የይሖዋ ዓላማ ወደ ታላቅ ግቡ ሲደርስ
ምዕራፍ 24
የይሖዋ ዓላማ ወደ ታላቅ ግቡ ሲደርስ
1, 2. (ሀ) ይሖዋ የማሰብ ችሎታ ያላቸውን ፍጡሮቹ በተመለከተ ምን ዓላማ አለው? (ለ) አንድነት ያለው ይሖዋን የሚያመልከው ቤተሰብ አባሎች እነማን ነበሩ? (ሐ) ይህንን በሚመለከት የትኛው የግል ጥያቄ ሊታሰብበት ይገባል?
የማሰብ ችሎታ ያላቸው ፍጡሮች በሙሉ በእውነተኛው አምልኮ በአንድነት በመጠቃለል የአምላክን ልጆች ታላቅ ነፃነት አግኝተው በደስታ ይኖራሉ። የይሖዋ ጥበባዊና ፍቅራዊ ዓላማ ይህ ነው። ጽድቅን የሚያፈቅሩ ሁሉ አጥብቀው የሚመኙት ነገርም ይኸው ነው።
2 ይሖዋ ይህንን ታላቅ ዓላማ መፈጸም የጀመረው ገና የፍጥረት ሥራውን እንደጀመረ ነው። ይሖዋ በመጀመሪያ የፈጠረው “የክብሩ ነፀብራቅ፣ የባሕርዩም ትክክለኛ ምሳሌ” የሆነውን ዕብራውያን 1:1–3 አዓት) ይኸኛው ልጁ አምላክ ብቻውን የፈጠረው ስለሆነ ከፍጥረታት ሁሉ የተለየ ነበር። በእርሱ አማካኝነት ሌሎች ልጆች ይኸውም በመጀመሪያ የሰማይ መላእክት፣ በኋላም በምድር የሚኖሩ ሰዎች ተፈጠሩ። (ኢዮብ 38:7፤ ሉቃስ 3:38) እነዚህ ሁሉ አንድ ጽንፈ ዓለማዊ ቤተሰብ ሆኑ። ለሁሉም አምላካቸው ይሖዋ ነበር። የሚያመልኩት እርሱን ብቻ ነበር። የጽንፈ ዓለም ሉዓላዊ ገዥ እርሱ ነበር። በተጨማሪም ይሖዋ አፍቃሪ አባታቸው ነበር። የአንተስ አባት ነውን? ከልጆቹ አንዱ ነህን? ይህ እንዴት ያለ ግሩም ዝምድና ነው!
ልጁን ነው። (3. (ሀ) ስንወለድ ሁላችንም የአምላክ ልጆች ያልነበርነው ለምንድን ነው? (ለ) ሆኖም ይሖዋ ለአዳም ልጆች ምን ፍቅራዊ ዝግጅት አደረገ?
3 ይሁን እንጂ አንድ ልንክደው የማንችል ሐቅ አለ። የመጀመሪያዎቹ ሰብአዊ ወላጆቻችን አውቀው ኃጢአት በመሥራታቸው አምላክ ሞት ፈረደባቸውና ከኤደን አስወጣቸው፤ ልጆቹ ከመሆንም ሰረዛቸው። የጽንፈ ዓለሙ የይሖዋ ቤተሰብ አባል መሆናቸውን አቆሙ። (ዘፍጥረት 3:22–24፤ ከዘዳግም 32:4, 5 ጋር አወዳድር) ሁላችንም የኃጢአተኛው የአዳም ዘሮች ስለሆንን ወደ ኃጢአት ከሚገፋፉ ዝንባሌዎች ጋር ተወልደናል። እንግዲህ ከአምላክ ቤተሰብ ከተባረሩ ወላጆች የተገኘን ልጆች በመሆናችን በሰብአዊ ትውልዳችን መሠረት የአምላክ ልጆች ነን ለማለት አንችልም። ይሁን እንጂ ይሖዋ ከአዳም ዘሮች መካከል አንዳንዶቹ ጽድቅን የሚወዱ እንደሚሆኑ ያውቅ ነበር። ለእነዚህ ሰዎች ይሖዋ ወደ አምላክ ልጆች ታላቅ ነፃነት የሚደርሱበትን ፍቅራዊ ዝግጅት አድርጎላቸዋል። — ሮሜ 8:20, 21
የእስራኤል ሕዝብ ያገኘው ልዩ የዝምድና አቋም
4. (ሀ) እስራኤላውያን የአምላክ “ልጆች” የነበሩት በምን መሠረት ነው? (ለ) ይሁን እንጂ ይህ ምን ማለት አልነበረም?
