታት የአምላክን ቃል ሁልጊዜ ከልብ አጥብቀው አልያዙትም፤ አልሠሩበትምም። ውጤቱስ ምን ሆነ? ይሖዋ እባርካችኋለሁ ኢያሱ 23:14–16) ይህ የታሪክ መዝገብና የቀረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሁሉ እስከ ዘመናችን ተጠብቆ የቆየው ለትምህርታችን ነው። ተስፋ እንዲኖረንና ያንን ተስፋ የሚያሳጣ ምንም ነገር እንዳናደርግ እኛን ለማስተማር ይሖዋ እስከ ዛሬ ድረስ አቆይቶታል። — ሮሜ 15:4
በማለት የሰጣቸው ተስፋዎች በትክክል እንደተፈጸሙ ሁሉ ካልታዘዛችሁ አመጣባችኋለሁ ብሎ ያስጠነቃቀቸውንም ነገሮች እንዳመጣባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። (2. (ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ ‘በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈው’ እንዴት ነው? (ለ) ይህንን ማወቃችን ምን ኃላፊነት ያመጣብናል?
2 ይሖዋ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጻፍ 40 በሚያክሉ ሰብዓዊ “ጸሐፊዎች” ቢጠቀምም የመጽሐፉ ባለቤት ወይም አዘጋጅ ራሱ ነው። ታዲያ እንደዚህ ሲባል ይሖዋ ሰዎችን እየመራና እየተከታተለ በውስጡ ያለውን ሁሉ አስጽፎታል ማለት ነውን? አዎን፤ ሐዋርያው ጳውሎስ በትክክል እንደተናገረው “ቅዱስ ጽሑፍ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነትና መሪነት ተጽፎአል።” ይህንን ያለ ምንም ጥርጥር ስለምናምንበት ራሳችን የመጽሐፉን ምክር ለመከተልና ሕይወታችንን በውስጡ ባሉት ሐሳቦች ለመምራት ጥረት እንደምናደርግ ሁሉ በየትም ሥፍራ የሚገኙ ሰዎች እንደዚሁ እንዲያደርጉ እናበረታታቸዋለን። — 2 ጢሞቴዎስ 3:16 አዓት ፣ 1 ተሰሎንቄ 2:13
ሌሎች ሰዎች መጽሐፉን እንዲወዱት ምን ሊረዳቸው ይችላል?
3. መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል መሆኑን ለማመን ያዳገታቸውን ብዙ ሰዎች የምንረዳበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ምንድን ነው?
3 የምናነጋግራቸው ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ብለው እንደ እኛ አያምኑም። ታዲያ እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን? ብዙውን ጊዜ ከሁሉ የተሻለው መንገድ መጽሐፍ ቅዱስን ገልጦ በውስጡ ያለውን ሐሳብ ማሳየት ነው። “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፣ የሚሠራም፣ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው . . . የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል።” (ዕብራውያን 4:12) “የእግዚአብሔር ቃል” የተባለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመዘገበው የተስፋ ቃሉ ነው። እርሱም ሕያው ነው እንጂ የሞተ ታሪክ አይደለም። አንድም የሚበግረው ኃይል ሳይኖር ወደ ፍጻሜው እየገሰገሰ ነው። በዚህ ጊዜ ቃሉን ለመስማት አጋጣሚ ያገኘ ሁሉ ብቃቶቹን ለማሟላት ፈቃደኛ መሆኑንና አለመሆኑን በተመለከተ እውነተኛው የልብ ፍላጎቱ ይገለጣል። ቃሉ እኛ በግል ከምንሰጠው ከማንኛውም ሐሳብ የበለጠ ሰውን የመለወጥ ኃይል አለው።
4. አንዳንድ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ የነበራቸውን ዝንባሌ የለወጠው ስለ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች የተሰጠው ቀላል ማብራሪያ ነው? እርሱስ ለምን ለወጣቸው?
