“የዓለም ክፍል አይደሉም”
ምዕራፍ 21
“የዓለም ክፍል አይደሉም”
1. (ሀ) ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት ስለ ደቀ መዛሙርቱ ምን ብሎ ጸለየ? (ለ) ‘የዓለም ክፍል አለመሆን’ በጣም አስፈላጊ የነበረው ለምንድን ነው?
ኢየሱስ እንደነገው ሊሰቀል እንደ ዛሬ ማታ ስለ ደቀ መዛሙርቱ አጥብቆ ጸልዮአል። ሰይጣን ከባድ ተጽዕኖ እንደሚያመጣባቸው በማወቅ ለአባቱ እንዲህ አለ:- “ከዓለም እንድታወጣቸው ሳይሆን ከክፉው የተነሳ እንድትጠብቃቸው እለምንሃለሁ። እኔ የዓለም ክፍል እንዳልሆንሁ እነርሱም የዓለም ክፍል አይደሉም።” (ዮሐንስ 17:15, 16 አዓት) ከዓለም መለየት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ገዥው ሰይጣን ስለሆነ ነው። የዓለም ክፍል የሆኑት ሁሉ በቁጥጥሩ ሥር ወድቀዋል። (ዮሐንስ 14:30፤ 1 ዮሐንስ 5:19) ሁኔታው እንደዚህ ስለሆነ እያንዳንዱ ክርስቲያን ‘የዓለም ክፍል አለመሆን’ ምን ትርጉም እንዳለው መረዳት ያስፈልገዋል። ታዲያ ኢየሱስ የዓለም ክፍል ያልነበረው እንዴት ነው?
2. ኢየሱስ “የዓለም ክፍል” ያልነበረው በምን መንገዶች ነው?
2 ኢየሱስ ራሱን ከሌሎች ሰዎች አግልሎ እንዳልኖረ የታወቀ ነው። “የዓለም ክፍል” አለመሆኑ ለሌሎች ፍቅር አልነበረውም ማለት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ከከተማ ወደ ከተማ እየሄደ የአምላክን መንግሥት ምሥራች ነግሯቸዋል። የታመሙትን ፈውሷል፣ የታወሩት እንዲያዩ አደርጓል፣ የሞቱትን አስነስቷል፣ ሕይወቱንም ለሰው ልጆች ሰጥቷል። ሆኖም በዓለም መንፈስ የተሞሉ ሰዎች የነበራቸውን አምላካዊ ያልሆነ ዝንባሌና ክፉ ድርጊታቸውን አልወደደም። ሰዎች የምንዝር ምኞት እንዳያድርባቸው፣ የፍቅረ ንዋይ መንገድ እንዳይከተሉና በራስ ወዳድነት ተገፋፍተው ከሌላው ልቀው ለመታየት እንዳይፈልጉ አስጠንቅቋል። (ማቴዎስ 5:27, 28፤ 6:19–21፤ ሉቃስ 12:15–21፤ 20:46, 47) ኢየሱስ ከአምላክ የራቁትን ሰዎች አኗኗር በመከተል ፈንታ በይሖዋ መንገዶች ተመላልሷል። (ዮሐንስ 8:28, 29) ምንም እንኳን ኢየሱስ ራሱ አይሁዳዊ ቢሆንም በሮምና በአይሁዶች መካከል በነበረው ፖለቲካዊ ውዝግብ ረገድ የአንዱም ወገን ደጋፊ አልሆነም።
“መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል አይደለችም”
3. (ሀ) የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች ለጲላጦስ ስለ ኢየሱስ ምን ክስ አቀረቡ? ለምንስ? (ለ) ኢየሱስ ሰብዓዊ ንጉሥ ለመሆን ምንም ፍላጎት እንዳልነበረው የሚያሳየው ምንድን ነው?