4 አዳም ከተፈጠረ ከ2, 500 ዓመታት በኋላ ይሖዋ ለአንዳንድ ዘፀአት 4:22, 23፤ ዘፍጥረት 12:1, 2) በኋላም በሲና ተራራ ለእስራኤል ሕጉን ሰጠ፤ እንደ አንድ ብሔር አድርጎም አደራጃቸው። ከዓላማው ጋር በተያያዘ ሁኔታም ተጠቀመባቸው። በብሔር ደረጃ ሲታዩ “የይሖዋ ልዩ ንብረት” ስለነበሩ “የአምላክ ልጆች” ተብለው ተጠርተዋል። (ዘዳግም 14:1, 2፣ ኢሳይያስ 43:1) ከዚህም ሌላ ከመካከላቸው ከአንዳንዶቹ ጋር በነበረው ልዩ ግንኙነት የተነሣ ይሖዋ ልጆቹ እንደሆኑ አድርጎ ይናገርላቸው ነበር። (1 ዜና. 22:9, 10) ይህ የልጅነት አቋም ከአምላክ ጋር በገቡት ቃል ኪዳን ላይ የተመሠረተ ነበር። ሆኖም አዳም የአምላክ ልጅ ሳለ የነበረውን ታላቅ ነፃነት አገኙ ማለት አልነበረም። አሁንም ገና በኃጢአትና በሞት ባርነት ስር ነበሩ።
ሰዎች ልጆቹ የመሆንን መብት እንደገና ሰጠ። ይሖዋ ለአብርሃም በገባው ቃል ኪዳን መሠረት እስራኤላውያን ሕዝቡ እንዲሆኑ መረጣቸው። ስለሆነም ለግብጹ ንጉሥ ለፈርዖን በላከው መልዕክት ላይ “እስራኤል ልጄ” እያለ ተናግሯል። (5. የእስራኤል ሕዝብ በአምላክ ፊት የነበረውን ልዩ አቋም ያጣው እንዴት ነው?
5 ቢሆንም እንደ ልጆቹ ስለተቆጠሩ በአምላክ ፊት ከሌሎች ሕዝቦች የተለየ የዝምድና አቋም አግኝተው ነበር። በተጨማሪም አባታቸውን የማክበርና ከዓላማዎቹ ጋር የሚስማማ ሥራ የመሥራት ኃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር። ኢየሱስ ያንን ግዴታ መፈጸማቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አጥብቆ ሲገልጽ አምላክን አባታችን ብለው መጥራታቸው እንደማይበቃና ልጆቹ መሆናቸውን በሥራ ማሳየት እንዳለባቸው ገልጾላቸዋል። (ማቴዎስ 5:43–48፣ ሚልክያስ 1:6) ይሁን እንጂ አይሁዶች በብሔር ደረጃ ይህንን ብቃት ሳያሟሉ ቀሩ። ስለዚህ በኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎት መጨረሻ ዓመት ላይ እርሱን ለመግደል ይፈልጉ የነበሩት አይሁዶች “አንድ አባት አለን፣ እርሱም እግዚአብሔር ነው” ብለው በተናገሩ ጊዜ ሥራቸውና የሚያሳዩት መንፈስ አባባላቸውን ውሸት እንደሚያደርግባቸው ኢየሱስ ጠንከር አድርጎ ነገራቸው። (ዮሐንስ 8:41, 44, 47) በ33 እዘአ አምላክ የሕጉን ቃል ኪዳን ሻረው። ስለዚህ እስራኤላውያን ከይሖዋ ጋር ልዩ ዝምድና እንዲኖራቸው ያደረገው መሠረት ፈረሰ። ይሁን እንጂ ይሖዋ ከሰው ልጆች መካከል እንደ ልጆቹ አድርጎ የሚቀበላቸው ሰዎች አልጠፉም።
ይሖዋ ሕዝቡን አንድ አደረገ
6. በኤፌሶን 1:9, 10 ላይ ጳውሎስ ስለየትኛው “አስተዳደር” ገልጿል? የአስተዳደሩ ግብ ምንድን ነው?