4 ብዙ ሰዎች የአምላክን ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማየታቸው ብቻ ሕይወታቸው ተለውጧል። ሌሎች ደግሞ መጽሐፉ ስለ መኖር ዓላማ፣ ክፉ ነገሮች እንዲኖሩ አምላክ ለምን እንደፈቀደ፣ የአሁኑ ጊዜ ሁኔታዎች ምን ትርጉም እንዳላቸው ወይም በአምላክ መንግሥት ላይ የተመሠረተውን እውን ተስፋ ስለገለጽንላቸው ብቻ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ወስነዋል። አጉል ሃይማኖታዊ ልማዶች ሰዎችን በክፉ መናፍስት እንዲጠቁ ባደረጉባቸው አገሮች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ይህ ነገር እንዴት እንደሚመጣና ከዚህ እንዴት መላቀቅ እንደሚቻል የሚሰጠው ሐሳብ ሲብራራላቸው ለማጥናት ፍላጎት አድሮባቸዋል። እነዚህ ነጥቦች ይህን ያህል የነኳቸው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ስለ እነዚህ ትልልቅ ጉዳዮች አስተማማኝ መመሪያ የሚሰጠው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ስለሆነ ነው። — መዝሙር 119:130
5. አንድ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ አላምንም ቢል ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል? እንዴትስ ልንረዳው እንችል ይሆናል?
5 ሆኖም አንድ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ እንደማያምን በቀጥታ ቢነግረንስ? ውይይታችን በዚሁ መቆም አለበትን? ሰውየው ምክንያታችንን ለመስማትና ለመወያየት ፈቃደኛ እስከሆነ ድረስ ማቆም የለብንም። የአምላክን ቃል በመደገፍ እውነተኛነቱን እንደምናምንበት ሆነን የመናገር ኃላፊነት እንዳለብን ሊሰማን ይገባል። ምናልባት ሰውየው መጽሐፍ ቅዱስን የሕዝበ ክርስትና መጽሐፍ አድርጎ ይመለከተው ይሆናል። ሕዝበ ክርስትና ያስመዘገበችው የግብዝነት ታሪክና በፖለቲካ ውስጥ መግባቷ እንዲሁም ሁልጊዜ ሰውን እየወተወተች ገንዘብ የምትሰበስብ መሆኗ ሰውየው መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጠላ ከማቴዎስ 15:7–9፤ ከያዕቆብ 4:4፤ ከሚክያስ 3:11, 12 ጋር አወዳድር።
አድርጎት ይሆናል። ለምን ሰውየውን ጠይቀህ ችግሩ ይህ መሆኑን አታረጋግጥም? መጽሐፍ ቅዱስ የሕዝበ ክርስትናን ዓለማዊ መንገድ ማውገዙና በእርስዋና በእውነተኛው የክርስትና ሃይማኖት መካከል ያለውን ልዩነት ማስረዳቱ ፍላጎቱን ሊቀሰቅስ ይችል ይሆናል። —6. (ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል መሆኑን አንተን የሚያሳምንህ ምንድን ነው? (ለ) ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ መሆኑን እንዲቀበሉ ለመርዳት ከየትኞቹ ሌሎች አቅጣጫዎች ማስረዳት ይቻላል?
6 ሌሎችን የሚረዳው ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነትና መሪነት የተጻፈ ስለመሆኑ በቀጥታ ማወያየቱ ነው። አንተ ራስህ መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ ለመሆኑ ግልጽ ማስረጃ ሆኖ የሚታይህ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ከማን እንደመጣ የሚናገራቸው ቃላት ናቸውን? (2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17፤ ራእይ 1:1) ወይስ መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት የሚሆነውን የሚናገሩ ብዙ ትንቢቶች የያዘ በመሆኑና እነዚህ ትንቢቶች ከሰው በላይ ከሆነ ምንጭ የተገኙ መሆን አለባቸው ብለህ ስለምታስብ ነውን? (2 ጴጥሮስ 1:20, 21፤ ኢሳይያስ 42:9) የሚያሳምንህ መጽሐፉ 1, 610 ዓመታት በፈጀ ረጅም ዘመን ውስጥ በብዙ ሰዎች የተጻፈ ቢሆንም በውስጡ ያሉት ሐሳቦች እርስ በእርሳቸው የሚስማሙ መሆናቸው ነውን? ወይስ በዚያ ዘመን ከተጻፉት ጽሑፎች ጋር ሲነጻጸር እርሱ ብቻ ከሳይንስ ጋር የማይጋጩ ሐሳቦችን የያዘ መሆኑ ነውን? ወይስ ጸሐፊዎቹ ጉድለታቸውን ሳይደብቁ በግልጽ መናገራቸው ነውን? ወይስ መጽሐፉን ለማጥፋት ክፉ ሙከራዎች ቢደረጉም እስከ ዛሬ ድረስ ተጠብቆ መቆየቱ ነውን? በጣም የሚነካህ የትኛውም ነጥብ ይሁን ሌሎችን ለመርዳት ልትጠቀምበት ትችላለህ።
የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን
7, 8. (ሀ) መጽሐፍ ቅዱስን በሚመለከት በግላችን ምን እያደረግን መሆን አለብን? (ለ) ከግል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በተጨማሪ ምን ማድረግ ያስፈልገናል? መጽሐፍ ቅዱስስ ይህንን የሚያሳየው እንዴት ነው? (ሐ) አንተ ራስህ የይሖዋ ዓላማዎች ሊገቡህ የቻሉት እንዴት ነው?