3 የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች ግን ኢየሱስ መንግሥትን ለመገልበጥ ያሴራል ብለው ከሰሱት። ካስያዙት በኋላ ወደ ሮማዊው አገረ ገዥ ወደ ጴንጤናዊው ጲላጦስ ወሰዱት። በጣም የተረበሹበት ጉዳይ የኢየሱስ ትምህርት የእነርሱን ግብዝነት የሚያጋልጥ መሆኑ ነበር። ሆኖም አገረ ገዥው እርምጃ እንዲወስድበት በማለት “ይህ ሕዝባችንን ሲያጣምም ለቄሳርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል ደግሞም እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ ሲል አገኘነው” ብለው ከሰሱት። (ሉቃስ 23:2) እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ከዚያ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ሕዝቡ ንጉሥ ሊያደርጉት ሲሞክሩ ኢየሱስ እምቢ ብሏቸው ነበር። (ዮሐንስ 6:15) ወደፊት ሰማያዊ ንጉሥ እንደሚሆንና ያ ጊዜ ገና እንዳልደረሰ እንዲሁም በዙፋን ላይ የሚቀመጠው በዲሞክራቲካዊ መንገድ በሕዝብ ተመርጦ ሳይሆን በይሖዋ አምላክ በመሾም መሆኑን ያውቅ ነበር።
4. ኢየሱስ ለቄሳር ግብር ስለ መክፈል ምን አቋም እንደነበረው ተጨባጩ ማስረጃ ምን ያሳያል?
4 ግብር ስለ መክፈልም ቢሆን ኢየሱስ ከመያዙ ሦስት ቀን ቀደም ብሎ ፈሪሳውያን በዚህ ጉዳይ እርሱን ለመወንጀል የሚያስችል ቃል ለማናገር ሞክረው ነበር። ኢየሱስ የተንኰል ጥያቄአቸውን ሲመልስ “አንድ ዲናር [የሮማውያን ሳንቲም] አሳዩኝ፤ መልኩ ጽሕፈቱስ የማን ነው?” አላቸው። “የቄሳር ነው” የሚል መልስ ሲሰጡት “እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ ብሎ መለሰላቸው።” —5. (ሀ) ኢየሱስ በተያዘበት ወቅት ለደቀመዛሙርቱ ምን ትምህርት ሰጠ? (ለ) ኢየሱስ እንደዚያ ያደረገበትን ምክንያት ለጲላጦስ የገለጸለት እንዴት ነው?
5 ኢየሱስ በተያዘበት ጊዜ የታየው ሁኔታ በሮም ላይ ለማሳደምም ሆነ ደቀ መዛሙርቱ እንዲያምጹ ለማድረግ ምንም ፍላጎት እንዳልነበረው ያረጋግጣል። የሮም ወታደሮች ከአይሁዶች ጋር ሆነው ሰይፍና ዱላ ይዘው ኢየሱስን ለመያዝ መጡ። (ዮሐንስ 18:3, 12፤ ማርቆስ 14:43) ሐዋርያው ጴጥሮስ ይህንን ሲያይ ሰይፉን መዘዘና ከሰዎቹ አንዱን መትቶ የቀኝ ጆሮውን ቆረጠው። ኢየሱስ ግን ጴጥሮስን ገሰጸውና “ሰይፍ የሚያነሱ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ” አለው። (ማቴዎስ 26:51, 52) ኢየሱስ ለምን እንደዚያ ብሎ እንደተናገረ በማግሥቱ ጠዋት በጲላጦስ ፊት ቀርቦ እንደሚከተለው ሲል ገልጿል:- “መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል አይደለም። መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል ቢሆን ኖሮ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር። ነገር ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለም።” — ዮሐንስ 18:36 አዓት
6. ኢየሱስ ለፍርድ ከቀረበ በኋላ በመጨረሻው ምን ሆነ?
6 ጲላጦስ የቀረበለትን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በኢየሱስ ላይ የተነሳው ክስ መሠረት የለውም ብሎ ወሰነ። ይሁን እንጂ ለሕዝቡ ጥያቄ ተንበረከከና ኢየሱስ እንዲሰቀል አደረገ። — ሉቃስ 23:13–15፤ ዮሐንስ 19:12–16
ደቀ መዛሙርቱ የጌታቸውን ምሳሌ ተከተሉ
7. የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች የዓለምን መንፈስ እንደሚጠሉ ነገር ግን ሰዎችን እንደሚወዱ ያሳዩት እንዴት ነው?
