በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትምህርት 1

አምላክ ሰማይንና ምድርን ሠራ

አምላክ ሰማይንና ምድርን ሠራ

ይሖዋ አምላክ ፈጣሪያችን ነው። በዓይን የሚታዩትንም ሆነ የማይታዩትን ነገሮች በሙሉ የሠራው እሱ ነው። በዓይን የሚታዩትን ነገሮች ከመሥራቱ በፊት ብዙ መላእክትን ፈጥሯል። መላእክት እነማን እንደሆኑ ታውቃለህ? መላእክት የይሖዋ አገልጋዮች ናቸው። አምላክን ማየት እንደማንችል ሁሉ እነሱንም ማየት አንችልም። አምላክ የፈጠረው የመጀመሪያው መልአክ የእሱ ረዳት ሆኖ አገልግሏል። ይህ መልአክ ይሖዋ ከዋክብትንና ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ሲሠራ አብሮት ሠርቷል። ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዷ ውብ መኖሪያችን የሆነችው ምድር ነች።

ከዚያም ይሖዋ ምድርን ለእንስሳትና ለሰዎች ተስማሚ መኖሪያ እንድትሆን አድርጎ አዘጋጃት። ፀሐይ ብርሃኗን ምድር ላይ እንድታበራ አደረገ። ተራሮችን፣ ወንዞችንና ባሕርን ሠራ።

ከዚያስ ምን አደረገ? ይሖዋ ‘ሣርን፣ ተክሎችንና ዛፎችን እፈጥራለሁ’ አለ። ብዙ ዓይነት ፍራፍሬ፣ አትክልትና አበቦች መብቀል ጀመሩ። ከዚያም ይሖዋ የሚበርሩ፣ የሚዋኙና መሬት ላይ የሚሳቡ እንስሳትን በሙሉ ፈጠረ። በተጨማሪም እንደ አይጥ ያሉ ትናንሽ እንስሳትንና እንደ ዝሆን ያሉ ትላልቅ እንስሳትን ፈጠረ። አንተ በጣም የምትወደው እንስሳ የቱ ነው?

ቀጥሎም ይሖዋ አብሮት እየሠራ የነበረውን የመጀመሪያውን መልአክ ‘ሰውን እንሥራ’ አለው። ሰዎች ከእንስሳት የተለዩ ናቸው። አዳዲስ ነገሮችን መፈልሰፍ ወይም መሥራት ይችላሉ። ከዚህም ሌላ መናገር፣ መሳቅና መጸለይ ይችላሉ። እንዲሁም ምድርንና እንስሳትን ይንከባከባሉ። አምላክ መጀመሪያ የፈጠረው ሰው ማን እንደሆነ ታውቃለህ? እስቲ እንመልከት።

“በመጀመሪያ አምላክ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።”—ዘፍጥረት 1:1