7 በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲያምኑ ሌሎችን መርዳት አስፈላጊ ሲሆን እኛም ራሳችን ጊዜ መድበን ዘወትር እንድናነበው ያስፈልጋል። ታዲያ እንደዚህ እያደረግህ ነውን? እስከ ዛሬ ድረስ ከተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ የሚበልጠው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህም ሲባል ግን መጽሐፍ ቅዱስን ካነበብን ሌላ ምንም ነገር አያስፈልገንም ማለት አይደለም። የማንንም እርዳታ ሳንፈልግ ራሳችን ልዩ ልዩ ጽሑፎችን በመመርመር ሁሉም ነገር ሊገባን ይችላል ብለን በማሰብ ራሳችንን እንዳናገል መጽሐፍ ቅዱስ ያስጠነቅቀናል። ምሳሌ 18:1፤ ዕብራውያን 10:24, 25
ሚዛናዊ ክርስቲያን ለመሆን የግል ጥናት ማድረግና ዘወትር በስብሰባ መገኘት ያስፈልጋል። —8 አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሥልጣን የኢሳይያስን ትንቢት በሚያነብበት ጊዜ አንድ መልአክ ፊልጶስ የተባለውን ወንጌላዊ ክርስቲያን እንደላከለት የሚገልጽ እኛን የሚጠቅም አንድ ታሪክ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ፊልጶስ ሰውየውን “በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” ብሎ ጠየቀው። ኢትዮጵያዊው ጃንደረባም “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” ብሎ በትህትና መለሰለት። ከዚያም ምንባቡን እንዲያብራራለት አጥብቆ ጠየቀው። ፊልጶስ መጽሐፍ ቅዱስን ለብቻው ሆኖ የሚያጠናና ስለ ቅዱሳን ጽሑፎች የግል ሐሳቡን የሚሰጥ ሰው አልነበረም። ከዚህ ይልቅ በኢየሩሳሌም ጉባኤ ከነበሩት ሐዋርያት ጋር የቅርብ ግንኙነት እንደነበረውና የይሖዋ ምድራዊ ድርጅት አባል እንደነበረ የታሪክ መዝገቡ ያሳያል። ስለዚህ ይሖዋ በዚያ ድርጅት አማካይነት ከሚሰጠው ትምህርት ኢትዮጵያዊውም እንዲጠቀም ፊልጶስ ሊረዳው ችሏል። (ሥራ 6:5, 6፤ 8:5, 14, 15, 26–35) ዛሬስ ቢሆን ከመሐላችን የማንንም እርዳታ ሳያገኝ በራሱ ጥረት የይሖዋን ዓላማ በግልጽና በትክክል የተረዳ ማን አለ? ከዚህ ይልቅ ሁላችንም ይሖዋ በሚታየው ድርጅቱ አማካይነት በፍቅር የሚሰጠው ትምህርት አስፈልጎን ነበር፤ ዛሬም ያስፈልገናል።
9. እንዴት ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራሞች ሁላችንንም ሊጠቅሙ ይችላሉ?