7 የኢየሱሰ ደቀመዛሙርት “የዓለም ክፍል” አለመሆን ምን ማድረግን እንደሚጠይቅ ገብቷቸው እንደነበረ በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች የታሪክ መጻሕፍት ላይ የተመዘገበው የጥንት ክርስቲያኖች ታሪክ ያሳያል። ከዓለም መንፈስ ለመራቅ ጥረት አድርገዋል። ወደ ሮማውያን የቲያትር አዳራሾች ገብተው የአመጽና የብልግና ትርኢቶች ለማየት እምቢ ስላሉ የሰውን ዘር የሚጠሉ እየተባሉ መዘባበቻ ይደረጉ ነበር። እነርሱ ግን ሰዎች የአምላክን ፍቅራዊ የመዳን ዝግጅት እንዲጠቀሙበት ለመርዳት ይደክሙ ነበር እንጂ ለሰው ልጆች ጥላቻ አልነበራቸውም።
8. (ሀ) እነዚያ የመጀመሪያ ደቀ መዛሙርት “የዓለም ክፍል” ባለመሆናቸው የተነሳ ምን ደረሰባቸው? (ለ) ይሁን እንጂ ለፖለቲካ መሪዎችና ግብር ለመክፈሉ ጉዳይ እንዴት ያለ አመለካከት ነበራቸው? ለምንስ?
8 እንደ ጌታቸው ሁሉ እነርሱም ብዙውን ጊዜ የተሳሳተ ሪፖርት ከደረሳቸው የመንግሥት ባለ ሥልጣኖች ከባድ ስደት ይመጣባቸው ነበር። (ዮሐንስ 15:18–20) ሐዋርያው ጳውሎስ በ56 እዘአ ገደማ በሮም ለነበሩት ክርስቲያኖች ደብዳቤ ጽፎ ኢየሱስ ቀደም ሲል የሰጠውን ምክር አጠናክሯል። “ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ በበላይ ላሉት ባለሥልጣኖች” ይኸውም ለፖለቲካ መሪዎች እንዲገዙ በብርቱ አሳሰባቸው። መንግሥታትን ያቋቋመው ይሖዋ ነው ማለት ሳይሆን መንግሥታት የሚገዙት በይሖዋ ፈቃድ ነው ማለቱ ነው። ጳውሎስ “ያሉትም ባለሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው” ብሏል። ይህ የሆነበት ምክንያት እነዚህ መንግሥታት ወደ ሥልጣን የሚመጡበትን ቅደም ተከተል አምላክ አስቀድሞ ስላወቀና ስለተናገረ ነው። እንግዲያው በኢየሱስ ክርስቶስ የሚመራው የአምላክ መንግሥት ብቻውን ምድርን መግዛት እስኪጀምር ድረስ ለአሁኑ ጊዜ ያለው “የእግዚአብሔር ሥርዓት” “በበላይ ያሉት ባለሥልጣኖች” ናቸው ማለት ነው። በዚህ ምክንያት ጳውሎስ ክርስቲያኖች ለዓለማዊ ባለሥልጣኖች ተገቢ አክብሮት እንዲያሳዩና የሚመድቡባቸውን ግብር እንዲከፍሉ መክሯቸዋል። — ሮሜ 13:1–7፤ ቲቶ 3:1, 2
9. (ሀ) “በበላይ ላሉት ባለሥልጣኖች” ስንገዛ ምንን መዘንጋት የለብንም? (ለ) የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ምሳሌ በጥንቃቄ እንደተከተሉ ታሪክ የሚያሳየው እንዴት ነው?
9 ነገር ግን ጳውሎስ አምላክን፣ ቃሉንና ክርስቲያናዊ ሕሊናን ገሸሽ አድርገው ሙሉ በሙሉ እንዲገዙላቸው አልተናገረም። ኢየሱስ ይሖዋን ብቻ እንዳመለከ፣ ሕዝቡ ንጉሥ እናድርግህ ሲሉት እምቢ እንዳላቸውና ጴጥሮስን ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ እንዳለው ክርስቲያኖች ያውቃሉ። የጌታቸውን አርአያ በጥንቃቄ ተከትለዋል። የሥልጣኔ ጉዞ፣ የዓለም ታሪክ የተባለው በሔኬልና ሲግማን የተዘጋጀ መጽሐፍ በገጽ 237, 238 ላይ እንዲህ ይላል:- “ክርስቲያኖች የሮም ዜጎችን አንዳንድ ግዴታዎች አንፈጽምም ይሉ ነበር። ወታደር ሆኖ ማገልገል እምነታቸውን እንደሚጻረር ይሰማቸው ነበር። የፖለቲካ ሥልጣን አይዙም፣ ንጉሠ ነገሥቱን ለማምለክ እምቢ ይሉ ነበር።”
10. (ሀ) በኢየሩሳሌም የነበሩት ክርስቲያኖች በ66 እዘአ ላይ የወሰዱትን እርምጃ ለምን ወሰዱ? (ለ) ይህስ ጠቃሚ ትምህርት የሚሰጠን በምን መንገድ ነው?