ኤፌ.1:9, 10 አዓት) ይህ “አስተዳደር” በኢየሱስ ክርስቶስ ማዕከልነት የተገነባ ነው። በእርሱ አማካኝነት ሰዎች በአምላክ ፊት ተቀባይነት ወደሚያገኙበት ሁኔታ ይመጣሉ። አንዳንዶቹ ወደ ሰማይ የመሄድ ሌሎቹ በምድር ላይ የመኖር ተስፋ ይዘው ለይሖዋ በታማኝነት ከቆሙት የአምላክ መላእክታዊ ልጆች ጋር በአንድነት ያገለግላሉ።
6 ሐዋርያው ጳውሎስ ይሖዋ ሕዝቡን አንድ ለማድረግ ስላለው ፕሮግራም፤ ማለትም እምነት ያላቸው ሁሉ የቤተሰቡ ውድ አባላት ስለሚሆኑበት የአምላክ ዝግጅት በኤፌሶን ለነበሩት ክርስቲያኖች ሲጽፍ እንዲህ ብሏል:- “[አምላክ] የፈቃዱን ቅዱስ ምሥጢር አስታውቆናል። አስቀድሞ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ አንድ አስተዳደር [የቤተሰብ አስተዳደር] አቋቋመ። በሰማይ ያሉትን ነገሮችና በምድር ያሉትን ነገሮች እንደገና በክርስቶስ ለመሰብሰብ በጎ ዓላማው ነው።” (7. “በሰማይ ያሉት ነገሮች” ምንድን ናቸው? አንድ ላይ መሰብሰባቸውስ ለእነርሱ ምን ትርጉም ይኖረዋል?
7 በ33 እዘአ ከዋለው የጴንጠቆስጤ ዕለት ጀምሮ በመጀመሪያ ‘በሰማይ ላሉት ነገሮች’ ማለትም በሰማያዊው መንግሥት ከክርስቶስ ጋር ወራሽ ለሚሆኑት ትኩረት ተሰጥቷል። እነርሱም የኢየሱስ መሥዋዕት ባለው ዋጋ ላይ ባላቸው እምነት መሠረት የጸደቁ መሆናቸውን አምላክ አስታውቆላቸዋል። (ሮሜ 5:1, 2) ከዚያም ‘እንደገና ተወለዱ’ ማለትም ሰማያዊ ተስፋ ያላቸው የአምላክ ልጆች ሆነው ተወለዱ። (ዮሐንስ 3:3፤ 1:12, 13) እነዚህ አንድ መንፈሳዊ ሕዝብ ሆኑና አምላክ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባ። ከጊዜ በኋላ ይህ ሕዝብ ከአይሁዶችና ከአሕዛብ የተውጣጡ አባላትን ያቀፈ ሆኗል። በመጨረሻው ቁጥራቸው 144, 000 ይሞላል። — ገላትያ 3:26–29፣ ራእይ 14:1
8. የመንግሥቱ ወራሾች ከሰማዩ አባታቸው ጋር ያላቸው ዝምድና በሙሴ ሕግ ስር የነበሩት አይሁዶች ከነበራቸው ሁኔታ የሚለየው እንዴት ነው?
ገላትያ 4:6, 7) በአረማይክ ቋንቋ “አባ” የሚለው ቃል “አባት” ማለት ነው። ሆኖም ልጆች አባታቸውን በፍቅር ስሜት ለመጥራት የሚጠቀሙበትም ቃል ነው። የኢየሱስ መሥዋዕት ብልጫ ያለው በመሆኑና በማይገባን የአምላክ ደግነት ምክንያት እነዚህ በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖች ከአምላክ ጋር ያላቸው ዝምድና ፍጽምና የሌላቸው ሰዎች በሙሴ ሕግ ስር ከነበራቸው ዝምድና የላቀ ነው። ይሁን እንጂ ወደፊት የሚያገኙት ሽልማት ከዚህ ይበልጥ አስደናቂ ይሆናል።
8 የእነዚህ የሰማያዊው መንግሥት ወራሽ ቀሪዎች አሁንም ገና አለፍጽምና ቢኖርባቸውም ከአባታቸው ጋር በጣም ውድ የሆነና የቀረበ ዝምድና አላቸው። ስለዚህ ጉዳይ ጳውሎስ “ልጆችም ስለሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮህ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ። ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፣ ልጅም ከሆንክ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ” ብሎ ጽፏል። (9. ሙሉ የልጅነት አቋም ማግኘታቸው ምን ማለት ይሆናል?