9 የይሖዋ ድርጅት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲገባንና እንድንጠቀምበት የሚረዳ እጅግ ግሩም የሆነ ቅዱስ ጽሑፋዊ ትምህርት በመጠበቂያ ግንብና በመሳሰሉት ጽሑፎች ላይ ያወጣል። ከዚህም በተጨማሪ በይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች ከሚካሄደው ቲኦክራቲካዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ጋር በማያያዝ ሣምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ይወጣል። አንዳንድ የይሖዋ ምሥክሮች ከዚህ በተጨማሪ መዝሙር 1:1–3፤ 19:7, 8) በግልህ ጠቅላላውን መጽሐፍ ቅዱስ አንብበኸዋልን? ካላነበብህ ከዳር እስከ ዳር ለማንበብ ልዩ ጥረት አድርግ። እያንዳንዱ ነገር ሙሉ በሙሉ ባይገባህም ስለ መጽሐፉ አጠቃላይ ሐሳብ ማግኘትህ ትልቅ ጥቅም ይሰጥሃል። የአማርኛውን መጽሐፍ ቅዱስ በቀን 3 ገጽ ብታነብ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ትጨርሰዋለህ።
የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም አላቸው። ቅዱሳን ጽሑፎችን በመመርመር የምናሳልፈው ጊዜ ትልቅ ጥቅም ሊያመጣልን ይችላል። (10. (ሀ) መጽሐፍ ቅዱስን የምታነበው መቼ መቼ ነው? (ለ) በዚህ ረገድ አዘውታሪነት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
10 ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ መቼ መቼ ለማድረግ ትችላለህ? ሌላው ቀርቶ በቀን 10 ወይም 15 ደቂቃ ብቻ እንኳን ለዚህ ብትመድብ እንዴት ትጠቀም ነበር! እንደዚህ ማድረግ ካልቻልክ በሣምንቱ ውስጥ ዘወትር በተወሰኑ ቀኖች ለማንበብ ቆርጠህ ፕሮግራሙን አጥብቀህ ተከታተል። በሕይወት ዘመናችን ሙሉ ምግብ እንደምንበላ ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብም የዕድሜ ልክ ልማዳችን መሆን አለበት። እንደምታውቀው ሁሉ አንድ ሰው በቂና ጥሩ ምግብ ካልተመገበ ጤንነቱ ይቃወሳል። መንፈሳዊነታችንም እንደዚሁ ነው። ሕይወታችን ‘ከይሖዋ አፍ የሚወጣውን ቃል’ ዘወትር በመመገባችን ላይ የተመካ ነው። — ማቴዎስ 4:4
11. መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ዓላማችን ምን መሆን አለበት?
11 መጽሐፍ ቅዱስን የምናነብበት ዓላማ ምን መሆን አለበት? ግባችን የተወሰኑ ገጾችን ለመሸፈን ወይም የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ብቻ ከሆነ ስህተት ነው። ዘላቂ ጥቅም ለማግኘት ከዚያ የተሻለ ዓላማ ሊኖረን ያስፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ የሚገፋፋን ለአምላክ ያለን ፍቅር፣ እርሱን የበለጠ ለማወቅ ያለን ፍላጎት፣ ፈቃዱን ለመረዳትና ተቀባይነት ባለው መንገድ እርሱን ለማምለክ ያለን ምኞት መሆን ይኖርበታል። (ዮሐንስ 5:39–42) አቋማችን “አቤቱ መንገድህን አመልክተኝ፣ ፍለጋህንም አስተምረኝ” ብሎ እንደ ጸለየው እንደ አንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ አቋም መሆን አለበት። — መዝሙር 25:4