10 የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በጊዜአቸው በነበረው ፖለቲካዊና ወታደራዊ ውዝግብ ረገድ ጥብቅ የሆነ የገለልተኝነት አቋም ወስደዋል። በ66 እዘአ ይሁዳ በተባለችው የሮም ክፍለ ሀገር የነበሩት አይሁዶች በቄሳር ላይ ዓመጹ። የሮም ወታደሮች ኢየሩሳሌምን በፍጥነት ከበቡ። ታዲያ በከተማዋ የነበሩት ክርስቲያኖች ምን አደረጉ? ኢየሱስ ገለልተኞች እንዲሆኑና ከተዋጊዎቹ ሠራዊቶች እንዲሸሹ የሰጣቸውን ምክር አስታወሱ። የሮም ወታደሮች ከበባውን ለጊዜው ተወት አድርገው ሲሄዱ ክርስቲያኖች አጋጣሚውን በመጠቀም የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ፔላ ወደተባለ ተራራማ ስፍራ ሸሹ። (ሉቃስ 21:20–24) በወሰዱት የገለልተኝነት አቋም ከእነርሱ በኋላ ለሚመጡት ክርስቲያኖች ታማኝ ምሳሌ ሆነው አገልግለዋል።
በፍጻሜው ዘመን ያሉ ገለልተኛ ክርስቲያኖች
11. (ሀ) የይሖዋ ምስክሮች የትኛውን ሥራ ለመሥራት ይሯሯጣሉ? ለምንስ? (ለ)በምን ጉዳይ ገለልተኞች ናቸው?
ማቴዎስ 24:14) በብሔራት መካከል በሚደረገው ግጭት ግን ጥብቅ የገለልተኝነት አቋም ወስደዋል።
11 በ1914 እዘአ ከጀመረው “የፍጻሜ ዘመን” ወዲህ የእነዚያን የጥንት ክርስቲያኖች ምሳሌ በመከተል ክርስቲያናዊ ገለልተኝነትን የጠበቀ የሰዎች ቡድን እንዳለ የታሪክ መዝገብ ያሳያልን? አዎን፤ የይሖዋ ምስክሮች እንደዚህ ያለ አቋም ወስደዋል። ጽድቅን ለሚወዱ ሁሉ ሰላም፣ ብልጽግናና ዘላቂ ደስታ የሚያመጣላቸው የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው እያሉ በዓለም ዙሪያ ለመስበክ ይሯሯጣሉ። (12. (ሀ) የይሖዋ ምስክሮች ገለልተኝነት ከቄሶች አቋም ጋር ሲነጻጸር እንዴት ሆኖ እናገኘዋለን? (ለ) የይሖዋ ምስክሮች ከፖለቲካ ገለልተኞች መሆናቸው ምንን ይጨምራል?
12 ከዚህ አንጻር ግን የሕዝበ ክርስትና ቄሶች በዓለም የፖለቲካ ጉዳዮች በከፍተኛ ሁኔታ ተጠላልፈዋል። በአንዳንድ አገሮች የመሪ ምርጫ በሚካሄድበት ጊዜ ተመራጮቹን በመደገፍ ወይም በመቃወም ዘመቻ ያካሄዳሉ። አንዳንድ ቄሶች ራሳቸው የፖለቲካ ሥልጣን ጨብጠዋል። በፖለቲካ መሪዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማድረግ ራሳቸው ወደፈለጉት አቅጣጫ የሚጠመዝዟቸው ቄሶችም አሉ። በሌሎች ስፍራዎች “ወግ አጥባቂ” የሚባሉት ቄሶች በሥልጣን ላይ ያሉት መሪዎች የቅርብ ደጋፊዎች ሲሆኑ “ተራማጅ” የሚባሉት ቄሶች ደግሞ መንግሥቱን ለመገልበጥ የሚታገሉትን የደፈጣ ተዋጊዎች ይደግፋሉ። የይሖዋ ምስክሮች ግን በየትኛውም አገር ቢኖሩ በፖለቲካ ውስጥ አይገቡም። ሆኖም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ለመሆን፣ በምርጫ ውድድር ውስጥ ለመግባት ወይም ድምፅ ለመስጠት
የሚፈልጉ ሰዎች ካሉ የይሖዋ ምሥክሮች ጣልቃ አይገቡባቸውም። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ “የዓለም ክፍል” አይሆኑም ብሎ ስለተናገረ የይሖዋ ምስክሮች በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ፈጽሞ አይሳተፉም።13. የይሖዋ ምስክሮች በጦርነት ስለመካፈል ያላቸው አቋም ተጨባጩ ማስረጃ ምን ያሳያል?