9 እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ከሆኑ ወደማይጠፋ ሕይወት በመነሣት የተሟላ የልጅነት አቋም ያገኛሉ። በሰማይ በይሖዋ ፊት አንድ ሆነው የማገልገል መብት ይኖራቸዋል። ከእነዚህ የአምላክ ልጆች መካከል በአሁኑ ጊዜ ጥቂቶቹ ብቻ በምድር ላይ ይገኛሉ። — ሮሜ 8:14, 23፤ 1 ዮሐንስ 3:1, 2
“በምድር ያሉትን ነገሮች” መሰብሰብ
10. (ሀ) “በምድር ያሉት ነገሮች” ምንድን ናቸው? እነርሱስ ወደ አምልኮ አንድነት የተሰበሰቡት ከመቼ ጀምሮ ነው? (ለ) ከይሖዋ ጋር ምን ዝምድና አላቸው?
10 የሰማያዊ ሕይወት ተስፋ ያላቸው ሰዎች ወደ አምላክ ቤተሰብ እንዲሰበሰቡ ያስቻለው የአምላክ “አስተዳደር” ትኩረቱን ‘በምድር ወዳሉት ነገሮችም’ ይመልሳል። በክርስቶስ መሥዋዕት ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች በተለይ ከ1935 ወዲህ በምድር ላይ የዘላለም ሕይወት ከማግኘት ተስፋ ጋር ሲሰበሰቡ ቆይተዋል። እነርሱም ሶፎንያስ 3:9፤ ኢሳይያስ 2:2, 3) ይሖዋ የሕይወት ምንጭ እንደሆነ በማመን በጠለቀ አክብሮት “አባት” ብለው ይጠሩታል። ይሖዋ ከልጆቹ የሚጠብቀውን ነገር ለማሟላት ጠባዮቹን ለማንፀባረቅ ከልብ ይጥራሉ። በፈሰሰው የኢየሱስ ደም ላይ ባላቸው እምነት መሠረት በፊቱ ሞገስ አግኝተው ይቆማሉ። (ማቴዎስ 6:9፤ ራእይ 7:9, 14) ይሁን እንጂ አምላክ እነርሱን ሙሉ በሙሉ ልጆቹ አድርጎ የሚቀበልበት ጊዜ ገና ወደፊት መምጣት ያለበት መሆኑን ያውቃሉ።
ከቅቡዓን ቀሪዎች ጋር ጎን ለጎን እየሄዱ የይሖዋን ስም ታላቅ ለማድረግ ይጥራሉ፤ አምልኮቱንም ከፍ ከፍ ያደርጋሉ። (11. (ሀ) ሮሜ 8:19–21 ለሰው ልጆች ምን ተስፋ ይዞላቸዋል? (ለ) “የአምላክ ልጆች” በጉጉት የሚጠብቁት “መገለጥ” ምንድን ነው?
11 ሮሜ 8:19–21 እንደሚያሳየው “የአምላክን ልጆች መገለጥ” በጉጉት ይጠብቃሉ፤ ምክንያቱም በዚያን ጊዜ እነዚህ ሰብአዊ ፍጥረታት “ከጥፋት ባርነት” ነፃነት ስለሚያገኙ ነው። ይህ “መገለጥ” የሚጀምረው ሰማያዊ ሽልማታቸውን ያገኙት በመንፈስ የተቀቡ የአምላክ ልጆች በክብር ከፍ ከተደረገው ጌታቸው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመሆን ሥራ መጀመራቸውን የሚያሳይ ማስረጃ በምድር ያሉት ሰዎች ሲመለከቱ ነው። የጠቅላላው ክፉ የነገሮች ሥርዓት መጥፋት የዚህ እንቅስቃሴ መግለጫ ይሆናል። ከዚያም በኋላ እነዚህ “የአምላክ ልጆች” ከክርስቶስ ጋር ነገሥታትና ካህናት የሚሆኑበት የሺው ዓመት የክርስቶስ ግዛት በረከቶቹን ማዝነብ ይጀምራል። — ራእይ 2:26, 27፣ 20:6
12. በመንፈስ የተቀቡት አሸናፊዎቹ የአምላክ ልጆች ከታላቁ መከራ በኋላ የትኛውን የምስጋና ዝማሬ ከሌሎች ጋር ይዘምራሉ? እርሱስ ምን ማለት ነው?