12. (ሀ) “ትክክለኛ ዕውቀት” ማግኘት ለምን አስፈላጊ ነው? ለዚህስ በምናነብበት ጊዜ ምን ጥረት ማድረግ ሊያስፈልገን ይችላል? (ለ) በገጽ 27 ላይ በተገለፀው መሠረት መጽሐፍ ቅዱስን ከየትኞቹ አምስት አቅጣጫዎች ብናነበው እንጠቀማለን? (ሐ) በመጽሐፍ ቅዱስ እየተጠቀምህ በአንቀጹ መጨረሻ ያሉትን ጥያቄዎች በመመለስ እነዚህን አምስት ነጥቦች አንድ በአንድ በምሳሌ አስረዳ።
ቆላስይስ 3:10 ፤ 2 ጢሞቴዎስ 2:15) ትክክለኛ ዕውቀት ለማግኘት በጥንቃቄ ማንበብ ያስፈልገናል። ሐሳቡ ጥልቅ ከሆነም ትርጉሙ በደንብ እንዲገባን ደጋግመን ማንበብ ሊያስፈልገን ይችላል። ጊዜ ወስደን ትምህርቱን ብናሰላስልበት ወይም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ብንመለከተው እንጠቀማለን። ጥቅሶችን ከአምስት የተለያዩ አቅጣጫዎች እንዴት መመልከት እንደሚቻል በዚህ መጽሐፍ በገጽ 27 ላይ ተገልጿል። የቅዱሳን ጽሑፎች ብዙ ክፍሎች ከእነዚህ አቅጣጫዎች በአንዱ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ መንገዶች ጥቅም በሚሰጥ መንገድ ሊመረመሩ ይችላሉ። በሚቀጥሉት ገጾች ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ስትመልስ ይህ እንዴት እውነት እንደሆነ ትመለከታለህ።
12 ይሖዋ ይህን ትምህርት ሲሰጠን እኛም ትክክለኛ ዕውቀት ለማግኘት ፍላጎት ሊኖረን ይገባል። ትክክለኛ ዕውቀት ከሌለን የአምላክን ቃል በሕይወታችን በሚገባ ልንሠራበትና ለሌሎችም በትክክል ለማስረዳት እንዴት እንችላለን? ((1 ) ብዙዎቹ የምታነባቸው ጥቅሶች ይሖዋ ምን ዓይነት አምላክ እንደሆነ የሚያመለክቱ ሐሳቦች አሏቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ይሖዋ የፍጥረት ሥራዎች የሚናገረውን በአድናቆት ስናሰላስልበት ለእርሱ ያለን ዝንባሌ በዚህ እንዴት ይነካል? (መዝሙር 139:13, 14፤ ኢዮብ ምዕራፍ 38–42፤ በተለይም 38:1, 2 እና 40:2, 8 ከዚያም 42:1–6 ልብ ብለህ ተመልከት)
ኢየሱስ በዮሐንስ 14:9, 10 በተናገረው መሠረት በሉቃስ 5:12, 13 ከተገለጸውና ከመሳሰሉት ሁኔታዎች ስለ ይሖዋ ምን ብለን ለመደምደም እንችላለን?
(2 ) የምታነበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተስፋ በተደረገበት ዘር በኢየሱስ ክርስቶስ የሚመራው መንግሥት የይሖዋን ስም ከስድብ ሁሉ ነፃ አድርጎ እንዴት እንደሚያስከብረው ለሚገልጸው ለአጠቃላዩ የመጽሐፍ ቅዱስ መልዕክት ምን አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ተመራመር።
ግብጽን የመቱት መቅሰፍቶች ከዚህ አጠቃላይ መልዕክት ጋር የተያያዙት እንዴት ነው? (ዘፀአት 5:2፤ 9:16፤ 12:12 ተመልከት)
ልብን ሞቅ ባለ ስሜት የሚሞላው የሞዓባዊቷ የሩት ታሪክስ? (ሩት 4:13–17፤ ማቴዎስ 1:1, 5)
ገብርኤል ስለ ኢየሱስ መወለድ ለማርያም ያበሰራት ዜናስ እዚህ ላይ የሚገባው እንዴት ነው? (ሉቃስ 1:26–33)
የኢየሱስ ደቀመዛሙርት በጴንጠቆስጤ ዕለት በመንፈስ ቅዱስ መቀባታቸው ትልቅ ትርጉም የነበረው ለምንድን ነው? (ሥራ 2:1–4፤ 1 ጴጥሮስ 2:4, 5, 9፤ 2 ጴጥሮስ 1:10, 11)
(3 ) ከአንድ ጥቅስ በፊትና በኋላ ያሉት ሐሳቦች ትርጉሙን ይወስናሉ።
በሮሜ 5:1ና 8:16 ላይ ያሉት ቃላት የተነገሩት ለእነማን ነው? (ሮሜ 1:7ን ተመልከት)
በ1 ቆሮንቶስ 2:9 ዙሪያ ያሉት ሐሳቦች ጥቅሱ በአዲሱ የአምላክ ሥርዓት በምድር ስለሚኖረው ሕይወት እንደሚናገር ያሳያሉን? በቁጥር 6–8 መሠረት ጳውሎስ የጻፋቸውን ነገሮች ያላስተዋሉት የማን ዓይኖችና ጆሮዎች ነበሩ?
