የክፍል 10 ማስተዋወቂያ
ይሖዋ ሁሉንም የሚገዛ ንጉሥ ነው። ከጥንት ዘመን አንስቶ ሁሉንም ነገር ሲቆጣጠር ኖሯል፤ ወደፊትም ቢሆን ሁሉንም ነገር የሚቆጣጠረው እሱ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ኤርምያስ ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ በነበረበት ወቅት ከሞት ታድጎታል። ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን ደግሞ ከእቶን እሳት ውስጥ አውጥቷቸዋል፤ እንዲሁም ዳንኤልን ከአንበሶች አድኖታል። አስቴርም ሕዝቧን ማዳን እንድትችል ረድቷታል። ከዚህም ሌላ ይሖዋ ክፋት ለዘላለም እንዲቀጥል አይፈቅድም። ስለ ግዙፉ ምስልና ስለ ትልቁ ዛፍ የሚናገሩት ትንቢቶች የይሖዋ መንግሥት በቅርቡ ክፋትን በሙሉ አስወግዶ ምድርን እንደሚገዛ ያረጋግጣሉ።
በዚህ ክፍል ውስጥ
ትምህርት 59
ይሖዋን የታዘዙ አራት ልጆች
አይሁዳውያን ወጣቶች በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር ቤተ መንግሥት ውስጥ በነበሩበት ጊዜም ጭምር ለይሖዋ ታማኝ ለመሆን ወስነው ነበር።