12 ከክርስቶስ ጋር አንድ ላይ መኖር የጀመሩት የአምላክ ልጆች ታላቁ መከራ አልፎ ከሌሎች ጋር ሆነው ከፍ ባለ ድምጽ አምላክን የሚያወድሱበት ጊዜ ሲመጣ እንዴት አስደሳች ይሆናል! በደስታ እንዲህ እያሉ ይዘምራሉ:- “ሁሉን የምትችለው ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ሥራዎችህ ታላቅና አስደናቂ ናቸው። የዘላለም ንጉሥ ሆይ፣ መንገዶችህ ጽድቅ ናቸው። ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ብቻ ታማኝ ነህና በእውነቱ አንተን የማይፈራና ስምህን የማያከብር ማን ነው? የጽድቅ ትእዛዞችህ ስለተገለጡ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፣ በፊትህም ይሰግዳሉ።” (ራእይ 15:3, 4 አዓት) አዎን፣ በፊት ከነበሩት ልዩ ልዩ አሕዛብ የተውጣጡ የሰው ልጆች በሙሉ በእውነተኛው አምላክ አምልኮ አንድ ይሆናሉ። በመታሰቢያ መቃብር ውስጥ ያሉትም ሳይቀሩ ይነሱና ከሌሎቹ ጋር ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይሖዋን ለማመስገን ዕድል ያገኛሉ።
13. ከታላቁ መከራ የተረፉት ሰዎች ወዲያው ምን አስደናቂ ነፃነት ያገኛሉ?
2 ቆሮንቶስ 4:4፤ ራእይ 20:1–3) የሐሰት ሃይማኖት አፍቃሪውን አምላካችን በውሸት መወከሉና ሰብአዊውን ኅብረተሰብ የሚከፋፍል ኃይል መሆኑ ይቀራል። የእውነተኛው አምላክ አገልጋዮች የመንግሥት ባለሥልጣኖች ይፈጽሙባቸው የነበረው ግፍና ብዝበዛ ያቆማል። ከታላቁ መከራ የሚተርፉት ሁሉ እንዴት ያለ ታላቅ ነፃነት ይጠብቃቸዋል ማለት ነው!
13 ከዚያ በኋላ ሰይጣን ዲያብሎስ የዚህ የነገሮች ሥርዓት አምላክ መሆኑ ያከትማል። በምድር የሚኖሩት ይሖዋን የሚያመልኩ ሰዎችም ከዚያ በኋላ ከሰይጣን ክፉ ግፊቶች ጋር መታገሉ ይቀርላቸዋል። (14. ከኃጢአትና ከውጤቶቹ በሙሉ የሚላቀቁት በምን አማካኝነት ነው?
14 ኢየሱስ ክርስቶስ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” እንደመሆኑ መጠን በመሥዋዕቱ ዋጋ ተጠቅሞ የሰውን ልጆች የቀድሞ ኃጢአቶች በሙሉ ይደመስሳል። (ዮሐንስ 1:29) ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ ሰዎችን ኃጢአታቸው ይቅር እንደተባለላቸው ሲነግራቸው ለዚያ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ሕመማቸውን ይፈውስላቸው ነበር። (ማቴዎስ 9:1–7) በተመሳሳይም ሰማይ ሆኖ ዓይነ ስውሮችን፣ ጆሮአቸው የደነቆረባቸውን፣ ዲዳዎችን፣ አካለ ጎደሎዎችን፣ የአእምሮና ሌላ ሕመም ያለባቸውን ሁሉ በተአምር ይፈውሳቸዋል። ታዛዥና ፈቃደኛ የሆኑት በሙሉ ራሳቸውን ቀስ በቀስ እየለወጡ ከአምላከ የጽድቅ መንገዶች ጋር ሲያስተካክሉ “የኃጢአት ሕግ” ከሰውነታቸው ጨርሶ ይደመሰስላቸዋል። በዚህ ምክንያት ድርጊታቸው፣ ሐሳባቸውና የልባቸው ምኞት ሁሉ ራሳቸውንም ሆነ አምላክን የሚያስደስት ይሆናል። (ሮሜ 7:21–23፤ ከኢሳይያስ 25:7, 8 እና ከራእይ 21:3, 4 ጋር አወዳድር) ሺው ዓመት ከማለቁ በፊት በሚደረግላቸው እርዳታ ምክንያት ወደተሟላ ሰብአዊ ፍጽምና ይደርሳሉ። ከኃጢአትም ሆነ ከአሳዛኝ ውጤቶቹ ሁሉ ይላቀቃሉ። ምድርን በሙሉ በሚያለብሰው ገነት ውስጥ እየኖሩ ‘የአምላክን ምሳሌና መልክ’ በትክክል ያንፀባርቃሉ። — ዘፍ. 1:26
15. በሺው ዓመት ፍጻሜ ላይ ኢየሱስ ምን ያደርጋል? ከምንስ ዓላማ ጋር?