(4 ) የምታነበውን ‘እንዴት ልሠራበት እችላለሁ? ’ እያልክ ራስህን ጠይቅ።
ዘፍጥረት 4:3–12፤ 1 ዮሐንስ 3:10–15፤ ዕብራውያን 11:4)
ቃየን አቤልን እንደገደለ የሚገልጸውን ታሪክ የምናየው እንደማንኛውም ታሪክ አድርገን ነው ወይስ ለእኛ ምክር ይዟል? (ከዘፀአት ጀምሮ እስከ ዘዳግም ድረስ የተገለጸውን የእስራኤል የምድረበዳ ታሪክ ስናነብ ለግላችን ምን ትምህርት መውሰድ አለብን? (1 ቆሮንቶስ 10:6–11)
ቅቡዓን ክርስቲያኖች ምን ዓይነት አኗኗር ሊኖራቸው እንደሚገባ የተጻፈው ምክር በምድር ላይ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ተስፋ ለሚያደርጉት ይሠራልን? (ከዘኁልቁ 15:16 ጋር አወዳድር፤ ዮሐንስ 10:16)
በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ጥሩ አቋም ቢኖረንም ቀደም ብለን የምናውቀውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር በምን ሌሎች መንገዶች የበለጠ ልንሠራበት እንደምንችል ማሰብ ያስፈልጋልን? (2 ቆሮንቶስ 13:5፤ 1 ተሰሎንቄ 4:1)
(5 ) የምታነበውን ሌሎችን ለመርዳት እንዴት ልትጠቀምበት እንደምትችል አስብበት።
ከሞት ስለተነሳችው የኢያኢሮስ ልጅ በሚናገረው ታሪክ እነማንን ለመርዳት እንችላለን? (ሉቃስ 8:41, 42, 49–56)
13. ከይሖዋ ድርጅት ጋር እየተባበርን ሳናቋርጥ መጽሐፍ ቅዱስን ብናነብና ብናጠና ምን ውጤቶችን እንደምናገኝ ልንጠባበቅ እንችላለን?
13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን በዚህ መንገድ ሲከናወን በአጸፋው እንዴት ብዙ ጥቅም እናገኝበታለን! እርግጥ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ትዕግሥትን ይፈታተናል ምክንያቱም በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ሳናቆም ልንከታተለው የምንችል ጠቃሚ ፕሮጄክት ነው። በመንፈሳዊነታችን እየበረታን እንሄዳለን። ከአፍቃሪው አባታችን ከይሖዋና ከክርስቲያን ወንድሞቻችን ጋር የበለጠ ያቀራርበናል። “የሕይወትን ቃል አጥብቃችሁ ያዙ” የሚለውን ምክር በሥራ ላይ ለማዋል ይረዳናል። — ፊልጵስዩስ 2:16 አዓት
የክለሳ ውይይት
● መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውና እስከ ዘመናቸን ድረስ ተጠብቆ የቆየልን ለምንድን ነው?
● ሌሎች ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲወዱ እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን?
● ዘወትር መጽሐፍ ቅዱስን በግል ማንበብ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? የምናነበውን ከየትኞቹ አምስት አቅጣጫዎች ብንመለከት እንጠቀማለን?
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 27 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]
መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የሚከተሉትን አስብባቸው:-
እያንዳንዱ የምንባቡ ክፍል ይሐዋን ምን ዓይነት አምላክ አድርጎ እንደሚገልጸው
ከመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ መልዕክት ጋር እንዴት እንደሚያያዝ
ከጥቅሱ ዙሪያ ያሉት ሐሳቦች ትርጉሙን እንዴት እንደሚነኩ
የራስህን ሕይወት እንዴት ሊነካው እንደሚገባ
ሌሎችን ለመርዳት እንዴት ልትጠቀምበት እንደምትችል