13 ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረው በዚህ “የፍጻሜ ዘመን” መንግሥታት በተደጋጋሚ ጦርነት አድርገዋል። በአንድ አገር ውስጥ ያሉ ተቀናቃኝ ወገኖችም እርስ በርሳቸው ተዋግተዋል። (ማቴዎስ 24:3, 6, 7) ይህ ሁሉ ሲሆን የይሖዋ ምስክሮች ምን አቋም ወሰዱ? ለዚህ ዓይነቱ ግጭት የሚያሳዩት የገለልተኝነት አቋም በሁሉም የዓለም ክፍሎች በደንብ የታወቀ ነው። ኅዳር 1, 1939 የወጣው መጠበቂያ ግንብ ኢየሱስ ክርስቶስ ከወሰደው በኋላም የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ካሳዩት አቋም ጋር በመስማማት እንዲህ ብሏል:- “ከጌታ ጎን የተሰለፉት ሁሉ በተፋላሚዎቹ ብሔራት ረገድ ገለልተኛ አቋም ይወስዳሉ። የሚቆሙት ለታላቁ ቲኦክራት [ለይሖዋና] እርሱ ለሾመው ንጉሥ [ለኢየሱስ ክርስቶስ] ነው።” በሁሉም ብሔራትና በማንኛውም ሁኔታ ሥር የሚገኙት የይሖዋ ምስክሮች በዚህ አቋማቸው እንደጸኑ ተጨባጭ ማስረጃዎቹ ያሳያሉ። ሰዎችን የሚከፋፍለው ፖለቲካና ጦርነት ይሖዋን በማምለክ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ወንድማማችነት እንዲያፈርስባቸው አልፈቀዱለትም። — ኢሳይያስ 2:3, 4፤ ከ2 ቆሮንቶስ 10:3, 4 ጋር አወዳድር።
14. (ሀ) ምስክሮቹ በገለልተኛ አቋማቸው የተነሳ ሌላስ ምን ነገር አናደርግም ብለዋል? (ለ) ለዚህስ ምን ምክንያት ይሰጣሉ?
14 ባለፉት ሃምሳ ዓመታት የይሖዋ ምስክሮች መለዮ ለባሽ በመሆን የጦር መሣሪያ ለመያዝ እምቢ ከማለታቸውም ሌላ የውትድርና አገልግሎት ምትክ የሆነ ውጊያን የማይመለከት ሌላ ዓይነት አገልግሎት ለመፈጸም ፈቃኞች እንዳልሆኑ የታሪክ መዝገብ ያሳያል። ለምን ፈቃደኞች አልሆኑም? አምላክ ምን እንደሚፈልግባቸው ካጠኑ በኋላ ከሕሊናቸው ጋር የሚስማማ የግል ውሳኔ ስላደረጉ ነው። ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማንም አይነግራቸውም። ሌሎች የመረጡትን ሲያደርጉም ጣልቃ አይገቡባቸውም። ነገር ሮሜ 6:12–14፤ 12:1, 2፤ ሚክያስ 4:3
ግን አቋማቸውን እንዲያስረዱ ሲጠየቁ የይሖዋ ምስክሮች ራሳቸውን ለአምላክ የወሰኑ ሰዎች እንደመሆናቸው መጠን ሰውነታቸውን ለአምላክ አገልግሎት እንዲጠቀሙበት ግዴታ የገቡ መሆናቸውንና ከአምላክ ዓላማ ተጻራሪ የሆነ ነገር ለሚያደርጉ ምድራዊ ጌቶች ሊሰጡት እንደማይችሉ ይገልጻሉ። —15. (ሀ) የይሖዋ ምስክሮች ከዓለም የተለዩ ስለሆኑ ምን ይደርስባቸዋል? (ለ) በእሥር ላይ እያሉም ቢሆን በክርስቲያናዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች የተመሩት እንዴት ነው?