15 ክርስቶስ የሰውን ልጆች ወደ ፍጽምና ካደረሳቸው በኋላ ይህንን እንዲያከናውን ከአባቱ ተሰጥቶት የነበረውን ሥልጣን በ1 ቆሮንቶስ 15:28 ላይ አስቀድሞ እንደተነገረው ኢየሱስ “ሁሉ ከተገዛለት በኋላ እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።”
መልሶ ያስረክባል።16. ወደ ፍጽምና የደረሱት የሰው ልጆች በዚህ ጊዜ ምን ይመጣባቸዋል? ለምንስ?
16 ወደ ፍጽምና የደረሱት የሰው ልጆች ሕያውና እውነተኛ የሆነውን አንድ አምላክ ለዘላለም ማገልገል የማይታጠፍ ምርጫቸው መሆኑን እንዲያሳዩ በዚህ ጊዜ አንድ አጋጣሚ ይቀርብላቸዋል። ይሖዋ ወደ ፍጽምና የደረሱትን ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንደ ልጆቹ አድርጐ ከመቀበሉ በፊት የመጨረሻው ማጣሪያ ፈተና እንዲመጣባቸው ይፈቅዳል። ሰይጣንና አጋንንቱ ከታሰሩበት ጥልቅ ይወጣሉ። ይህ ሁኔታ ለይሖዋ እውነተኛ ፍቅር ባላቸው ላይ የሚያመጣው ዘላቂ ጉዳት አይኖርም። ታማኝ ባለመሆን በሰይጣን ተመርተው ለይሖዋ አንታዘዝም ያሉት ግን ከመጀመሪያው ዓመፀኛና ከአጋንንቱ ጋር ለዘላለም ይጠፋሉ። — ራእይ 20:7–10
17. ይሖዋ የሰጠው የተስፋ ቃል ይፈጸም ዘንድ የማሰብ ችሎታ ባላቸው ፍጥረታት መካከል እንደገና ምን ሁኔታ ይፈጠራል?
17 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ወደ ፍጽምና የደረሱትንና የመጨረሻውን ወሳኝ ፈተና ያለፉትን በክርስቶስ በኩል ልጆቹ አድርጐ በፍቅር ይቀበላቸዋል። እነርሱም ከዚያ በኋላ “የአምላክን ልጆች ታላቅ ነፃነት” በተሟላ ሁኔታ በሕይወታቸው ላይ ያያሉ። (ሮሜ 8:21) በመጨረሻው አንድነት ያለው የአምላክ ጽንፈ ዓለማዊ ቤተሰብ አባል ይሆናሉ። ይህ ቤተሰብ የዘላለም አምላኩ፣ ጽንፈ ዓለማዊ የበላይ ገዥውና አፍቃሪ አባቱ ይሖዋ ብቻ ሆኖ ይኖራል። በዚያን ጊዜ በሰማይም ሆነ በምድር የሚገኙት የማሰብ ችሎታ ያላቸው የይሖዋ ፍጥረታት በሙሉ እውነተኛው አንድ አምላክ ባስገኘው አምልኮ ውስጥ እንደገና ተጠቃለው አንድ ይሆናሉ።
የክለሣ ውይይት
● በዔደን ዓመፅ ከመጀመሩ በፊት ይሖዋን የሚያመልኩ ሁሉ ከእርሱ ጋር እንዴት ያለ ዝምድና ነበራቸው?
● የአምላክ ልጆች በሆኑት ላይ ምን ኃላፊነት ተጥሏል?
● ዛሬ የአምላክ ልጆች እነማን ናቸው? ወደፊት የአምላክ ልጆች የሚሆኑትስ እነማን ናቸው? ይህስ ይሖዋ አንድ አምልኮ ብቻ እንዲኖር ካለው ዓላማ ጋር የተያያዘው እንዴት ነው?
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]