15 ከዚህ የተነሳ “የዓለም ክፍል ስላልሆናችሁ ዓለም ይጠላችኋል” ብሎ ኢየሱስ የተናገረው ቃል ተፈጽሞባቸዋል። (ዮሐንስ 15:19) ብዙ የይሖዋ ምስክሮች ክርስቲያናዊ ገለልተኝነታቸውን አንጥስም በማለታቸው ታሥረዋል። አንዳንዶች በጭካኔ ተደብድበዋል፣ እስከ ሞት ድረስ የተደበደቡም አሉ። ሌሎችም በብዙ የእሥራት ዓመታት በገለልተኝነታቸው ቀጥለዋል። አና ፖዌልዚንስካ የጻፉት በአውሽቪትስ የታየው አቋምና ግፍ የተባለው መጽሐፍ በገጽ 89 ላይ እንዲህ ይላል:- “በማጎሪያ ካምፕ ከነበሩት የይሖዋ ምስክሮች መካከል አንዱም ቢሆን ከሃይማኖታዊ እምነቱ የሚጻረር ትእዛዝ እንደማይፈጽም ወይም በሌላ ሰው ላይ፣ ለምሳሌ በነፍሰ ገዳዮች ወይም ኤስ ኤስ በተባሉት የፖሊስ ባለስልጣኖች ላይ፣ ምንም ዓይነት ክፉ ነገር እንደማያደርግ ሁሉም እስረኛና ወታደሮች ያውቁ ነበር። ሌላ ዓይነት ሥራ ከተሰጣቸው ግን ሥነ ምግባር የማያስጥስ እስከ ሆነ ድረስ የቱንም ያህል የሚያስጠላ ሥራ ቢሆንም ችሎታቸው በሚፈቅድላቸው ሁሉ ይሠሩታል።”
16. (ሀ) ሁሉም ብሔራት ወዴት እየተጓዙ ነው? በመሆኑም የይሖዋ ምስክሮች ምን እንዳያደርጉ ይጠነቀቃሉ? (ለ) እንግዲያው ከዓለም መለየት ይህን ያህል ከባድ ጉዳይ የሆነው ለምንድን ነው?
16 የይሖዋ ምስክሮች ሁሉም ብሔራት በአርማጌዶን ወደሚሆነው “ሁሉን የሚችለው አምላክ ታላቅ የጦርነት ቀን” እየተጓዙ እንዳሉ ያውቃሉ። የይሖዋ አገልጋዮች እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው በመሲሐዊው መንግሥት ጎን ተሰልፈዋል። ስለዚህ ሰዎች ያንን መንግሥት የሚጻረር አቋም እንዲወስዱ እንዳያደርጓቸው ይጠነቀቃሉ። (ራእይ 16:14, 16 አዓት፤ 19:11–21) ኢየሱስ ተከታዮቹ “የዚህ ዓለም ክፍል አይደሉም” ሲል የተናገረው ቃል ምን ያህል ጥብቅ እንደሆነ ይገነዘባሉ። ይህ አሮጌ ዓለም በቅርቡ እንደሚጠፋና የአምላክን ፈቃድ ከልባቸው የሚያደርጉት ብቻ ለዘላለም እንደሚኖሩ ያውቃሉ — 1 ዮሐንስ 2:15–17
የክለሣ ውይይት
● ‘የዓለም ክፍል አለመሆን’ ምንን እንደሚጨምር ኢየሱስ ያሳየው እንዴት ነው?
● የመጀመረያዎቹ ክርስቲያኖች (1) ለዓለም መንፈስ (2) ለዓለማዊ ባለሥልጣኖችና ግብርን ለመክፈሉ ጉዳይ (3) ለውትድርና አገልግሎት የነበራቸውን አቋም የሚያመለክተው ምንድን ነው?
● በዛሬው ዘመን የይሖዋ ምስክሮች ክርስቲያናዊ ገለልተኝነት እንደሚጠብቁ የሚያሳዩት በምን በምን መንገዶች ነው?
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]